Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
AbebeB
Member+
Posts: 7694
Joined: 15 Oct 2016, 10:31

ኦነግ በታሪኩ የስርአት እንጂ የህዝብ ጠላት ኖሮት አያውቅም።ወደፊትም አይኖረውም። ዛሬ ላይ ሀበሾችም የሚቀበሉት ሀቅ ሆኖአል፡፡

Post by AbebeB » 02 Apr 2021, 13:34

ኦነግ በታሪኩ የስርአት እንጂ የህዝብ ጠላት ኖሮት አያውቅም።ወደፊትም አይኖረውም። ዛሬ ላይ ሀበሾችም የሚቀበሉት ሀቅ ሆኖአል፡፡

በብዛት ከ ዩኒቨርስቲዎች የተመረቁ፣ በማንነታቸው ምክንያት በአምባገነኖች ከትምህርት ቤት ታፍሰው ወደ እስርቤት የተጋዙ ተማሪዎች ናቸው።
ብዙዎቹ ገዳዩን ስርአት በመሸሽ ወደ ጫካ ሲያመሩ አብይ አህመድ ያሰማራቸው ነብሰበላዎች ቤተሰቦቻቸው ቤት ድረስ እናትና አባቶቻቸው ተገድለዋል።

የዛሬ አመት አከባቢ ወለጋ ላይ ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር ጋር የተቀላቀለው ወጣት ለዚህ ምሳሌ ሊሆን ይችላል።
የተወለደው ወለጋ ላይ ነው። ቤተሰቦቹ አማራዎች መሆናቸው ከስርአቱ ጭቆና ሊያድነው አልቻለም። እናም የኦሮሞ ነጻነት ታጋዮችን ተቀላቀለ። ይህ መረጃ የደረሳቸው የመንግስት ደህንነቶች አዛውንት እናት አባቶቹኖ ቤታቸው ውስጥ በጥይት ደብድበው ነው የገደሏቸው። ያ ወጣት ዛሬም ከኦሮሞ ነጻነት ታጋዮች ጋር ትግል ላይ ይገኛል።
ኦነግን ማጠልሸት፣ በኛ ዘመን የተጀመረ አይደለም
አዎ ትናንት…

የኦነግን ስም ለማቆሸሽ በደኖ፣ አርባ ጉጉ፣ ወተር፣ አረካ፣ አሰቦት ገዳም ወዘተ… ቦታዎች ላይ “የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሰራዊት የፈጸማቸው” ተብሎ የተፈበረኩት ቪድዮዎችና የጥላቻ ስም ማጥፋት ተግባራት የሚዘገንኑ ነበሩ፡፡
ኦነግ ፈጸመው የተባለውን ሌሎች እንዲያምኑህ ብቻ እናትን ገድሎ የአንድ አመት ህጻን ከእናቷ በድን ጡት ስትጠባምኮ ተመልክተናል፡፡
ኦነግን በህዝብ ዘንድ ሳጥናኤልን ለማድረግ በማለት ብቻ የሰማንያ አመትን ምስኪን እናት አንገታቸው ተቀንጥሶ ለብቻ ወድቆ የሰራችሁትን ፊልም አይተናል፡፡

“ኦነግ ዘጠኝ የአማራ ብሄር ተወላጆችን (ሙሉ ቤተሰብን) በር ዘግቶባቸው አቃጠላቸው” በማለት እንደ ከሰል ያረረ የህጻን ገላን ጭምር ህዝብ በቀበሌ እየወጣ እንዲመለከት ሲደረግ ኦነግን የክፋት ጥግ ተደርጎ ሰራበት የተኖረው በህዝብ የነበረውን ተቀባይነትን ለመደምሰስ የታሰበ ነበር፡፡
መረሳት የሌለበት በዚህ ሁሉ፣በእያንዳንዷ ተግባር ውስጥ የትናንቷ ኦህዴድ/ኦዴፓ ያልተሳተፈችበት የለም፡፡
ቢያንስ ከትላንት መማር ሲገባቸው በነ ታዬ ዳንደአ በመሰሉ ርካሽ ቅልብ ካድሬዎቻቸው “ኦነግ የሰውን ስጋ አስበላ” እስኪባል ወራዳ እና የሰው ልጅ በአምሳያው የማይፈጽመውን ተግባር በኦነግ ላይ እየደገሙበት ሊያጠፉት ቢፍገመገሙም ኦነግ ይበልጥ ሀይሉ እየበረታ ከሚጠብቁት በላይ እየጠነከረ ዛሬ ደርሷል።

ትናንት ይህን ስላላቹ ኦነግ አልጠፋም
እመኑኝ ፈጽሞ ኦነግ አይጠፋም

Dabessa Gemelal