Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11588
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

ዶ/ር ዐብይ ምን ማድረግ ነበረበት? በኣብርሃ ደስታ

Post by sarcasm » 07 Feb 2021, 12:42

ዶር ዐብይ ምን ማድረግ ነበረበት?

14 September 2020


============
ትግራይ ክልል በተናጠል ምርጫ አካሂዳለች። ይህ ድርጊት ከሀገር ኢትዮጵያ ግዛታዊ አንድነት አንፃር አደገኛ ነው። ምክንያቱም አሁን በአንድ ሀገር ውስጥ ሁለት ምርጫ፣ ሁለት ምርጫ ቦርድ፣ ሁለት ወታደር፣ ሁለት ግዛት፣ ሁለት ንጉስ አለ ማለት ነው። በአንድ ጫካ ውስጥ ሁለት ሸፍታ መኖር ይችላሉን?
ለዚሁ ጉዳይ የህወሓት ስርዓት ግትርነት አስተዋፅኦ ቢያደርግም በማንም አካል ይፈፀም የሀገር አንድነት አደጋ ላይ የሚጥል ድርጊት ሲከሰት ሐላፊነቱ የማእከላይ መንግስት ነው። አሁን ለተከሰተው ችግር በአመዛኙ የፌደራል መንግስትን እወቅሳለሁ። እንዴት?

የፌደራል መንግስትን በተቸሁበት ግዜ፡ አንድ የብልፅግና ፓርቲ አመራር አባል "ዶር ዐብይ ምን ማድረግ ነበረበት? እስኪ ንገረኝ! ህወሓት ኮ ነው የሸፈተው!?" ብሎኛል።

የህወሓት ጥፋት በሌላ ፅሑፍ እመለስበታለሁ። አሁን ግን የትግራይ ክልል የተናጠል ምርጫ ለማስቀረት ዶር ዐብይ ምን ማድረግ እንደነበረበት ልናገር!
አምስት ነጥቦች

(1) መንግስት መሆን

ያኔ መጀመርያ ዶር ዐብይ አሕመድ ስልጣን እንደያዘ ከሁሉም የኢትዮጵያ አከባቢዎች አንፃራዊ ድጋፍ ነበረው። ያኔ "ሪፎርም" የማካሄድ ዕቅድ ከነበረው ወድያው "መንግስት ለመሆን" ጥረት ማድረግ ነበረበት።
"መንግስት መሆን" ምንድነው?
በሁሉም የኢትዮጵያ አከባቢዎች መንግስታዊ መዋቅር በመዘርጋት Effective Government Control እንዲኖር በማስቻል ከመንግስት ቁጥጥር ውጭ የሆነ አከባቢ እንዳይኖር ማረጋገጥ ነበረበት። ይህ መጀመርያ አከባቢ አብዛኛው ህዝብ ተስፈኛና ደጋፊ በነበረበት ግዜ ይቻል ነበር። ዶር ዐብይ የትግራይ ህዝብም ድጋፍ ጭምር ነበረው።

ቁጥጥር ማኖር በራሱ በቂ አይደለም። ሀገሪቱን ከመቆጣጠር ቀጥሎ የህዝብ "እምነት" ማግኘት ወሳኝ ነው። የህዝብ እምነት ለማግኘት ህዝብን ማገልገል አለበት። ህዝብ ለማገልገል ያለምንም (ብሄር ወይ ቋንቋ ወይ ሀይማኖት ወይ ዝምድና ወይ ሌላ) አድልዎ በእኩል ዓይን ማገልገል የሚችሉ መንግስታዊ ተቋማት መገንባት!
ህዝብ በፀጥታ አካላት ላይ እምነት ካሳደረ የራሱን ደሕንነት በራሱ ለመጠበቅ መሳርያ አይገዛም ነበር፤ በየግዜው "ሕገ ወጥ የመሳርያ ዝውውር" እየተባለ ዜና ባልተሰራ ነበር። ዜጎች ወይ ድርጅቶች "የደሕንነቴ ዋስትና መንግስት ነው። የመንግስት የፀጥታ አካላት ይጠቡቁኛል" ብሎ ቢያምን ኖሮ አርሶአደሮች በሬያቸው እየሸጡ ጠመንጃ ባልገዙ ነበር፤ ህወሓትም (በፌደራሉ መንግስት እምነት ቢኖራት ኖሮ) መሳርያ ባልታጠቀች ነበር። ባትታጠቅ ኖሮ በተናጠል ምርጫ ለማድረግ ባልወሰነች ነበር።
ስለዚህ ለሁሉም ዜጋና ድርጅት የፀጥታና የደሕንነት መንግስታዊ ዋስትና በመስጠት ዜጎች ይሁኑ የፖለቲካ ድርጅቶች እንዳይሸፍቱና ለሀገር አንድነት ስጋት እንዳይሆኑ ማድረግ ይቻል ነበር።

መንግስት በሁለት ዓመት የሪፎርም ግዜው በመንግስታዊ ተቋማት ግንባታ ላይ ማተኮር ይገባው ነበር። የተለያየ የፖለቲካ አመለካከት ያላቸው ሐይሎች የሚተማመኑበት መንግስታዊ የፍትሕ ተቋም ያስፈልግ ነበር። የፖለቲካ ልዩነት ከRuling party ጋር እንጂ ከመንግስት ጋር መሆን አልነበረበትም። በኢትዮጵያ ብዙ ችግር የሚፈጠረው የተለያየ አመለካከት ስላለን ሳይሆን የተለያየ አመለካከታችን የምንናንፀባርቅበት ሜዳ (መንግስታዊ ተቋም) ስለሌለን ነው።
አንድ ግለሰብ ወይ ድርጅት ከገዚው ፓርቲ ጋር በሐሳብ ቢለያይ (ቢጣላ) እንኳ ሕግ እስካልጣሰ ድረስ እንደማይታሰር ወይ ችግር እንደማይደርስበት እርግጠኛ የሚሆንበት የሚተማመንበት የፍትሕ ተቋም መኖር አለበት።

"አንድ ባለስልጣን ሊያስረኝ ቢሞክር እንኳን ሕግ እስካልጣስኩ ድረስ ፖሊስ አያስረኝም፤ ፖሊስ አለአግባብ ቢያስረኝ እንኳ ንፅህናየን አይቶ ፍርድቤት በነፃ ይለቀኛል" ብሎ የሚተማመንበት ተቋም መገንባት ቢቻል ኖሮ ሽፍትነት አይኖርም ነበር።
ህወሓቶች የራሳቸው ወታደር በማሰልጠን የፌደራል መንግስትን ትእዛዝ ባለመቀበል በራሳቸው አቅም በተናጠል ምርጫ ለማካሄድ የወሰኑበት ዋና ምክንያት በፍትሕ ተቋሙ እምነት ስለሌላቸው ነው፤ ዝም ካሉ ዋስትና የላቸውም። ለዚህ ነው በሕግ ሳይሆን በቅልጥማቸው መተማመን የጀመሩት። እናም ሁሉም የሚተማመንበት የፍትሕ ስርዓት በመገንባት የህወሓትን ግትርነት ማስቀረት ይቻል ነበር፤ የተናጠል ምርጫውም እንዲሁ።
ይሄ ሁሉ ቀላል አይደለም። ግን አስፈላጊ ነው። አስፈላጊ ሆኖ ቀላል ካልሆነ ሌሎች እንዲያግዙህ መጋበዝ ነው!

(2) የተሻለ መሆን

ለውጡ እንደተጀመረ ሁሉም ያለአድልዎ ከባለፈው የተሻለ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በእኩልነትና በነፃነት የሚኖርበት ስርዓት መገንባት አስፈላጊ ነው። ለምሳሌ በለውጥ ሂደት በግልፅ የተቀመጠ ሁሉም የተስማማበት የሽግግር ፍትሕ (Transitional Justice) ስርዓት መኖር ነበረበት።

ህወሓትን ጨምሮ ብዙ የትግራይ ልጆች "ሁሉም የኢህአዴግ ባለስልጣናት ባጠፋት የትግራይ ተወላጆች የሆኑ የህወሓት ሰዎች በብሄራቸው ምክንያት ተለይተው ዒላማ ተደርገው ታስረዋል" የሚል እምነት ነበራቸው።

የሽግግር ፍትሑ (Transitional Justice) ግልፅ መሆን ነበረበት፤ ስርዓት አልነበረውም። የሽግግር ፍትሕ ስርዓት ነበረን ወይ? ምንድነው የሚለው? እንደ ሕግ ለሁሉም የሚሰራ ነው ወይ የተወሰኑ ሰዎች ዒላማ ያደረገ? ሁሉም ያጠፉ የቀድሞ ባለስልጣናት ይታሰሩ? ወይስ የተወሰኑ ብቻ? በምን መስፈርት? ባጠፉት ጥፋት መጠን? በፖለቲካ አመለካከታቸው? ወይስ በብሄራቸው? ግልፅ የሆነ የሽግግር ፍትሕ ስርዓት አላየሁም። ወይም አልተነገረንም።

ይህም በትግራይ ተወላጆች ላይ ጥርጣሬ ፈጥሯል። "ከህወሓት መሸነፍ በኋላ በብሄራችን ምክንያት እየተጠቃን ነው። አሁን ስልጣን የተረከበ አካል ፀረ ተጋሩ ነው። ሊያጠፋን ይችላል። ከህወሓት የባሰ ነው። ህወሓትን አጥፍቶ እኛን እንደ ብሄር ሊያጠፋን ስለሚችል አንድ ላይ መሰባሰብ አለብን። ህወሓትን መደገፍ አለብን" በሚል ብዙ የትግራይ ተወላጆች ህወሓት ወደ መደገፍ ገብተዋል። አሰራሩ ግልፅነት ስላልነበረው።

ህወሓትም ይሄንን የተጋሩ ግዝያዊ ድጋፍ ተጠቅሞ ለብቻው ማሳብ ጀመረ። በድጋፉ የልብልብ ተሰምቶት ምርጫን በተናጠል እስከማካሄድ ደረሰ። የተጋሩ ድጋፍ ባያገኝ ኖሮ ምርጫ ለማድረግ ይቅር በስልጣን የመቆየት ዕድልም አልነበረውም። የእስር ሂደቱ ግልፅነት ቢኖረው ኖሮ ተጋሩ ህወሓትን አይደግፉም ነበር። ባይደግፉ ምርጫ ለማድረግ አይነሳሳም ነበር።

የሪፎርም መንግስቱ ባጠቃላይ ካለፈው ስርዓት በተግባር የተሻለ መሆን ነበረበት። በፍትሕ፣ በፀጥታ እና በዴሞክራሲ ጉዳዮች ላይ ከባለፈው የህወሓት መንግስት የተሻለ መሆን ስላቃተው ህዝብ የኢህአዴግን በደል እንዲረሳ ሆኗል። እስሩ፣ ሞቱ፣ መፈናቀሉ ወዘተ ህዝብን ግራ አጋብቷል። በዚህ ምክንያት ተቃውሞዎች ስላየሉ የፌደራል መንግስት የትግራይን ጉዳይ ትቶ በሌሎች ጉዳዮች በመጠመዱ ህወሓት ምርጫው ለማካሄድ ግዜና ዕድል አግኝቷል።

(3) መወሃድ ወይ መተው

የኢህአዴግ መንግስት በህዝባዊ ዓመፅ ከተነቃነቀ በኋላ "ሪፎርም አካሂዳለሁ" በሚል መንግስት ሲተካ የፓርቲውን ዕድሜ ለማራዘም ሲባል በአዲስ ሐሳብ በአዲስ መንፈስ ለመነሳሳት የውህደት ሐሳብ ይዞ መጣ። በመርህ ደረጃ መዋሃድ አስፈላጊ ነው። ከህዝባዊ ዓመፁ በኋላ ኢህአዴግ በአዲስ መልክ ስራ መጀመር ስለነበረበት ለመወሃድ ማቀዱ ትክክል ነበር።

ውህደት አስፈላጊ ነው፤ ለአንድ ሀገር አንድነትና የህዝብ ደሕንነት! ግን ኢህአዴግን ለማዋሃድ ሁሉም ኢህአዴጎች ሊቀበሉት ይገባል። ሁሉም እንዲቀበለው ደግሞ የውህደትን አስፈላጊነት በመተንተን ማሳመን ይጠበቃል። ማሳመን ካልተቻለ ውህደት አይኖርም።

በውህደት ሂደቱ የኢህአዴግ ድርጅት መስራችና መሪ የነበረው ህወሓት አልተስማማም። በህወሓት እምነት ኢህአዴግ ሳይወሃድ እስከ ምርጫ ድረስ እንደነበረው በግንባር ደረጃ መቆየት ነበረበት። ስለዚህ አንድ የኢህአዴግ ዋና አካል ያልተስማማበት የኢህአዴግ ውህደት ሊኖር አይችልም።

በዚህ ጉዳይ ዶር ዐብይ ውህደቱን ከፈለገ ማድረግ የነበረበት ነገር (1) ህወሓትን (በድርድርም ቢሆን) ማሳመን ነው። (2) ህወሓትን ማሳመን ካልቻለ ውህደቱን መተው ነው። አሁን ችግሩ ህወሓትን አሳምነው ኢህአዴግን ማዋሃድ አልቻሉ፤ ውህደቱን ትተው ግንባሩን ማቆየት አልቻሉ።

ኢህአዴግ ቢወሃድ ጥሩ ይሆን ነበር። ሁሉም ነገር አብረው ስለሚወስኑ በትግራይ ክልልና በፌደራል መንግስት መካከል ውጥረት ነግሶ ህወሓትም በተናጠል ምርጫ አካሂዳ የሀገር አንድነት አደጋ ላይ ባልወደቀ ነበር።

ዶር ዐብይ ህወሓትን አሳምነው ኢህአዴግን ማዋሃድ ካልቻለ የውህደት ሐሳቡን ትቶ ኢህአዴጎች እንደነበሩበት በግንባር ደረጃ አብረው እንዲቀጥሉ ማድረግ ነበረበት። በግንባር ቢቀጥሉ ቢያንስ በእንደ ምርጫ ያሉ ሀገራዊ ጉዳዮች በተናጠል ሳይሆን አብሮነት ይወስኑ ነበር። በዴሞክራሲያዊ ማእከላዊነት መርህ መሠረትም የተለያዩ ሐሳቦች አይንፀባረቁም ነበር። ስለዚህ የተናጠል ምርጫ አይኖርም ነበር።

አሁን የሆነው ግን... ኢህአዴግ አልተወሐደም፤ በግንባር ደረጃም አልቆየም። ኢህአዴግ ግንባሩን አፍርሶ ሳይወሃድ ለሁለት ተከፍሎ "ብልፅግናና ህወሓት" ሆኗል።
ኢህአዴግ ሳይወሐድ ግንባርም ሳይኖረው ለሁለት መከፈሉ ሁለቱም የኢህአዴግ ድርጅቶች ለየብቻ እንዲያስቡና በተናጠል እንዲወስኑ አድርጎ አንድ ሀገር ሁለት ባላንጣ መንግስታትን ፈጥሯል።

(4) ድርድር ማካሄድ


በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት 6ኛው ሀገራዊው ምርጫ በግዜው ማከናወን እንደማይችል የምርጫ ቦርድ ሲያሳውቅ ምን ማድረግ እንዳለብን ለመወሰን ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት እውነተኛ ውይይትና ድርድር መደረግ ነበረበት።

ምርጫችን በወረርሽኝ ምክንያት ቢራዘምም የሀገራችን የፖለቲካ ችግር ከምርጫ መራዘም በላይ መሆኑ ሁላችን እንገነዘባለን። መንግስት የውይይትና የድርድር በር ዘግቶ በተናጠል ወስኖ ወደ ሕገ መንግስት ትርጉም መጠየቅ መጣደፉ በሁለት ዓመታት ግዜ ውስጥ ከተሰሩ ስሕተቶች ዋነኛው ነው።
መንግስታዊ ተቋማትና መዋቅር ባልተዘረጉበት ሀገር ሁሉም የፖለቲካ ችግሮች በሕግ አግባብ አይፈቱም። ሁሉም ነገር በሕግ የሚፈታ ቢሆን ኖሮ በፌደሬሽን ምክርቤት "ሕገ ወጥ" የተባለውን የትግራይ ምርጫ እንዴት ማስቆም አልተቻለም? ፖለቲካው ባልተስተካከለበት ሀገር ሁሉም ችግር በሕግ አይፈታም።
ስለዚህ መንግስት ወደ ሕግ ከመሮጡ በፊት ፖለቲካውን ማስተካከል ይቻል ዘንድ ወደ ውይይትና ድርድር መግባት ነበረበት። የምርጫው ጉዳይ በውይይትና ድርድር በስምምነት መወሰን ይቻል ነበር። ህወሓትም በግዜው በድርድር እንፍታው ብላ ነበር። ስለዚህ ችግሩ በሕግ አግባብ ሳይሆን በፖለቲካ ድርድር ቢፈታ ኖሮ የሀገር አንድነት አደጋ ላይ የሚጥል የትግራይ የተናጠል ምርጫ ባልተካሄደ ነበር።

የፖለቲካ ድርድር ማካሄድ ሕገ ወጥ አይደለም። ያኔ እንደተባላው የፖለቲካ ድርድር "ሕገ ወጥ" ቢሆን አሁን ታድያ የፖለቲካ ውይይት ለምን ተጀመረ? ባጭሩ ችግሩ በድርድር አለመፈታቱ ለትግራይ ምርጫ እና ለኦሮምያ ብጥብጥ ዳርጎናል።

(5) ምርጫውን መቀበል

እንደምንም ተደራድሮ የተናጠል ምርጫውን ማስቀረት የማይቻል ከሆነ ያለው የተሻለ አማራጭ ምርጫውን መቀበል ነው። ዶር ዐብይ ምርጫውን ማስቀረት እንደማይችል እያወቀ "የጨረባ ምርጫ የሚደረግ ከሆነ የሐይል እርምጃ ለመውሰድ እንገደዳለን" ብሎ ማስፈራራት አልነበረበትም፤ የትግራይ ህዝብ በእልኽ ምርጫውን እንዲደግፍ ምክንያት ሆኗል።

በምርጫው ዋዜማም "የጨረቃ ምርጫ ነው" ብሎ መናገር ጉዳት እንጂ ጥቅም የለውም። ህዝብ ለመምረጥ ተመዝግቦ፣ ቅስቀሳ ተካሂዶ፣ የምርጫ ቁሳቁስ ተዘጋጅቶ በተሰራጨበት ግዜ መቀበል ወይም ዝም ማለት ነበረበት።

አሁን መደረግ ያለበት፥ ነገሮችን ወደ ግጭት እንዳያመሩ ማለዘብ!
ሰላም ለሀገራችን!
14 September 2020

END

What the above analysis missing is the "Isaias Factor". Isaias and Abiy have already made their mind up on annihilating TPLF. Abiy told the parliament that he has been preparing by building capacity (including missailes - I wonder who was paying for these!) outside the knowledge of Ministry of Defence. Isaias said he will annihilate them and “We will not try to convince them”.


Sabur
Member
Posts: 1364
Joined: 11 Aug 2018, 07:41

Re: ዶ/ር ዐብይ ምን ማድረግ ነበረበት? በኣብርሃ ደስታ

Post by Sabur » 07 Feb 2021, 13:39


sarcasm:

A Bankrupt merchant goes through old receipts again and again .

TPLF, the cancer in the Region, is Gone and is NOT coming back.

Give it up, will 'ya !!



sarcasm wrote:
07 Feb 2021, 12:42
ዶር ዐብይ ምን ማድረግ ነበረበት?

14 September 2020



Post Reply