Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11590
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

"ጠቅላይ ሚንስትር ዶር አብይ አህመድና መከላከያችን የካደው በአማራ ብልፅግና የተሰገሰጉ ቀማኛ ናቸው።" የኣቢይ activist ወልቀታይ መለስ ብስራት

Post by sarcasm » 05 Mar 2021, 21:51


ጠቅላይ ሚንስትር ዶር አብይ አህመድና መከላከያችን የካደው በአማራ ብልፅግና የተሰገሰጉ ቀማኛ ናቸው።


መንግስት ትግራይ ክልል ህግ ለማስከበር ግዴታውን በ17 ቀን ተውጥቷል። የቀረው የተበታተኑ የህወሓት ቅሬቶች መለቃቀም ነበር ይህም በተሳካ ሁኔታ እያካሄደ ነበር።
ነፃ የወጡ የትግራይ ክልል ከተማዎች የፌዴራል መንግስት ባዋቀረው ግዝያዊ አስተዳደር መሰረት የመጀመርያ ጉዞ ወደ ምዕራብ ትግራይ ከተማ ሑመራ የፌዴራል ፖሊስ ጋር በማያያዝ ተላኩ ባህርዳር ላይ አናሳልፍም ብለው ሰዓታት ገትርዋቸው በስተመጨረሻ ሽኩቻው ሲከር ተመለሱ ተብለው ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ።

ምክንያቱ ያቀረቡት የአማራ ብልፅግና የህወሓት ቅሬቶች ፀድተው አልፀዱም መጀመርያ እነሱን እናፅዳ ነበር።

መንግስት ይሁን የትግራይ ግዝያዊ አስተዳደር ትክክል ነው ብለው ታገሱ ግን ትዕግስት ብቻ ሁኖ ቀረ። ርስታችን ነው ብለው እርፍ!

ይባሱን ብለው ዘረፋ፣ ግድያ፣ ነዋሪውን ማፈናቀል የቀን ተቀን ስራቸው ሆነ ይህንንም ተግባር ለፀጥታ የተላከው የፌዴራል ፖሊስ የዓይን ምስክር ነው። ከአቅሙ በላይ ስለሆነበት ማስቆም አልቻለም እያንዳንዱ ዘረፋ፣ ግድያ፣ አፈና ግን በእግዚቢት መዝግቧል። የግዜ ጉዳይ እንጂ ወንጀለኛ በህግ ይጠየቃልም ብለዋል በቅርቡ ጠቅላይ ሚንስትር ዶር አብይ አህመድ ስለ ምዕራብ ትግራይ የተፈፀመ ያለው መረን የለቀቀ ግፍ ሲጠየቁ።
መንግስትም መከላከያችንም የትግራይ ህዝብም ክህደት ተፈፀመባቸው።
Please wait, video is loading...