የኢዜማ አባሉ ተገደሉ
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የቢሾፍቱ ከተማ የአድአ ምርጫ ወረዳ 1 ሊቀመንበር የነበሩት ግርማ ሞገስ ለገሰ ትላንት እሑድ የካቲት 7 ቀን 2013 ዓ.ም ምሽት በተተኮሰባቸው ጥይት ሕይወታቸው ማለፉን ኢዜማ አስታወቀ፡፡ ኢዜማ በክስተቱ የፓርቲው አባላት እና አመራሮች ከፍተኛ ሐዘን እንደተሰማቸው ገልጾአል።
ኢዜማ በአባሉ ላይ የተፈፀመውን የግድያ ወንጀል በፅኑ የሚያወግዝ ሲሆን ተጨማሪ መረጃዎችን ሰብስበን እንደጨረስን ዝርዝር ጋዜጣዊ መግለጫ የምንሰጥ መሆኑን እናሳውቃለን ብሏል፡፡
ፓርቲው በመጨረሻም ለግርማ ሞገስ ቤተሰቦች፣ ወዳጆች እና የትግል አጋሮች ልባዊ መጽናናትን እንደሚመኝ ገልጾአል፡፡
