Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Selam/
Senior Member
Posts: 17690
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Oromos have 100% right to take Tigray

Post by Selam/ » 05 Apr 2021, 16:38

የታላቅ ብርታንያ የአየርላንድ ንግስተ ወኩሉ አድያምሃ ቢክቶርያ።

የተላከ ከንጉሠነገሥት ዮሐንስ ዘኢትዮጵያ ወኩሉ አደያምሃ። እጅግ ደስ አለኝ። ደብዳቤየንና የሰደድሁትን ገፀ በረከት በሰደድኋቸው አሽከሮቹ እጅ ተቀበሉ ብሰማ። ደግሞም እጅ አጥብቆ ደስ አለኝ በጅዎ የታተመ ደብዳቤና ፲ ሳጥን ማለፊያ ገፀበረከት የያዘ በተቀበልሁ ጊዜ። የእርሶም ሎሌ ካፒቴን ፒራዶ የሚባል በአደን በጢስ መርከብ የርስዎን ደብዳቤና ገፀበረከት ምጥዋ ድረስ ይዞ መጣ ፲ ሳጥን ሰደደልኝ አንዱን ሳጥን አደን ትቼ መጥቼ አለሁ ኋላ እሰድልህ አለሁ ብሎ ላከብኝ። እርስዎ የኢትዮጵያን ታሪክ ያውቃሉ። መሃመድ ግራኝ የሚባል እስላም አላዊ ተነስቶ ነበር በአገራችን።ንጉሥ ገደለ ህዝበ ክርስትያንን ሁሉ አረደ ገደለ የክርስትያንን ሁሉ ደም አፈሰሰ አብያተ ክርስትያናትን ሁሉ ተኮሰ አቃጠለ። ከሞት የቀሩትን ምዕመናን አገራቸውን አስለቅቆ ወደ ምድረበዳ ተሰደዱ። አሁንም ከግዛቴ ውስጥ አንዲት አገር አለች ስምዋ አዘቦ የምትባል በውስጥዋ ያሉት ሰዎች እስላም ጋላ ናቸው እነዚያ ሸፈቱ እኔም ዘመትሁባቸሁ የወጣሁበት ነገር በእግዚአብሔር ኀይል ቀንቶኝ ተመለስሁ ወደ ከተማየ አድዋ በኋላየ እስማኤል ባሻ ንጉሥ ነኝ ብሎ ምንሰጅር ቤን ሹሞ ሰደደው ከብዙ ወታደር ጋራ መረብ ምላሽ የትግሬን እኩሌታ የኢትዮጵያን የዳር የዳሩን አገር ሁሉ። ደግሞ እነዚህ ሻንቅሎች የአገርዎን ሰዎች ምስተር ቶማስን ከሚስቱ ከሰዎቹ ጋር የገደሉ ናቸው ነጋዴንም ሁሉ ከትግሬ ወደ ወልቃይት ከወልቃይት የሚመላለሰውን ይገላሉ የክርስትያንን ሁሉ ደም ያፈሳሉ። በዚህ ሁሉ ክፋታቸው አንዱን አሽከሬን ደጅ አዝማቹን ሹሜ ሰደድሁት በነዚያ ላይ ሊቀጣቸው ብዬ። እስማኤል ባሻ እንዲህ ብሎ ጣፈልኝ ይህን አሽከርህን ቅጣልኝ ያለዚያ ለኔ ስደድልኝ እንደፈቀደኝ አድርጌ ልቅጣው ብሎ ከጥቂት ቀን በፊት የኔን ምክር ስማ ብለው ደብዳቤ ፅፈው ልከውልኝ ነበር። እኔም ምክረዎን ሰምቼ ካገሬ ዝም ብዬ ተቀምጬ ሳለሁ ዋግሹም ጎበዜ ጦሩን ሁሉ ሰብስቦ ሊወጋኝ መጣ እኔ ግን ድል አደረግሁት በእግዚአብሔር ኅይል። ከሹማምቶቹ ከሰራዊቱ ጋር ያዝሁት ዛሬም ከኔ ጋር አለ። አሁንም እስማኤል ባሻ የሚበድለኝን በደል ሁሉ ይፍረዱት እኔ አንድ በደል እንኳን አልበደልሁትም። እኔ ከሮም ካሉ ነገሥታት ሁሉ ከርስዎ በቀር የማምነው ሌላ ወዳጅ የለኝም የክርስትያን ዘመድ ክርስትያን ነውና። ከመሃመድ ግራኝ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የኢትዮጵያ ነገሥታት እየደከሙ ሄዱ እስላሞች ግን እየበረቱ ይኖራሉ የያዙትን አገር አልበቃቸው ብሎ ኢትዮጵያን ሁሉ ጨርሰው ሊገዙ ይፈልጋሉ። እኔ ከዚህ ቀደም ተስፋ ነበረኝ እስላሞች በኅይል የወሰዱትን አገር በብዙ ዘመናት አገሬን በእንግሊዝ መንግሥት ኅይል ይመለስልኝ አል ብየ። ዛሬ ግን ኢትዮጵያን ሁሉ ሊገዙ ይፈልጋሉ። በጄ ያለውን ሁሉ ይህን ሁሉ ፃፍኩልዎ የሚሉኝን ሁሉ ምክር ልስማ ብዬ ነው የክርስትያን ሁሉ ደም በከንቱ ሲፈስ አሎድምና የርሶን ምክር ልስማ። ይህንን ደብዳቤ ባንድ ባገርዎ ልጅ በታመነ ሰደድሁልዎ ጀነራል ከርካም በሚባል ቸኩየ አለሁና ምላሹን ቶሎ ቀልጥፈህ ይዘህልኝ ና ብየው አለሁ። ደግሞ አንድ ነገር እለምነዎ አለሁ። ግፌን ሁሉ የሚአይልኝ አንድ ደህና ሰው ጠባዩ ከሰው ጋር የተስማማ ቢሰዱልኝ እወድ አለሁ ምስክር ይሆነኛል ብየ ነው ደመዙን እኔ እሰጥ አለሁ። ደግሞ ኩራተ ርእሱ የሚባል ስዕል የጌታችን የመድኅኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስዕል ነው ንጉሥ ቴዎድሮስ ከጎንደር ወደ መቅደላ ከብዙ መፅሃፍት ጋር ወስደው ዳርዳሩ በወርቅ መህሉ በቀለም ተስሎ አል። እርሱን ቢሰዱልኝ እወድአለሁ። ደግሞ ክብረነገሥት የሚባል መፅሃፍ አለ አብሮ ሄዶ አል የአገሬን ሁሉ የሹማምንቱን የአብያተ ክርስትያናትን ስራት የሚነግር ነው ባገሬ ተፋልሶ ሁኖብኝ አል። አሁንም ሁለቱን ክብረነገሥቱንና ኩራተ ርእሱን ቢሰዱልኝ እወድ አለሁ ካለበት ሁሉ አስፈልገው። ደግሞ አንድ ነገር ልንገርዎ ይስሙኝ የካቶሊኮችን ነገር ባገርህ የኛን ሃይማኖት እናስተምር አሉኝ።እኔ ግን መለስሁላቼው በሥላሴ ስም ተጠምቄ አለሁ። ክርስቶስን በወንጌል አምናለሁ የሚያስተምረኝም በማርቆስ ወንበር የተቀመጠ የማርቆስን እጣ የያዘ ከእስክንድርያ እርሱ ነው ለሕዝቤም የሚያስተምሩ እርሱ የሾማቸው ቀሳውስት አሉኝ። ደግሞ አልኋቼው ማስተማር ብትፈልጉ በዚች ዓለም በሥላሴ ስም ያልተጠመቁ ክርስቶስን በወንጌል የማያምኑ ብዙአሕዛብ አሉ እነዚያን አስተምሩ አልኋቸው ስለዚህ ነገር ነው ዋግ ሹም ጎበዜን ደብዳቤ ልከው ና ብለው በኢትዮጵያ ያሉ የክርስትያንን ደም ያስፈሰሱ እነዚያ ናቸው። ደግሞ ካለፍቃዴ ቤተክርስትያን ሰሩ ካገሬ ሕዝቡንም ሁሉ ወደኛ ግብር እንዳትገብሩ ሺፍታ አመጠኞች አደረጉአቸው እኔም አንድ ሹሜን ሂድ ግብር አውጣ ብየ ሰደድሁት እነዚያም አንገብርም እምቢ አሉ አዝጄ የሰደድሁት ሹም የነዚያን አመጠኞች ቤት ሲተኩስ አብሮ ተኮሰባቸው የካቶሊኮችን ነገር ይወቁ የኔን ስም ሊአከፉት ይህን ሁሉ የሚያደርገኝ ምንስጅ ቤ ነው ቱርክ መርቼ አስገድልህ አለሁ ብሎ ፎከረልኝ ግፌን ይውት። ደግሞ የካቶሊኮችን የክፋታቸውን ሁሉ ወረቀት ደብዳቤ ፅፌ ወደእርሶ ብሰድ ምንስጀር ቤ ምጥዋ ላይ ቀምቶ ከባህር አገባው። እኔም ደብዳቤ መፃፌ ስለ አመንሆዎ ነው አሁንም ነገር በዛ ብለው ኣይሰለቹኝ።

ተጽሕፈ በ፰ ቀን ነሐሴ በ፲ወ፰፻ ፷ወ፬ አመተ ምሕረት በአድዋ ከተማ