Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11590
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

በትግራይ የተደረገውን ጦርነት ተከትሎ በክልሉ የሚገኙ የጤና ተቋማት ተዘርፈዋል አልያም ሆን ተብሎ እንዲወድም ተደርጓል ሲል ዓለማቀፍ ድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን አስታወቀ DW Amharic

Post by sarcasm » 15 Mar 2021, 09:11

በትግራይ ክልል የተደረገውን ጦርነት ተከትሎ በክልሉ የሚገኙ የጤና ተቋማት ተዘርፈዋል አልያም ሆን ተብሎ እንዲወድም ተደርጓል ሲል ዓለማቀፍ ድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን (MSF) አስታወቀ።

ቡድኑ እንዳለው በክልሉ ከታህሳስ ወር ጀምሮ 106 የጤና ተቋማት ያሉበትን ሁኔታ ተመልክቷል። 70 በመቶ የሚሆኑ የጤና ተቋማት መዘረፋቸውን ያመለከተው የሀኪሞች ቡድኑ «30 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ሆን ተብለው እንዲወድሙ ተደርገዋል» ሲል ዛሬ ባወጣው መግለጫው አመልክቷል።

በየጤና ተቋማቱ የሚገኙ እና ከዘረፋ የቀሩ የህክምና አገልግሎት መስጭ ቁሳቁሶች ሆን ተብለው እንዲወድሙ መደረጉን ተመልክቷል። «በሮች እና መስኮቶች ተሰባብረዋል፤ መድኃኒቶች እና የታካሚዎች የህክምና መረጃዎች መሬት ላይ ተበትነዋል» ብሏል። «ሌሎች ክልሊኒኮች እና ሆስፒታሎች ደግሞ የሮኬት እና የላውንቸር ጥቃት ደርሶባቸዋል » ሲል ድንበር የለሽ የህክምና ቡድኑ አክሏል። የጀርመን ዜና ምንጭ ዲፒኤ እንደዘገበው የአቢ አዲ ሆስፒታል የመንግስት ወታደሮች ቁስለኞች ብቻ የሚታከሙበት መሆኑንን እና ለሌሎች ሲቪል ሰዎች አገልግሎት እንደማይሰጥ ቡድኑ ታዝቧል። በተጨማሪም በየህክምና ተቋማቱ የጤና ባለሞያዎች እና ሌሎች አጋዥ ሰራተኞች በነበረባቸው ስጋት አልያም ለረዥም ወራት ደሞዝ ባለማግኘታቸው በስራ ቦታ መገኘት አለመቻላቸውን አመልክቷል። ዩናይትድስቴትስ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰሞኑን እንዳስታወቁት በፌዴራል መንግስት እና በህወሓት ሃይሎች መካከል ግጭቶች መቀጠላቸውን የሚያመለክቱ ሪፖርቶች እየወጡ ነው።
Please wait, video is loading...