Asfaw Abreha
·
አባ ሓጎስ ____
"የሰሜን ዕዝ ከወያኔ ጋር ወግኗል" ሲሏቸው አሜን ብለው የተቀበሉ የወያኔ ቀፎዎች በርካታ ነበሩ።
_ ታዲያማ የመከላከያ ሰራዊቱ የወያኔን የኩታራ ጀሌ ደረማምሶ ሁመራ ሲገባ አንዱ የወያኔ ቀፎ ሁነቱን በተቃራኒው ነበር የተቀበለው _ _ ከወያኔ ጋር ወገነ ተብሎ የተነገረው የሰሜን ዕዝ ጦር የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን ድል አድርጎ ሁመራ የገባ መስሎታል ለካ!!
ይህ ሰው( አባ ሓጎስ ) አስፋልት መንገዱ ላይ ጎራዴ ይዞ 'እልል' እያለ ሰራዊቱን ከተቀበለ በኋላ የተወሰኑትን ወታደሮች ወደ ንግድ ቤቱ ( ልኳንዳ ቤት ) ወስዶ ምሳ እየጋበዝ ...
" እና እንዴት ነው ? አሃዳዊያኑን ጨረሳችኋቸው አይደል ? ጦርነቱስ አለቀ ? " እያለ ወታደሮቹን አከታትሎ ይጠይቃቸዋል ።
ወታደሮቹም " ደብረፂዮንን ካልያዝን የሚያልቅ ጦርነት የለም !! " ብለው ሲሉት ..
ሰውየው በድንጋጤ " በስመአብ ወልዴ ! ምን ? .... ነይማ ማነሽ ! ካልጫው፣ ከቀዩ ፣ ከጥብሱ ፣ ከዱለቱ ፣ ከቅልጥሙ ጨመርመር አድርጊላቸው እስኪ .. እኔ የሚጠጣ ነገር ላምጣላቸው " ብሎ እንደወጣ ሳይመለስ ቀረ ።
አሁን ሱዳን _ ሃምዳይት አለ !!
እኔ ሁመራ በነበርኩበት ጊዜ የአባ ሓጎስ ምላስ እና የልኳንዳ ቤታቸው 'ምላስና ሰንበር' እጅግ የተለዩ ነበሩ !!!