ሀገር ማለት
ከሌላው ቆርስህ የምታስፋው:
ተሳሳትኩ ብለህ የምትፅፈው:
መሪሁነህ የምትዘርፈው::
አይደለም ስማኝ ልንገርህ
ህዝብ ማለት
የምትሞትለት ዘርክን ቆጥረህ
የምታኖረው ሌላውን ገድለህ
የምትቸረው ከአንዱ ስርቀህ
የምታለማው ሌላ አድርቀህ
አይደለም
ምታበዛው ሌላ አምክነህ
ምትመግበው ሌላ አስርበህ
አይደለም
ሀገር ማለት
እንዲሁ ዝም ብሎ መሬት ማለተም አይደለም
ከማንነትም ከመሬት ይሰፋል
ከቋንቋ ከዘርም ያልፋል
ከዘር ከቀለም ከደምምይተርፋል
ተወለደው ያደጉበት
ልጅ ሆነው ተረትተረት የሰሙበ
እዚያ ማዶ እዚህ ማዶ የተጫወቱበ
ሰው ሆነው የንሩበት
ጎልምሰው ያገቡበት
ሰርተው እንጀራ ያገኙበት
የራስን ባህል ከሌላው ያጋሩበት
ስለሀገር ተዋግተው የሙቱበት
ድልንም ሽንፈትንም የቀመሱበት
ኑረው ኑረው ያለፉበት
ይሄሁሉ የሆነበት ብቻም አይደለም
እንዲህ አይሆንክ አየኖርክ
ሁሉንም እየከወንክ ሌላ ሀገር ይታይሀል
ከዚህ ያልፋ ይተርፋል
ሀገር ማልት እንዲሁ ዝም ብሎ መሬት አይደለም
ወንዙ ሸለቆው ተራራውም ህዝቡም ብቻ አይደለም
ብህዝብ መሀል ሆነህ ሌላ ሰው ይናፍቅሀል
በምቾት ሆነህ ችግር ያየህበትተቋርሰህ የበላህበት ውል ይልሀል
ሀገር ማለት ውስብስብ ነው
ላንዳንዱ የማይገባው
የተጋመደበት ገመዱ
የተያያዘበት ዘመዱ
የማይታየው::
የምትኖር ሲኖር እርሱ
የምትፈርስ ሲፈርስ እሱ
ለሌላው
ምስጢሯ ጥልቅ
የማትፈታ ሰምና ወርቅ
በደስታውም በሀዘኑም
በሰርግ በለቅሶውም
በድሎትም በችግርም
እየሞተም እየገደሉትም
ዘር ድንበር ሳይገድበው
ሀገር ብሎ የሚያላዝን
በሞቱ በችግሩ የማያዝን
ሁሌም ስለርሷ የሚሰዋ
ሀገር ማለት
ቀጥሉበት. ..