Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
-
Revelations
- Senior Member+
- Posts: 34573
- Joined: 06 Jan 2007, 15:44
Post
by Revelations » 13 Feb 2021, 07:31
የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ህንፃ ወደሆስፒታል ተቀየረ!
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተገነባው በሀገራችን የመጀመሪያው ትልቁና ዘመናዊ የእናቶችና ህፃናት ሆስፒታል ተጠናቀቀ ።
በ20 ሺ ካሬ ላይ ያረፈው ፣ 400 በላይ ተኝቶ መታከሚያ አልጋዎች ያሉት፣100 የልህቀት ማዕከል አገልግሎት መስጫ ክፍሎች፣በተመሳሳይ ሰአት ለ7 እናቶች የኦፕራሲዮን አገልግሎት መስጠት የሚያስችለው ዘመናዊና ወረቀት አልባ መስተንግዶ የሚሰጠው ይህ ሆስፒታል ዘመናዊ የህክምና ቁሳቁሶች ተሟልተውለታል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጤናው ዘርፍ በተለይ በወሊድ እና ተያያዥ ጉዳዮች በእናቶች እና ህጻናት የሚደርሰውን የሞት ምጣኔ ለመቀነስ በአይነቱ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነና ደረጃውን የጠበቀ የእናቶች እና ህጻናት ሆስፒታል ግንባታ ያጠናቀቀ ሲሆን በክብርት ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የካቲት 4 ቀን 2013 ዓ.ም ተመርቆ ስራ የሚጀምር ይሆናል።
ግንባታው ቀድሞ ለመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ተብሎ የተጀመረ ሲሆን የከተማ አስተዳደሩም ካቢኔ በከተማችን ትልቅ የአገልግሎት ችግር ያለበትን የእናቶችና ህጻናት ጤና ቅድሚያ በመስጠት ሰባት መቶ ሚሊየን ብር በመመደብ ተጨማሪ ግንባታ በማድረግ እና ነባሩን ግንባታ በማሻሻል ወደ ሆስፒታልነት እንዲቀየር አድርጓል ።(አ/አ ኘረስ ሴክሬቴሪያት)

-
Ethoash
- Senior Member+
- Posts: 26144
- Joined: 20 Apr 2013, 20:24
Post
by Ethoash » 13 Feb 2021, 08:32
AbebechGobena
በጣም የሚያስቅ ስም ነው። እውነትም ጎበና ።
ነገ ደግሞ አባይ የስራው ሁሉ ተቀይሮ ፣ አዲስ ስም ተስጥቶት እናያለን የግዜ ብቻ ነው። አሁን ይህችን ጎበና ማክበር ከፈለግን ለምን የተነካካ ቤት እንስጣታለን ለምን አዲስ ህንፃ አንስራላትም ። ኢትዬዽያ በጣም የአስተዳደር ችግር ያለባት ሐገር ናት ባይሆን የትምህርት አስጣጡን አሻሽሎ ከአሜሪካ ወይ ከእንግሊዝ የአስተዳደር ዘይቤ ተቀድቶ ትልቅ አገርን ማስተዳደር የሚችሉ ልጆችን ብናፈራበት ምኑ ነው ጥፋቱ ። ይህ የናቶች ሆስፒታ የተስራው እኮ በአስተዳደር ት ህዛዝ ነው ። መጥፎ አስተዳደር ደግሞ ቂም በቀልን ያስተምራል አንዱ የስራውን ሌላው በማፈረስ። እኔ እያልኩ ያለሁት መለስ የመንጌ ስራ አላፈረስም እያልኩ አይደለም ይህ ማፍረስ ስራ ይቁም እያልኩ ነው።
መለስ አንዴ ሞቅ ሲለው አስመራ መንገድ የሚለውን ዋና መንገድ ሐይሌ ገ፣ስላሴ ብሎ ስየመው ። ታድያ አሁን ስንታረቅ የአስመራ መንገድ ስሙ እንደገና ይስየማል ወይ ። ምን ሊኮን ነው መንገዱ ወድ አስመራ ነው የሚያመራው ምን ብለን ልንስይመው ነው ወይስ ሐይሌን በቃህ ስሙን ለቀቅ አርገው በኤርትራ መንገድ ልንስይመው ነው ልንለው ነው ወይ።
-
Revelations
- Senior Member+
- Posts: 34573
- Joined: 06 Jan 2007, 15:44
Post
by Revelations » 13 Feb 2021, 14:57
አይዞህ! ያለፈው አይመለስምና ጠንከር በል::
Ethoash wrote: ↑13 Feb 2021, 08:32
AbebechGobena
በጣም የሚያስቅ ስም ነው። እውነትም ጎበና ።
ነገ ደግሞ አባይ የስራው ሁሉ ተቀይሮ ፣ አዲስ ስም ተስጥቶት እናያለን የግዜ ብቻ ነው። አሁን ይህችን ጎበና ማክበር ከፈለግን ለምን የተነካካ ቤት እንስጣታለን ለምን አዲስ ህንፃ አንስራላትም ። ኢትዬዽያ በጣም የአስተዳደር ችግር ያለባት ሐገር ናት ባይሆን የትምህርት አስጣጡን አሻሽሎ ከአሜሪካ ወይ ከእንግሊዝ የአስተዳደር ዘይቤ ተቀድቶ ትልቅ አገርን ማስተዳደር የሚችሉ ልጆችን ብናፈራበት ምኑ ነው ጥፋቱ ። ይህ የናቶች ሆስፒታ የተስራው እኮ በአስተዳደር ት ህዛዝ ነው ። መጥፎ አስተዳደር ደግሞ ቂም በቀልን ያስተምራል አንዱ የስራውን ሌላው በማፈረስ። እኔ እያልኩ ያለሁት መለስ የመንጌ ስራ አላፈረስም እያልኩ አይደለም ይህ ማፍረስ ስራ ይቁም እያልኩ ነው።
መለስ አንዴ ሞቅ ሲለው አስመራ መንገድ የሚለውን ዋና መንገድ ሐይሌ ገ፣ስላሴ ብሎ ስየመው ። ታድያ አሁን ስንታረቅ የአስመራ መንገድ ስሙ እንደገና ይስየማል ወይ ። ምን ሊኮን ነው መንገዱ ወድ አስመራ ነው የሚያመራው ምን ብለን ልንስይመው ነው ወይስ ሐይሌን በቃህ ስሙን ለቀቅ አርገው በኤርትራ መንገድ ልንስይመው ነው ልንለው ነው ወይ።
-
Weyane.is.dead
- Member+
- Posts: 6796
- Joined: 19 Oct 2017, 11:19
Post
by Weyane.is.dead » 13 Feb 2021, 16:40
Great move. The west's servant will be turning in his grave. The imperialist bast.ards lost all their eggs with the midget.