ሃገረ ኤርትራና መንግስቷ፡ ኢትዮጵያ እንድትረጋጋ በሚል ቅዱስ አላማ፡ ለኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት ተጦቢያ መንግስትና ተመሪያቸው ተብልጽግናዎች ጋር የቀጠናውን ነቀርሳ ለመመንገል ሳያሰልሱ እየተጉ ይገኛሉ። ይህ በንዲህ እንዳለ ብልጽግና ውስጥ የተሰገሰጉ የቀንጅቦችና የደርግና የአጤው መንግሥት ቅሪቶች፡ በሃገራችን በልዑላዊቷ በኤርትራ ላይ ለርካሽ ቦለቲካዊ ዓላማ ሲሉ፡ በጀርባ ነገር መጎንጎን ነገር መሸመንና ነገር መሸረብን እንደተያያዙት የሚያመላክት አካሄድን፡ ልቦና የመላው ሰፊው የኤርትራ ህዝብ ሲታዘብ፡ እንዲህ የምትለዋን ሁነኛ ምሳሌው ያስታውሳል።
ኣነ ክዳን እሰፍየላ፡ ንሳ ነገር ትኣልመለይ
ትርጉም
እኔ ልብስ እየሰፋሁላት፡ እሷ ነገር ትሸምንል[ብ]ኛለች። [እንደ የብልጥግናው የጅብ ችኩል እንደ ዲና]
ኣብዪና ዲና እየሰማችሁ ነውን? ኤርትራዊቷ ሁነኛ ምሳሌ እንዲህም ልትተረጎም ትችላለች
እኔ ልብስ እየሰፋሁላት፡ እሷ ነገር ትጎነጉንል[ብ]ኛለች። [እንደ የብልጥግናው የጅብ ችኩል እንደ ዲና]
ኣብዪና ዲና ይሰማል ወይ? መደነጋገር እንዳይፈጠር እንዲህም እንተረጉማታለን
እኔ ልብስ እየሰፋሁላት፡ እሷ ነገር ትሸርብል[ብ]ኛለች። [በብልጥግናው የጅብ ችኩል በዲና ቤት፡ ነገር ‘ሹራብ’ መሆኑ ነው!]
‘ብልጤ’ ብልጥግና፡ በውስጥህ የተሰገሰጉ የጅብ ችኩሎችንና ጅቦችን በመላ አራግፍ።
ክብር ለጨዋው ለዴመቀ መኮነን!