DW : በኦሮሚያ ክልል በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን፣ አሙሩና ኪሪሙ ወረዳዎች ማንነታቸዉ በዉል ያልተነገረ ኃይላት ካለፈዉ ዕሁድ ጀምሮ በከፈቱት ጥቃት በትንሹ 13 ሠላማዊ ሰዎች ገደሉ፤ ሌሎች 10 አገቱ። የአካባቢዉ ነዋሪዎች እንደሚሉት ከተገደሉና ከታገቱት በተጨማሪ በርካታ ሰዎች የገቡበት አይታወቅም።የዶቸ ቬለ የረጅም ጊዜ አድማጭና የኪሩሙ ወረዳ፣ የሐሮ ቀበሌ ነዋሪ መሆናቸዉን የጠቀሱት ያሲን ይማም በፅሁፍ በላኩልን መልዕክት እንዳሉት ደግሞ አብዛኞቹ ሰዎች የተገደሉት በስለትና ጦር ተወግተዉ ነዉ።አቶ ያሲን እንዳሉት ከሟቾቹ 7ቱ ዘመዶቻቸዉ፣ አንዷ፣ የ3 ቀን ጨቅላ ነበረች።የአሶሳዉ ወኪላችን ነጋሳ ደሳለኝ እንደዘገበዉ የሆሮ ጉድሩ ዞን ባለስልጣናት ስለጥቃቱ መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ አይደሉም።ወለጋ ዉስጥ በተለያዩ ዞኖች በሚኖሩ ኦሮሞ ባልሆኑ ኢትዮጵያዉያን ላይ ጥቃት ሲደርስ ያሁኑ የመጀመሪያዉ አይደለም።
https://mereja.com/amharic/v2/424077
"ባለስልጣናት ስለጥቃቱ መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ አይደሉም።"
Yeah!! until they sort out the very minimum number of the murdered to report, they are not willing to speak. Orommuma is at its grandeur gloating over how and when to swallow the entire country. The targeted communities are considered sub-humans and be exposed to the blades of OLF, TPLF and Gumuz Cannibals with no repercussion whatsoever. The forces that have been able to crash TPLF within a mere two weeks, are still blaming the dead "Junta ' for the continued genocide.
Today it is the Agews and the Amharas, tomorrow who knows...time will tell.
-
Za-Ilmaknun
- Member
- Posts: 4487
- Joined: 15 Jun 2018, 17:40