Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

Horus
Senior Member+
Posts: 42469
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: NASA approves the energy-time uncertainty relation prove quantization of timeby ትግራዋይ scientist!!!!!

Post by Horus » 09 Feb 2021, 02:37

Dawi,

የዛሬ ስንት አመት ቨርነር ሃይዘንበርግ ዘ ፕሪንሲፕል ኦፍ አንሰርተንቲ በሚለው የፊዚክስ ህግ የደመደመው የማተር ፓርቲክልነትና የዌቭነት ህግ ተቀጥያ ነው ። እስፔስ ታይም ከዚህ ሕግ ጋር እንደ ሚተሳሰር ይታውቅ ነበር ። ግን ችግሩ ግዜን እንደ ጠጠር መቁጠሪያ ማቲማቲካል ሞዴል ወይም አርቲፋክት የሚፈለስፉ ሰዎች ነበር የሚጠብቀው ።
ይሀውልህ! ለምሳሌ ሃሳብ በፊዚክስ ሆነ በኒውሮሎጂ ፊዚካል ነገር እንደ ሆነ ሁሉ ያውቃል፣ ግን ሃሳብን በሂሳብ ማስላት መደመርና መቀነሻ ዜዴ ገና አልተገኘም ። ይህም ልክ እንድዚያ ነው። ሂሳብ ቋንቋ ነው። ልክ ለሺ ዘመን በቃል ይነገር የነበረውን አፈ ታሪክ የፊደል ሞዴል ፈልስፎ በጽሁፍ መሰውሰውና መፍተል ማለት ነው ። ግዜ የፊልድም የፓርቲክልነትም ባህሪ እንደላው ድሮም ይጠረጠር ነበር ፣ ግን ኳንተም ሪያሊቲ ስለሆነ (ስለማይታይና ስለማይዳሰስ) አሁን ያለው ያይምሮ ሚታፎር ሊገነዘበው ስላልቻለ እንጂ ጥያቄው አይናችን ስር ያለው ሪያሊቲ ነበር ። ልጁ ጎበዝ ነው ይህን ሃይፖቲሲስ ማቅረቡ ። አው ግዜ ተዘርዝሮ የሚለካ ሪያሊቲ ነው ልክ እንደ ስንዴና ሽሮ !!!


በእኔ ግምት ኢንሳይቱን ያገኘው ከኢትዮጵያ የግዜ አጠቃቀም ካልቸር ይመስለኛል ። ለምሳሌ በምዕራባዊያን የቋንቋ ሚታፎር " የግዜ መቁጠሪያ" ወይም "የዘመን መቁጠሪያ" የሚባል ሜታፎር የላቸውም ። በኢትዮጵያ አይምሮ ግዜ ይቆጠራል። ግዜ ይለካል ። ይህን ይዞ ማቲማቲካል ሞዴል መፍጠሩ ውብ ነው ። ትንሽ የቋንቋ እውቀት ቢጠይቅም !! እሱ እንዴት ወደ ሃይፕቲሲሱ እንደ ደረሰ ባላውቅም ማለት ነው?!!! አበሻ የግዜ መቁጠሪያ ይላል ! እንዴት ነው ግዜ ሚቆጠረው !?? አበሻን መናቅ ትልቅ የኢንተለጀንስ ዉድቀት ነው !

Post Reply