Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11590
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Southern region in Ethiopia went bankrupt

Post by sarcasm » 01 Apr 2021, 18:39

«የደቡብ ክልል የፋይናንስ ቀውስ ደሞዝ መክፈል እስኪሳነው ደርሷል» ጥናት

የደቡብ ክልል መንግስት ባጋጠመው የበጀትና የጥሬ ገንዘብ ችግር ምክንያት በአንዳንድ የክልሉ መዋቅሮች ደመወዝ መክፈል በማይቻልበት ደረጃ መድረሱን የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ አደረኩት ባለው ጥናት ይፋ አደረገ፡፡ ለሥራ ማስኬጃ ወጪዎች የተጋነነ ክፍያ መፈጸም ለጥሬ ገንዘቡ እጥረት ምክንያት ናቸው ተብሏል።

የደቡብ ክልል መንግሥት ባጋጠመው የበጀትና የጥሬ ገንዘብ ችግር ምክንያት በአንዳንድ የክልሉ መዋቅሮች ደመወዝ መክፈል በማይቻልበት ደረጃ መድረሱን የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ አደረኩት ባለው ጥናት ይፋ አደረገ፡፡ የማዳበሪያ ዕዳ ጫና፣ በአንድ መደብ በርካታ ሠራተኞችን መቅጠር፣ የቀን አበል፣ ለተሽከርካሪዎች ነዳጅና ጥገና፣ ለሥራ ማስኬጃ ወጪዎች የተጋነነ ክፍያ መፈጸም ለጥሬ ገንዘቡ እጥረት ምክንያት ናቸው ተብሏል። ይህም አንዳንድ መዋቅሮች ለሠራተኞቻቸው ደሞዝ ለመክፈል እንዳይችሉ ከማድረጉም በላይ ጉዳዩ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ሆኖ ሰላማዊ ሰልፍ እስከመውጣት መደረሱን ጥናቱ አመልክቷል። ዶቼ ቬለ (DW) ያነጋገራቸው የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች በበኩላቸው ክልሉ ከገባበት የፋይናንስ ቀውስ ለመውጣት በቅድሚያ መሠረታዊ ችግሮችን በመለየት የመውጫ ወይም exit strategy በማዘጋጀት ገቢራዊ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል።

https://www.dw.com/am/%E1%8B%A8%E1%8B%B ... a-57079285