ለ 22 ዓመታት ሲያገለግል የቆየው የጋራ ገቢዎች ማከፋፈያ ቀመር በፌደሬሽን ም/ቤት በመሻሻሉ ምክንያት ባለፉት 6 ወራት11,991,401,706.11 የክልሎች ድርሻ እንደተለየ የገቢዎች ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
የክልሎች ድርሻ በጀት ዓመት ተመሳሳይ ስድስት ወራት አንፃር ሲታይ የብር 8,681,102,030.61 ወይም 262.25% ዕድገት አለው ተብሏል፡፡
የገቢው ምንጭ ከኤክሳይዝ፣ ከተርን ኦቨር፣ ከተጨማሪ እሴት እና ከንግድ ትርፍ ግብር ታክሶች ብቻ የተሰበሰበ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የጋራ ገቢው ድርሻ ያደገው የጋራ ገቢ ማከፋፈያ ቀመሩ በመቀየሩና የተቋሙ ገቢ የመሰብሰብ አቅም እያደገ በመምጣቱ መሆኑን የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው ተናግረዋል።
የጋራ ገቢዎችን ለፊዴራል እና ለክልሎች እንዲከፋፈል በፌዴሬሽን ምክር ቤት በተቀመጠው የማከፉፈያ ቀመር መሰረት በስድስት ወራት የተሰራ እና አሁን ከተደረሰበት ውጤት ላይ መድረሱን ሚኒስትሩ አክለው ገልጸዋል።
Average increase 262.25%
Tigray has the lowest increase 27% - the only region with below average increase!
Oromia increase 185.5%
Amara increase 314.91%
South increase 375.61%

Please wait, video is loading...