Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Masud
Member+
Posts: 8502
Joined: 18 Jun 2013, 09:06

ለሚመለከተው ሁሉ

Post by Masud » 30 Mar 2021, 12:33

የመሬው ነኝ
ለሚመለከተው ሁሉ፦
ጉዳዩ፦ አስቸኳይ የማጣራት ስራ እንዲደረግልን ስለመጠየቅ፤
ይህ The Amhara Informar የተሰኜ የደም ነጋዴዎች ገፅ ትናንትና የክልላችንን ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ አገኘሁ ተሻገርን ለምን መተከል ሄደው ተፈናቃዮችን አይጠይቁም በማለት ሲሳለቅና ሲዘልፍ ውሏል።
ዛሬ ደግሞ የመተከል ተፈናቃዮች የእህል መጋዘን በሴራ እንዲቃጠል ከተደረገ በኋላ ወዲያውኑ ፎቶ አንሺዎችን በመመደብ የመቃጠሉን ዜና ቀድሞ የነገረን ይህ ገፅ ነው።
የሚገርመው የወንጀል ፈፃሚወችን ትክክለኛ መረጃ ለማድበስበስና የማጣራት ሂደቱን አቅጣጫ ለማሳት በአካባቢው የሌለን የኦነግ ቡድን የድርጊቱ ተዋናይ አድርጎ በመክሰስ ሌላ አጀንዳ እየሰጠን ይገኛል።
ስለሆነም ድርጊቱ የተፈፀመው በኦነግ ሸኔ ሳይሆን ይልቁንም በዚህ ገፅ ባለቤቶችና መሰል ተባባሪ እርካሽ የፖለቲካ ነጋዴዎች ለመሆኑ ብዙ ማሳያዎችን ማቅረብ ይቻላል።
አንደኛ ከአሁን በፊት አስተባባሪዎች ነን በሚል ለመተከል ተፈናቃዩች ከተለያዩ ድጋፍ ሰጪ አካላት ሲመጣ የነበረን ድጋፍ መጋዘን የገባ በማስመሰል እና ለተጎጅዎች የተሰጠ በማስመሰል እያስወሩ በጎን ደግሞ ሲሸጡ የነበሩ ሰዎች በህግ እንዳይጠየቁ ሆን ብለው መጋዘኑ እንዲቃጠል በማድረግና ድጋፉ አብሮ የተቃጠለ በማስመሰል ከተጠያቂነት ለመዳን ያደረጉት ሴራ እንደሆነ ይገመታል።
ሁለተኛ ተቆርቋሪዎች መስለው የሚታዩ ካሁን በፊት በወገናችን ሞትና መፈናቀል እርካሽ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት እየዳከሩ ያሉ አረመኔወች ዛሬም በጭካኔ ያደረጉት ሴራ እንደሆነ ግልፅ መሆኑ አያሻማም።
በመሆኑም በጥቂቱ ከላይ ያስቀመጥናቸው አጭር ማሳያዎች ተወስደው በህዝብ ችግር እየነገዱ የሚገኙ እነዚህ አካላትና ልሳናቸው የሆነው The Amhara Informer የተሰኘ አደገኛ የአማራው የጠላት ገፅ ምርመራ እንዲደረግባቸውና ለህግ እንዲቀርቡ እንዲደረግልን እንጠይቃለን።
ግልባጭ/
➢ አገኘሁ ተሻገር -Agegnehu Teshager official
➢ አብርሃም አለኸኝ ጥሩነህ/Abrham Alehegn Tiruneh
➢ ለአብክመ ሰላምና ደህንነት ቢሮ
➢ ለአብክመ አማራ ፖሊስ ኮሚሽን ሚዲያ
➢ Temesgen Tiruneh - ተመስገን ጥሩነህ
➢ #ለኢንሳ