ሱዳን - የሞተው ጅብ በገባበት ወጥመድ ዘላ የገባች ተረኛ ምርኮኛ::ሞት ቢዘገይ ሞኝ የቀረ ይመስለዋል ይላል አማራ መጭውን በምሣሌ ሲያስረዳ። በዐረቦች የወሬ ስካር ተገፋፍታ ሱዳን በባዶ ቤት ዘው ብላ ከማታወጣው የሞት ድጥ ገብታለች። ወደ ኋላ ምነው የጠላው ዕለት፣ ምነው የጠጁ ለት በሆነ ጉልበቴ ማለቷ እንዴማይቀር ግን እውነት ነው። ዐረቦች ወሬ እና በበና ወይም ጉራ ከማንም በላይ ያበዛሉ - የምር ቀን ሲደርስ ግን የተነፈሰ ጎማዎች ናቸው - ማናቸውም ከጥጓ ቁመው ላይረዷት ይችላሉ። የፈሪ ዱላ ብዙ ነው እንድሉ አንድት ትንሽ አገር እሥራዔል ነበረች በስድስት ቀን ግብፅን ከነ ጋሻጅግሬዋ አስጥታ የወቃቻቸው። እናም ዕድሜ ይስጠን እንጅ ሱዳን በግርድና የገባችበትን ጉዳይ ተገርፋ እና ተለብልባ ትወጣለች።
የትግሬ ወያኔ ቁሞ አልቃሾች አሁን እንዴ ቁላ ከዳር ቁመው ሱዳንን ደግፈው ይወነወናሉ። ይህም ከበሰበሱ አይቀር ግምት ነው ማለት ነው እንጅ። ከእንግድች ስለትግሬ ወያኔ የምንሰጋበት ዘመን ላይ አይደለንም። ከትግራይ ወያኔ ከመቃብር አፈሩን አራግፎ ኢትዮጵያን ዳግም ይዘርፋል ብሎ ከመጨነቅ ከሰማይ ላይ ተወርዋሪ ኮከብ ረግፎ ጉዳት ያመጣል ማለት አብላጫ ትክክል ግምት ነው። ወያኔም አምና ሁኗል ሱዳንም ትከተላለች።