************************
በትግራይ ክልል አዲስ የካቢኔ አባላት ተሹመው ወደ ስራ መግባታቸውን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አስታወቀ።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ገብረመስቀል ካሣ ለኢዜአ እንደገለጹት በክልሉ አዲስ የካቢኔ አባላት ተሹመው ወደ ስራ ገብተዋል።
በክልሉ ከሚያስፈልጉ 16 የካቢኔ አባላት መካከል 11 ተሿሚዎች በይፋ ስራ መጀመራቸውን ገልጸዋል።
በዚሁ መሠረት፡-
ዶክተር ካህሣይ ብርሃኑ …… የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ
ኢንጂነር አሉላ ሃብተአብ …… የኮንስትራክሽን፣ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ
ዶክተር ፋሲካ አምደ ስላሴ …… የጤና ቢሮ ሃላፊ
አቶ አበራ ንጉሴ ………. የፍትህ ቢሮ ሃላፊ
ወይዘሮ እቴነሽ ንጉሴ ……… የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ
አቶ ዮሴፍ ተስፋይ ………. የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ሃላፊ
ዶክተር ተስፋይ ሰለሞን …….. የትምህርት ቢሮ ሃላፊ
ዶክተር ገብረህይወት ለገሠ ……. የውሃ ጥናትና ዲዛይን ቢሮ ሃላፊ
አቶ ሰለሞን አበራ …….. የውሃ ሃብት ቢሮ ሃላፊ
አቶ አብርሃ ደስታ ……. የማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ እና
አቶ ገብረመስቀል ካሣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የጽህፈት ቤት ሃላፊ ሆነው መሾማቸው ተገልጿል።
ሌሎች ያልተሟሉ የካቢኔ አባላት በቀጣዮቹ ሳምንታት ተሟልተው ወደ ስራ ይገባሉ ተብሏል።
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
Please wait, video is loading...