Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11590
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

ኢትዮጵያ ሰላሟን አረጋግጣ እና ህልውናዋን አስጠብቃ ወደፊት መራመድ የምትፈልግ ከሆነ በድርድር መፍታት ያለባት ጉዳዮች የሚከተሉት ናቸው:- By Andinet Zeleke Bekele

Post by sarcasm » 04 Apr 2021, 07:58

ኢትዮጵያ ሰላሟን አረጋግጣ እና ህልውናዋን አስጠብቃ ወደፊት መራመድ የምትፈልግ ከሆነ በድርድር መፍታት ያለባት ጉዳዮች የሚከተሉት ናቸው:-

1. ከትግራይ ህዝብ እና በክልሉ ከተመረጠው ህወሃት ጋር ድርድር ማድረግ:: እምቢ ካሉም ለምና አስለምና!

2. ከኦነግ (OLA) ጋር ድርድር ማድረግ:: እምቢ ካለ ለምና አስለምና!

3. የኤርትራ ጦር ከትግራይ ማስወጣት እምቢ ካለ በጉልበት::

4. የአማራ ልዩ ሀይልን ከትግራይ እና ከኦሮሚያ ክልሎች ማስወጣት:: እምቢ የማለት አቅም ስለሌለው ውጣ ከተባለ ይወጣል::

5. የታሰሩ የፓለቲካ እስረኞች የሆኑ እነ ጃዋር መሀመድ; እስክንድር ነጋ; በቀለ ገርባ; የመሳሰሉትን እና የትግራይ ወረራን ተከትሎ የታሰሩትን በሙሉ ያለምንም ቅድመሁኔታ መፍታት::

6. ከግብፅ እና ሱዳን ጋር የታላቁ ህዳሴ ግድብን አስመልክቶ በUN, US እና EU አደራዳሪዎች ፊት መደራደር:: (አሁን ላይ ኢትዮጵያ እነዚህን አደራዳሪዎች በሙሉ አልፈልግም ብላለች)

7. ከሀገራዊ ምርጫ በፊት ሀገር አቀፍ ንግግር እና መግባባት ላይ እንዲደረስ ከሁሉም ፓርቲዎች ጋር ተቀራርቦ በመመካከር መስራት ያስፈልጋል:: ንጉሳዊ ስርአት ያለ ይመስል #ባእለ_ሲመት የሚባል ቀልዶች መቅረት ይኖርበታል::

ከላይ የተዘረዘሩት ጉዳዮች በቅርብ በድርድር ካልተፈቱ የኢትዮጵያ መከራ; የዲፕሎማሲ ማእቀቦች; ጦርነቶች; የጦር ወንጀል ክሶች; የግብፅና ሱዳን ጥቃት; የኑሮ ውድነት ተንሰራፍቶ መቀጠል; ነዳጅ መጥፋት; የውጭ ምንዛሪ ከፍተኛ እጥረት; የአሻጥር ግድያዎች እና የመሳስሉት ከአሁኑ በባሰ እየሰፉ ይሄዱና ኢትዮጵያን የህልውና አደጋ ላይ ይጥሏታል::


https://www.facebook.com/andinetzeleke. ... 6041430279