አማንሚካኤል
የራሱ ህዝብ በሌላ ሃገር ወታደር እየተገደለ እየተዘረፈ እየሰማ ማውገዝ ሲገባው ርካሽ ተወዳጅነት ለማግኘት ከግፈኛው የውጩ ሃይል ጋር የሚያሽቋልጥ ታይቶም ተሰምቶም አያቅም።
የሻዕብያ ወታደር ጁንታው ለማጥፋት መዋጋቱ ብዙም ቅሬታ የለብኝም። የኔ ቅሬታ ንፁሃን ዜጎች ስለገደለ ነው፣ንብረት ስለዘረፈ ነው።
ላጠፋው ጥፋት መኮነኔ እና ማጋለጤ ግን ይቀጥላል። የትግራይ ህዝብ ኢትዮጵያዊ ነው በኤርትራ ወታደር ግፍ ሲደርስበት ካላመመን ጥላቻችን ከህዝቡ ጋር ነው ማለት ነው። ከትግራይ ህዝብ ይልቅ የኤርትራ ወታደር ከቀረበህ በግልፅ እንነጋገር ባንዳነህ።
የሻዕብያ ወታደር ለህዝቡ ያልሆነ ለገዛ ወገኑ ኩላሊት እያወጣ ለባእድ የሚሸጥ ወታደር በፍፁም ለኢትዮጵያ ህዝብ ይራራል ብዬ አልጠብቅም።የሻዕብያ ወታደር በንፁሃን የፈፀመው በደል ለኢትዮጵያ መንግስትም ትልቅ ፖለቲካዊ እና ታሪካዊ ኪሳራ አክስሮታል።
የሻዕብያ ወታደር የጁንታ ታጣቂ ጋር ተፋልሞ ከጨረሰ ቦሃላ ቀጥ ብሎ ቢወጣ እኔም አልቃወምም። አሁን ያደረገው ድርጊት ግን ምንም የማያቀው ህዝቡን ነው የገደለው።ይሄ የሻዕብያ ወታደር ዛሬ ድረስ ትግራይ ላይ ግፍ እየሰራ ይገኛል። ለዚህ የማይጮህ ሰው የትግራይ ህዝብ ጠላት የኢትዮጵያ ክብር የማያቅ ብቻ ነው።
ትላንት የለጠፍኩት ፎቶ ላይ ሃሳቤ ይገልፅልኛል ያልኩት ፎቶ ነው የተጠቀምኩት እንጂ ትግራይ ላይ ነው አላልኩም።
ፍረጃ ፣መንጋ አልፈራም ድጅታል ወያነም ሲፈርጀኝ ቦታ አልሰጠውም ስንት ነገር አልፌ የመጣሁ ሰው ነኝ። ለሃቅ ዛሬም እሞታለሁ። ሰሜን እዝ የደረሰው ጥቃት አምርሬ የተቃወምኩት ለእውነት ስለምኖር እንጂ በሰፈር የማስብ ሰው ብሆን የሰፈሬ ሰዎች ምን ወያሉ እንዳሉ እያያቹህ ነው። የመንጋነት አስተሳሰብ በጣሜም የምኮንን ሰው ነኝ። ሃቅካለኝ ብቻዬም ብሆን እታገላለሁ። ሰው ስላበደ ፣ስለዋሸ እውነት ደብቆ ስለኖረ እሱን ለመመሰል አልጥርም።
የውጪ ሃይል ህዝቤን በግፍ እየገደለ ነው ማለቴ ጁንታ ነህ አላቹህ በየትኛው ሞራላቹህ ነው የምትፈርጁት። ሃገርህ በውጪ ተደፍራ ያገርህ ሰው እየገደለ ዝም ያልከውስ ምን ስም ሊወጣልህ ነው? እኔ በማስበው ካላሰብክ አንተ እንዲህ ብሎ መፈረጅ የጁንታ ህወሓት ደንበኛ መገለጫው ነበር። የምትፈርጁ ሰዎች የጁንታው ተፅእኖ ያላቹህ ይመስለኛል። አሁን መሰራት ያለበት የጁንታ አስተሳሰብ አውቀውትም ሳያቁትም የተለከፉ ሰዎች ልክ ልካቸው ነግረን ወደ እውነት እና ትክክለኛው ኢትዮጵያዊ ባህሪ መመለስ ነው።
የሃገሬ ህዝብ በባእድ ሃይል እየተጠፈጨፈ ዝም ማለት አልችልም አባቶቼ እንደዚህ አላስተማሩኝም። ኢትዮጵያ በማንም ያልተገዛችው አባቶቻችን ለከብራቸው ስለወደቁ ነው።
በኢትዮጵያዊነቱ የሚይደራደር የትግራይ ህዝብ በውጪ ሃይል እየተገደለ ንብረቱ እየተዘረፈ ኢትዮጵያውያን ዝም ልንል አይገባም ብያንስ ድርጊቱ ማውገዝ ይገባል።
https://www.facebook.com/emacool.mesfin ... 8803662416