Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Wedi
Member+
Posts: 8649
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

በትግራይ ሀውዜን ነዋሪ የነበሩት መምህሩ በግፍ ተገደሉ!

Post by Wedi » 15 Mar 2021, 05:30

በትግራይ ሀውዜን ነዋሪ የነበሩት መምህሩ በግፍ ተገደሉ!

መምህሩ በግፍ ተገደሉ!

በሀውዜን ነዋሪ የነበሩት መ/ር ጠአመ በጁንታው በግፍ እንደተገደሉ ማረጋገጥ ተችሏል። በነዋሪው የሚታወቁት መ/ር ጠአመ ባለፈው ረቡዕ ጠላ ቤት እያሉ የጁንታው ታጣቂዎች ደርሰው ጎትተው በማውጣት እየደበደቡና እያንገላቱ ሲያወጧቸው "እባካችሁ አትግደሉኝ? እሰሩኝ?" እያሉ ቢማፀኑም ከጁንታው የጭካኔ ጥይት ድብደባ መትረፍ አልቻሉም። የሚያሳዝነው የጭካኔ ጥግ መምህር ጠአመን በጥይት ደብድበው ከገደሉ በኋላ ደማቸው ቀኑን ሙሉ እየፈሰሰ "ሬሳቸውን ማንም ሰው እንዳያነሳ፣ ማንም እንዳይቀብረው" በማለት "የአብይ ደጋፊ የሆነ እጣው ይህ ነው" ሲሉ ነዋሪውን ሰብስበው በፉከራ ማስፈራራታቸው ታውቋል። የመከላከያ ሰራዊት ከሰንቃጣ መጥቶ የመምህር ጠአመን ሬሳ በማንሳት እንዲቀበር ማድረጉን የከተማዋ ተወላጅ የሆኑ እማኞች በሀዘን ተናግረዋል። የጁንታው ጭካኔ "ከእኛ ጋ አልተሰለፋችሁም" በሚል በርካታ ወጣቶችን መግደል ቀጥሏል። ይህን አረመኒያዊ ድርጊት BBC ትግርኛም ሆነ የትግራይ ቲቪ እየዘገቡና እያጋለጡ አይደለም። የጁንታው ልሳን መሆናቸው በግልጽ እየታየ ነው! ለመ/ር ጠአመና እየተገደሉ ለሚገኙ ወጣቶች ማን ድምፅ ይሁንላቸው!?

#AT