Re: Alo
Eden:
ይሀውልህ ዛሬ ወጣቱ ሁሉ ከተማ ሄዶ ባህል ተረሳ እንጂ እኛ ስናድግ ይህ የምታየው የገና ባህል አሁን ካሁን እስከ ገና ቀን ድረስ ይደረግ ነበር ። እንዞሪቴ (የሆያ ሆዬ ዙረት ይባላል)። ለሁለት ሳምንት ከቤት ቤት እየዞርን ገንዘብ፣ እህል ሌላም ሰብስበን የገና እናት ቤት ከትመን እንበላውው ነበር ። የገና ጨዋታም ከወር በላይ ተካሂዶ የገና ቀን አንዱ ቀበሌ አሸንፎ ያልቅ ነበር ። የሴቶቹ ፣ የኢምር ኢምር ባህል በመስቀል ደመራ ግዜ የሚካሄድ የብርሃን በአል ነው ። ኢምር ማለት እጅግ ድንቅ የሆነ የኮከብ ወይም የጸሃይ ብርሃን ነው ።
በነገራችን ላይ አሲና የአገው ቃል ቢመስልም ጉራጌ አዚየን፣ አዝንደ ይለዋል ፣ እሱም ይሀውህ ማለትም በግዕዝ ኢዮሃ በአማራኛ እነሆ ማለት ነው !! እነሆ ገና አበበ፣ ገና በራ ማለት ነው !!!

Last edited by Horus on 19 Dec 2020, 04:43, edited 2 times in total.