Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
-
C beyond
- Member
- Posts: 1903
- Joined: 31 May 2013, 21:30
Post
by C beyond » 15 Dec 2020, 14:15
ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብልጽግና ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ
*************
በህገ-መንግስት የተደራጀ ክልል ውስጥ ከፌደራል መንግስት ዕውቅና ውጭ ገብቼ እዋጋለሁ ብሎ በተደጋጋሚ ዛቻ እና ማስፈራሪያ አዘል ቃላቶች ጭምር በመጠቀም መግለጫ መስጠት በህዝቦች መካከል ግልፅ ጦርነት ማወጅ ነው!!!
በፌደራል ሥርዓት ውስጥ የክልሎች ጤናማ ግንኙነት መኖር ወሳኝ ተግባር ነው፡፡ ክልሎች የተዋቀሩትበት ዋና ዓለማ በፌደራል ሥርዓት ውስጥ ሆነው በራስ አስተዳደር ሥርዓት አካባቢያቸውን ሙሉ በሙሉ የመምራት ኃላፊነት እንዳላቸው ይታወቃል፡፡
ሆኖም ግን አንዳንድ የአሮጌ ሥርዓት ናፋቂዎች አሁንም ህብረ-ብሔራዊ ፌደራሊዝም በጉልበት በማፍረስና ህገ-መንግስታዊ ሥርዓትን በመናድ በህዝቦች መካከል ለዘመናት የቆየውን አብሮነትና ወድማማችነት እንዲሻክር ይባስ ብሎም የብሔረሰብ ስም በመጥቀስ ጥላቻና ግጭት እንዲበረታ አልመው በመስራት ላይ እንደሚገኙ ለማስተዋል ችለናል፡፡
ባለፉት ዓመታት በሀገራችን ፖለቲካ ውስጥ በብሔርተኝነት፣ በዘረኝነትና በጎጠኝነት አስተሳሰብ ሲያከፋፍሉንና ሲያባሉን የነበሩ አሁንም የብልፅግና ካባ ደርበው ሁልጊዜ ከብሔር ቆጠራ ያልወጡ በርካታ የለውጡ አደናቃፊ ኃይሎች በመንግስትና በፓርቲ መዋቅር ውስጥ ራሱን በመደበቅ ክልል ከክልል ጋር በማጋጨት እኩይ ተግባራቸወን በማከናወን ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡
በአንድ ክልል ውስጥ የሚከሰቱ ችግሮችን ቶሎ የብሔር እና በክልሎች የሚገኙ ብሔረሰቦች አጀንዳ በማድረግ ችግሮች የበለጠ እንዲባባሱ ከዛም አልፎ ሉዓላዊነት ያለው፤ በህገ-መንግስት የተደራጀ ክልል ውስጥ ከፌደራል መንግስት ዕውቅና ውጭ ገብቼ እዋጋለሁ ብሎ በተደጋጋሚ ዛቻ እና ማስፈራሪያ አዘል ቃላቶችን ጭምር በመጠቀም መግለጫ መስጠት በህዝቦች መካከል ግልፅ ጦርነት ማወጅ ነው፡፡
ስለሆነም በክልላችን ውስጥ የሚትኖሩ ብሔር-ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ጦርነት ለማንም የማይበጅ አጥፊ ተግባር መሆኑን ተረድታችሁ በተለይ በመተከል ዞን ሥር የምትገኙ ወረዳዎች በሚዲያና በመግለጫ ጋጋታ ሳትደናገሩና ሳትረባበሹ እንዲሁም በብሔርና በጎጥ ሳትከፋፈሉ ለረጅም ዓመታት ያካበታችሁን የባህል እሴቶቻችሁን በመጠቀም ከመንግስትና ከፀጥታ አካላት ጋር ሆናችሁ አካባቢያችሁን በንቃት መጠበቅ ቀዳሚ ሥራ መሆኑን በመረዳት እና አጥፊዎች ለህግ ቀርበው ተገቢ ፍትህ እንዲያገኙ የራሳችሁን አስተዋጽኦ እንድታበረክቱ እንጠይቃለን።
Please wait, video is loading...
-
C beyond
- Member
- Posts: 1903
- Joined: 31 May 2013, 21:30
Post
by C beyond » 15 Dec 2020, 14:25
Please wait, video is loading...
-
C beyond
- Member
- Posts: 1903
- Joined: 31 May 2013, 21:30
Post
by C beyond » 15 Dec 2020, 14:47
Please wait, video is loading...
Please wait, video is loading...
-
TGAA
- Member+
- Posts: 5747
- Joined: 07 Apr 2019, 20:34
Post
by TGAA » 16 Dec 2020, 20:24
እነዚህ ደም ጠም ጎሰኞች ገና የአማራ ደም መጠጣት ጥማታቸው አልረካም ፤ ከግራና ከቀኝ የሚናገሩት ስለክልላቸው ነው ፤ የሚሉትም ግልጽ ነው ክልላችንን ዘግተን አማራን የመጨፍጨፍ ምበታችን ይጠበቅልን፤ ነው ፡፡ ፈዴራል የሚባለውም አማራ እየተገደለነ ሲባል መገደል የለባቸውም ብሎ እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ አማራ ብቻ አይደለም የሞተው የሚል ገበና በማይሸፍን
መልስ ነው የሚሰጠው ፤ ስለዚህ ፊደራሉ አቅም ካጣ አቅም ያለው ሄዶ እነዚህ ገዳዮች መንጥሮ ማውጣት ይችላል ፤ የምንናገረው ስለገዳዮች እንጂ ሌላ አይደለም ፤ ወያኔዎች ናቸው ተብሎ ምክንያት ሲሰጥ ቆይቷል አሁን ደግሞ ምን ሊባል ነው ? በውስጡ የሚኖሩ ዜጎችን ካመት እስካመት መከላከል የማይችል ክልል የክልል መብቴ ተነካ ብሎ ማልቀስ አይችልም ፤ አማሮች በመቶዎች ሲገደሉ ጋዜጠኞች ገበተው ሪፖርት እንዳያደርጉ ከማድረግ በስተቀርና በየደረጃው በአሰተዳደሩ ስር ከገዳዮች ጋር የሚተባበሩ ሰዎችን ከመሰግሰግ በሰተቀር ሌላ ያደረገው ነገር የለም ስለዚህ የክልል ዘፈኑን አቁሞ ዜጎችን የመከላከል ብቃት ካለው ይከላከል ፤ በወያኔ ፊክ ክልል አማሮች በአማርነታችው ሲጨፈጨፉ እርምጃ መውሰድ የአማራው ብቻ ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያዊ ሀላፊነት ነው ይህንን ውንብድና ማስቆም ፡ ይሄ የፈንቅል አሳማ ያልተረዳው ነገር ቢኖር ወያኔ የዘረፍው ግዛት ህጋዊ ነው ብሎ ከሆነ የሚከራከረው እዚያ የሚኖረው ህዝብ ምን እንደሚፈልግ ተጠይቆ እስኪወስን ወደ ታሪካዊ ቦታው ተመልሶ ይተዳደራል ፤
-
Abere
- Senior Member
- Posts: 15264
- Joined: 18 Jul 2019, 20:52
Post
by Abere » 16 Dec 2020, 21:27
ይህችን የጅብ ለቅሶ የሚያላዝነው ቤንሻንጉል ተብዬ የወያኔ ተላላኪ ዋና ዓላማው ለትግሬ ወያኔ የጥገኝነት ከለላ መስጫ ክልል መሆኑ ነው። የፌደራል መንግሥት ህግ የማስከበረ አቅም ካጣ የግደታ የአማራ ክልል ኃይል ገብቶ ወንጀለኞቹን ለፍትህ የማቅረብ የህግም የሞራልም መብት አለው። አሁንም ቤኒሻንጉል የሚባል የፈጠራ ክልል እንዴ ትግራይ የአገር ሀብት ተዘርፎ ዓመታት ምሽግ እና መሣርያ አዘጋጅቶ እንዴገና ብዙ አገራዊ ጥፍት እንዳደረሰው ሳይሆን ከወድሁ በትንሽ ኃይል አይቀጡ ቅጣት መሰጠት አለበት። የብልፅግና ማህተም እየለጠፈ ዝግ በሆን ክልል አማራ ሲጨፈጭፍ የሚኖርበት አንድም ምክንያት የለም። በጽዝህ ጉዳይ ላይ ከቤኒሻንጉል ይልቅ ቀድሞ የአማራ ክልል ቀነ ገደብ በመቁረጥ ጉዳዩ የሚስተካከልበት መንገደ መፈጠር አለበት። ያ ካልሆነ ግን የሰው ልጅ አርዶ ጉበት እና ኩላሊት ከሚበላ አውሬ ጋር ብዙ ሳፋጣ እና ቀልድ አያስፈልግም - ዋጋውን ከአለበት መክፈል ነው። ፌደራል ይዞ የሚያስገድል እና የሚያስደበድብ ከሆነ እርሱ እራሱ ወንጀለኛ ነው - የሟች ወገኖቻችን ነፍስ ይፋረዳቸዋል። ከዚህ በፊትም ወያኔን 27 ዓመት ትግራይን በአንቀልባ አዝለው አማራ አብረው ሲጨርሱም ሲያስጨርሱም ነበር። የፌደራል ኃይል ከጥንት ኃጥያቱ መማር እና መንፃት ይገባዋል። በህይወት የመኖር መብት ዓለም አቀፋዊ እንጅ ፌደራላዊ ወይም የአንድት ሰው አርዳ ሰው የምትብላ ታናሽ አውራጅ አይደለም። በዚህ አጋጣሚ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ህዝብ እራሱን ለዕልቂት ከሚጋብዙት የትግሬ ቀኝ ገዥዎች ማለትም የብልፅግና ሁቴል ተመጋቢው የማነ እንድሁም የኦነጉ ኦደፓ ታዬ ደንዳ ወዘተ ቅስቀሳ መጠበቅ ይገባዋል።