ግብጽና ሌሎች ያካባቢያችን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጠላቶች ወደዱም ጠሉ ኢትዮጵያ አንዱ ያፍሪካ ሃያል አገር ከመሆን የሚገታት ነገር የለም፤ የውስጥ አንድነትና ፖለቲካችንን እስከ አስካስተካከልን ድረስ። ይህም የሚሆነው በሚከተሉት ምክኒያቶች ነው ።
አንድ፣ በሚቀጥሉት 20 አመታት ከፍተኛ የኤንርጂ አብዮጥ ቀውስና ለውጥ እየመጣ ነው ። የጸሃይ ሃይል የፔትሮሊየምና ጋዝ ነዳጅን የተካል። የሚንቀሳቀሱ መኪናዎች፣ ቴክኖሎጂዎች የሚገፉት በጋዝ ሳይሆን በኤሌክትሪክ ይሆናል። የሌሌክትሪክ ሃይል የሚመነጨው ከፎሲል ሃብት ሳይሆን ከዉሃ፣ ጸሃይና ነፋስ ሃብት ይሆናል ።
ኢትዮጵያ እጅግ ግዙፍ የዉሃ፣ የጸሃይና ነፋስ ሃብት አላት ። ስለሆነም ላፍሪካ ቀንድና ምስራቅ አፍሪካን የሚያንቀሳቅስ የሌክቴክ ሃይል ታመርታለች ።
በሃያ አመት ውስጥ ባለም ላይ ያሉ መኪናዎች የአሌክትሪክ መኪና ይሆናሉ ። ባለም ላይ ያሉ ቤትና ህንጻዎች የሚሞቁትና የሚቀዘቅዙት በጸሃይ ሃይል ይሆናል።
ስለዚህ ኢትዮጵያ ምጡቅ ቴክኖሎጂና ሰው ሰራሽ ልህቀት (ኢንተለጀንስ) በስፋት የምትጠቀም፣ በዉሃና ጸሃይ ሃይል በሚመት ኤሌክትሪክ ሃይል የሚነዱ መርኪናዎች (ኤሌክትሪክ ቪሀክልስ) ተጠቃሚና አምራች ትሆናለች ።
ይህን ብሩህና ከፕቴትሮሊየም ነጻ የሆነ የንጹ ቴክኖሎጂ የወደ ፊት ራዕይ ስላላት ነው እነግብጽና ሌሎች የአሮጌው ነዳጅ ባለሃብቶች ኢትዮጵያን የሚቶናከሉት ።
የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ የኢትዮጵያ ሊቃውንትና ጠቢባን ከማይረባው የደንቆሮ የዘር ንትርክ ወጥተው ታላቅ አገር ዘመናዊ አገር በንጽሁ ቴክኖሎጂና በምጡቅ ክህሎት የተደገፈ የኢትዮጵያ፣ ያፍሪካ ስልጣኔ ለመገንባት መነሳት አለብን እላለሁ !!
እኔ ሆረስ አይነ ኩሉ