Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11589
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

የህወሀት ቁልፍ አባላት አቶ ሴኮቱሬ ጌታቸው ፣ አቶ ዘርአይ አስገዶም ፣ አቶ ዳንኤል አሰፋ እርምጃ ተወሰደባቸው

Post by MINILIK SALSAWI » 07 Jan 2021, 12:53

የህወሀት ቁልፍ አባላት አቶ ሴኮ ቱሬ ጌታቸው ፣ አቶ ዘርአይ አስገዶም ፣ አቶ አበበ ገ/መድህን ፣ አቶ ዳንኤል አሰፋ እርምጃ ተወሰደባቸው


የመከላከያ ሀይል ሰምሪት መምሪያ ኃላፊ ብ/ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው እንዳረጋገጡት ፣ .......................

1. የጁንታው ቃል አቀባይ ሴኩቱሬ ጌታቸው፣
2. ዘርአይ አስገዶም የቀድሞው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ስራ አስኪያጅና የብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የነበረ፣
3. አበበ ገብረመድህን የድምጸ ወያኔ ሃላፊ የነበረ፣
4. ዳንኤል አሰፋ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ የነበረ ከሹፌሮቻቸውና ከጥበቃዎቻቸው ጋር በጀግናው የመከላከያ ሰራዊት፣ በፌዴራል የጸጥታ ተቋማትና በትግራይ ህዝብና በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር በተደረገ የተቀናጀ ዘመቻ መደምሰሳቸውን ብርጋዴል ጀኔራል ተስፋዬ አያሌው ተናግረዋል።
ከተደመሰሱት ውስጥ ሴኩቱሬ ጌታቸው ከዚህ ቀደም በጁንታው መገናኛ ብዙሃን በኩል ጁንታው የመከላከያ ሰራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ መብረቃዊ ጥቃት ፈፅሟል ብሎ ማረጋገጡ ይታወሳል።

ከተደመሰሱት በተጨማሪም 9 የጁንታው ቁልፍ አባላት በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን እነሱም፣
1. ወይዘሮ ቅዱሳን ነጋ የቀድሞ የክልሉ አፈጉባኤ የነበረች፣
2. ዶክተር ሰለሞን ኪዳኔ የቀድሞ የትግራይ ክልል ከተማ ልማት ቢሮ ሃላፊና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ የነበረ፣
3. አቶ ተክለወይኒ አሰፋ የማረት ስራ አስፈጻሚ የነበረ፣
4. አቶ ገብረመድህን ተወልደ የክልሉ ንግድ ቢሮ ሃላፊ የነበረ፣
5. አቶ ወልደጊዮርጊስ ደስታ የክልሉ መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ የነበረ፣
6. አምባሳደር አባዲ ዘሙ በሱዳን የኢትዮጵያ የቀድሞ አምባሳደር የነበረና የጁንታውን ፖለቲካ ክንፍ የተቀላቀለ፣
7. አቶ ቴዎድሮስ ሃጎስ የመለስ አመራር አካዳሚ ፕሬዚዳንትና የኢፈርት ቦርድ ሃላፊ የነበረ፣
8. ወይዘሮ ምህረት ተክላይ የክልሉ ምክር ቤት ህግ አማካሪ የነበረች እንዲሁም
9. አቶ ብርሃነ አደም መሃመድ የክልሉ የንብረትና ግዢ ስራ ሂደት ሃላፊ የነበረ ሁሉም በቁጥጥር ስር ውለዋል።
የህወሃት ጁንታ ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር የዋሉት በጫካና ዋሻ ለዋሻ ሲንቀሳቀሱ በተደረገ ጠንካራ አሰሳ መሆኑንም ብርጋዴል ጀኔራሉ ገልጸዋል።የአገር መከላከያ ሰራዊት እነዚህ የጁንታው ቁልፍ የጥፋት ቡድን አባላት እንዲደመሰሱና በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ያላሰለሰ ድጋፍ ላደረገው መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ምስጋናውን አቅርቧል።ሰራዊቱ ወንጀለኞቹን አድኖ ለመያዝ ቃል በገባው መሰረት ግዳጁን እየተወጣ መሆኑን ገልፀዋል። #MinilikSalsawi

MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11589
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

Re: የህወሀት ቁልፍ አባላት አቶ ሴኮቱሬ ጌታቸው ፣ አቶ ዘርአይ አስገዶም ፣ አቶ ዳንኤል አሰፋ እርምጃ ተወሰደባቸው

Post by MINILIK SALSAWI » 08 Jan 2021, 08:40

በምኞታቸው ኢትዮጵያንና አንድነቷን የደመሰሱት ከቅዠታቸው ሳይነቁ ተደመሰሱ፡፡ ያ ሁሉ ዛቻ መጨረሻው በየተራ ቂሊንጦ መውረድ ሆነ ፤ “አትታበዩ” እንዲል መጽሐፉ፡፡ (ስናፍቅሽ አዲስ)

ትዕቢት መጥፎ ነው፡፡ መጽሐፉም ቢሆን አትታበዩ በኩራትም አትናገሩ ይላልና፡፡ በየስፍራው ሲዝቱ የከረሙት ወንበዴዎች ከየስፍራው እየተለቀሙ ነው፡፡ በምኞታቸው ኢትዮጵያንና አንድነቷን ደምስሰውት ነበር፡፡ ምኞታቸው እውን አልሆነም፡፡ እውን የሆነው ከየጉሮኖው መለቀማቸው ነው፡፡

መጨረሻቸው እንዲህ ሊሆን የብዙ ንጹሃን ህይወት ተመሳቀለ፡፡ ሀገር ወደመ፡፡ ያ ምስኪን ህዝብ አገኘሁ ያለውን ብርቅ ሰላም ነጠቁት፡፡ ያለ እኛ ትግራይ አትኖርም በሚል ጭካኔያቸው በአንቡላንስ ተኩስ ከፍተው ሲበረታ ጥለው ጠፉ፡፡ በአርባ ደቂቃ አመድ አደረግነው ያሉት የሀገር ክብር ከነታሪካቸው አመድ አደረጋቸው፡፡

አቶ ሴኮቱሬ ምን አስበው እንዲህ ያለው መዓት ውስጥ እንደገቡ ለመገመት እቸገራለሁ፡፡ ዘርን አስቀይሮ ፣ ሀገርን አስጠልቶ ፣ ወንበዴን አስጠግቶ ፣ ታሪክ አልባ ሞት መሞት ክብሩስ ለማን ነው?

ትናንት የገና ስጦታ ከመከላከያ ሠራዊት ቀርቦልናል፡፡ የሀገራችን ጠላቶች የሆኑት አኩራፊ ፖለቲከኞች በሚጠሏት ሀገር ሠራዊት እጅ ገብተዋል፡፡ መግለጫውን የሰጡት የሀገር መከላከያ ጀነራል ፣ የትግራይ ህዝብ ምግብና ውሃ ሳይቀር እየከለከለ ፣ ያሉበትን እየጠቆመ ፣ ከየስርቻው እንዲወጡ እንዳደረጋቸው ገልጸው ፣ ቀሪዎቹንም ለመያዝ ተመሳሳይ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ከመደምሰሳቸውም ሆነ በስተርጅና ማረሚያ ቤት ከመንከራተታቸው እኛ አንዳች ጉዳይ የለንም፡፡ ይህንን ያደረሰባቸው ትምክህትና ጥጋብ ነው፡፡ ዘርፎ በቃኝ ያለ ማለት ውጤት ለዚህ አብቅቷቸዋል፡፡ የናቁት ህዝብና ሀገር ከእግሩ ጫማ በታች አውሏቸዋል፡፡

ሰዎቹ በትግራይ ህዝብ ላይ ያደረሱትን በደል ለተመለከተ ፣ እንዲሁም በገዛ ወገኖቹ ፣ ወንድሞቹ ፣ እህቶቹና እናት አባቱ ላይ እንዲህ ያለ ጭካኔ የሚፈጽም ነጻ አውጪ በዓለም ታሪክ ታይቶ አይታወቅም፡፡

አሁን ያ ሁሉ ዛቻ በየተራ ወደ ቂሊንጦ በመውረድ እያበቃ ነው፡፡

ድሬ ቲዩብ ድረ ገጽ

Post Reply