Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11588
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

"ኢንጂነር ይልቃል ጌትነትና አቶ ልደቱ አያሌው የኤርትራ ወረራ ማውገዛቸው እደግፈዋለሁ" የኣቢይ ደጋፊ Activist ወልቀታይ መለስ ብስራት

Post by sarcasm » 30 Jan 2021, 11:42

ኢንጂነር ይልቃል ጌትነትና አቶ ልደቱ አያሌው ከመንግስት ጋር የህልክ ፖለቲካ የገጠሙ ይመስላል።

ትናንት ይህንን ብለዋል «አሁንም የኢትዮጵያ ቁጥር አንድ ጠላት ኢሳያስ አፍወርቂ ነው። ኢሳያስ በትግራይ ጣልቃ ሳይሆን የገባው ወረራ ነው የፈጸመው። ድንበራችንን፣ ሉአላዊነታችን መድፈር ብቻ አይደለም ዜጎቻችን እየገደለ ነው። » - ልደቱ አያሌው

«ኢሳያስ አፈወርቂ እንዲህ ችጋራም አዕምሮ እንዳለው አላውቅም ነበር» - ኢ/ር ይልቃል ጌትነት
እውነት ነው የኤርትራ ወታደር በትግራይ ውድመት አድርሷል፣ ወረራ ፈፅሟል ቁጥሩ በግልፅ ባይታወቅም ንፁሃን ዜጎች ገድሏል።
ይህንን ማውገዛቸው ብደገፈግፈውም ንግግራቸው በጣም ጥላቻ የበዛበት ሁኖ አግኝቸዋለሁ።


ሁለተኛው ለምን ህወሓት በሰሜን እዝ የፈፀመው ኢሳያስን እንዳወገዙበት ጭካኔውን መናገር እንዳልፈለጉ ሊገባኝ አልቻለም።
መርጦ ማውገዝ ትርጉም አይሰጥም።

Please wait, video is loading...