Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11590
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

ዛሬ የትግራይን ጦርነት የደገፈው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሲኖዶስ ፤ በላይ ዘለቀን ፈርሞ ማሰቀሉን ስንቶቻችሁ ታውቃላችሁ?

Post by sarcasm » 15 Mar 2021, 10:20

ዛሬ የትግራይን ጦርነት የደገፈው ሲኖዶስ በላይ ዘለቀን ፈርሞ ማሰቀሉን ስንቶቻችሁ ታውቃላችሁ?

እንደ ዋኖቹ ሃዋርያት እና አበው ሰላምን በመስበክ ፋንታ የትግራይ ጦርነትን የደገፈው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሲኖዶስ በቀደመው ዘመንም ጀግናውን በላይ ዘለቀን እና የንጉስ ተክለሃይማኖት የልጅ ልጅን ደጃዝማች በዛብህን በግፍ አሰቅሏል።

በብሄራዊ ቤተ መፅሃፍት የሚገኘው ያልታተመው የፍርድ ሰነድ እና የበለጠ ገብሬ "የእድሜ ትዝታ" መጻህፍ እንደሚያስረዱት ቤተ ክርስቲያኗ የመጀመሪያ ፖትርያርክ ብላ በሰየመችው በሸዋው ተወላጅ በእጨጌ ገብረ ጊዮርጊስ በሁዋለኛው አቡነ ባስሊዮስ ፊርማ የጎጃሙ አርበኛ በላይ ዘለቀና የንጉስ ተክለ ሃይማኖት የልጅ ልጅ ጀግናው ደጃዝማች በዛብህን ጥር 5 1937 ዓ.ም ከቀኑ በስድስት ሰአት ጃንሜዳ አደባባይ አሰቅላለች! አቡነ ባስሊዮስ በበላይ ዘለቀ ላይ የሞት ፍርድ የፈረዱበት ሰነድ እና ይህንን አሳፋሪ ታሪክ የዘገቡ የታሪክ ፀሃፊዎች አስረጅዎች ናቸው። ሲኖዶሱ መንፈስ ቅዱስ የተለየው በየግዜው ስልጣን የሚጨብጡ ሃይሎች የፖለቲካ አስፈፃሚ የከለባት ስብስብ መሆኑ ከጥንት እስከ አሁን ታይቷል። ይህ የከለባት ስብስብ በጎጃም ላይ ጥላቻ የሚሰቡክ የቤተ ክርስቲያኒቱ መፃህፍት በመንፈስ ቅዱስ አነሳሽነት የተፃፋ ስላልሆነ ይወገዱ ቢባልም አሻፈረኝ እንዳለ ነው። እኛም ለአዲሱ ትውልድ እውነታውን ማሳወቃችንን እንቀጥላለን።

ማስረጃ
1. የእስረኞች መያዝና ፍርድ "ያልታተመ ሰነድ " በብሄራዊ ቤተ መጻህፍት
2. በለጠ ገብሬ "በእድሜ ጎዳና ላይ የጉዞ ትዝታ" ገፅ 196- 201 ፣ ገፅ 211-220፣ 2004 ዓ.ም
Via Haileyesus Adamu
በላይ ዘለቀ ያስገደሉት የኦሮሞ ዝርያ ስላለውይሆን የሚል ጥርጣሪም ጫረብኝ። ከዚህ በፊት በላይ ዘለቀ የወሎ ኦሮሞ መሆኑ ምንጮች ጠቅሼ አቅርቤ ነበር!
Please wait, video is loading...