Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Hameddibewoyane
Member
Posts: 3890
Joined: 25 Sep 2019, 02:42

የትግራይ ቅዠት !!!!

Post by Hameddibewoyane » 11 Dec 2020, 17:02

ትግራይ አስባው የነበር ሙሉ ኤርትራን እና ከፊል የጎንደር አማራን በትግራይ ስር አድርገው ታላቋን ትግራይ ገንብተው ሊገነጠሉ ነበር ግን ምን ዋጋ አለው ላም አለኝ በሰማይ ወተቷንም አላይ ሆነ ነገሩ !!
ከዚህ በኋላ የትግራይን የበላይነት ዳግም እንዳይነሳ መቀሌ ላይ ገለን ተቀብሯል!!
ኤርትራ በክብር ለዘላለም ትኑር!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
ድል ለመላው አማራ ህዝብ !
ተሰብሰብ አማራ አንድ መሆን ነው ከዚህ በኋላ ጠላት አይከፋፍለንም።


Ejersa
Member
Posts: 3978
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

Re: የትግራይ ቅዠት !!!!

Post by Ejersa » 11 Dec 2020, 17:08

ያዝ እንግዲህ ግን ምን ዋጋ አለው በአንድ ወቅት ደብረጽዮን ነፍጠኛ ነፍጠኛውን እየለየህ በለው ሲል ሰማሁት እኔም ግርም ብሎኝ ሁለት አይነት ስሜት ሲፈራርቅብኝ ነበር ዛሬ ላይ ሁኘ የነሱን ሞት በማየቴ ግዜ ዳኛው ከማለት ውጭ ምንም የምለው የለም።
Hameddibewoyane wrote:
11 Dec 2020, 17:02
ትግራይ አስባው የነበር ሙሉ ኤርትራን እና ከፊል የጎንደር አማራን በትግራይ ስር አድርገው ታላቋን ትግራይ ገንብተው ሊገነጠሉ ነበር ግን ምን ዋጋ አለው ላም አለኝ በሰማይ ወተቷንም አላይ ሆነ ነገሩ !!
ከዚህ በኋላ የትግራይን የበላይነት ዳግም እንዳይነሳ መቀሌ ላይ ገለን ተቀብሯል!!
ኤርትራ በክብር ለዘላለም ትኑር!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
ድል ለመላው አማራ ህዝብ !
ተሰብሰብ አማራ አንድ መሆን ነው ከዚህ በኋላ ጠላት አይከፋፍለንም።


Abere
Senior Member
Posts: 15264
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: የትግራይ ቅዠት !!!!

Post by Abere » 11 Dec 2020, 17:21

ግን ይኸ በፎቶው ላይ ያለው ባሬ አፍ የሆነ የመቀሌ የወሬ ትምህርት ብሮፌሰር ማናምን እያለ አውራምባ ላይ እየወጣ የሚቦተልከው አስቀያሚው ልጅ ምን ሆነ? እስከ አሁን አልታሰረም ማለት ነው? ያስ ጠጃሙ መምህር ማን ቅብጥርስዮ የሚባል ከሀዲድ የንጨት ሽበት ምን ውጦት ይሆን? እነኝህን አስሮ አሁን ውሸታቸው መተንፈሱን ማሳየት ያስፈልጋል።

Ejersa
Member
Posts: 3978
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

Re: የትግራይ ቅዠት !!!!

Post by Ejersa » 11 Dec 2020, 18:07

Please wait, video is loading...

pushkin
Member+
Posts: 9684
Joined: 23 Jul 2015, 06:10

Re: የትግራይ ቅዠት !!!!

Post by pushkin » 11 Dec 2020, 20:21

“የብሄረ አግአዚያንና” “የትግራይ ትግረኝት” የጭንቋሌ ፖለቲካ

ብሄረ አግአዚያን የሚል የTPLF think-thank ቡድን የሚያራምደው ከኤርትሪያዊያን ጋር ሊፈጥረው ስለሚፈልገው የወንድማማችነትና ጓዳዊ ትስስር መመርመር ፤ በአንክሮ መከታተልና ተገቢውን ምላሽ መስጠት ይገባል ባይ ነኝ፡፡

ከሚቀጥሉት ጹሁፎች በመነሳት ነብስ ዘርቶና ስጋ ለብሶ መንቀሳቀስ የጀመረ እርኩስ መንፈስ የተላበሰ ሌሎችን ለመዋጥ ተዘጋጀ ማህበር ነው፡፡ ይህ ለመሆኑ ማሳያዎቼን ማቅረብ ይኖርብኛል፡፡ የሚቀጥለው አርፈተ ነገር ከተስፋይ ኪሮስ (ተስፋኪሮስ አረፈ አይደለም) የተወሰደ ነው፡፡

"የአግአዚያን እንቅስቃሴ ወደድንም ጠላንም እንቅስቃሴው በአውሮፓ፣ በአሜሪካ፣ በመካከለኛው ምስራቅና በአፍሪካ ሀገራት ጽ/ቤቶችን በመክፈት የአባላቱን ቁጥር በሚገርም ፍጥነት እያበዛ ያለ ማሕበር ነው፡፡ በ19ኛው ክፍለ ዘመን የሚኒሊክ የአሻጥር ፖለቲካ የተለያየ ህዝብ አንድ የሚሆንበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም፡፡" Even if this information is true, the plan will be hard or impossible for its realization on the ground. Null result! Just my opinion”

በታሪክ ከደቡብ አረቢያ ወደ ኢትዮጵያ ፈልሰው ገቡ የሚባሉ አጋአዚያን ፤ ሀድራማዊት የሚባሉ ጎሳዎች እንደነበሩና ሰሜን ኢትዮጵያ ውስጥ ከነበረው የአገው ማህበረሰብ ጋር ተዋህደው መጥፋታቸውን ታሪክ ይመሰክራል፡፡ በዚህ ሰአት ብሄረ አግአዝያን የሚባሉ ስደተኛ ቅሪቶች መኖራቸውን አላውቅም፡፡
ትግራይ ራሱ ኢሮፕን/ሳሆን ፤ ኩናማን እና አገውን በማቀፍ አይደለም ወይ እየተመሰረትኩኝ ነው እያለን ያለው??? እና እነዚህ አካላት በምን መስፈርት አጋአዚያን ሆነው ነው ለተፈጻሚነቱ አብረው ሰርተው የተባለውን ሃሳብ እውን ሊየያደርጉ የሚችሉት???? ብሎ ማሰብ ይቻል ይሆናል፡፡ ምእራብ ትግራይ የሚባለው የኩናማ ተጽእኖ የበዛበት ፤ በታሪክ በአገውነት የሚታወቀው ተምቤንና ከተምቤን ወደ ደቡብ አቅጣጫ ያለው ሰሃርቲ ሳምረ ፤ ቦራ ስላዋ ፤ አበርገሌ እና ከአገው ጋር ከፍተኛ ቅርኝት አለው የሚባለው እንደርታ በምን መስፈርት አጋአዚያን ይሆናሉ???? ማለትም ይቻላል፡፡ ሌሎች ታሪካዊ ይሁን ማህበረ-ባህላዊ ቁም ነገሮችን ያዘሉ መሰል ጥያቄዎችን መጠየቅ ይቻላል፡፡

ነገር ግን መነሻ ታሪካዊ መሰረት ይኑረው አይኑረው ፤ ትርጉም ያለው ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል ድጋፍ ያገኛል አያገኝም ፤ የሚገመተው የፖለቲካ አላማውስ አሁን ካለው ነባራዊና ተጨባጭ የኢትዮጵያና የኤርትራ ሁኔታ ጋር ሊመስልና ሊሳካ የሚችል አካሄድ ነውን???? ሌላ ጥያቄ ነው፡፡ ተቋቁሞ ግን “በምንልክ አሻጥር ተለያየ” የሚሉትን የኤርትራና የትግራይን ትግሬዎች በቅርቡ ለማገናኘት በሚል በእንቅስቃሴ ላይ መሆኑ የማይታበል ሀቅ ይመስላል፡፡ የኤርትራና ትግራይ አግአዚያን እንቅስቃሴ ለቀሪዎቻችን ሊኖረው የሚችለውን ትርጉም ምንድን ነው የሚለውን እንድናስብ ለማስገንዘብ ነው፡፡
--------------
ብሄረ አግአዚያን የሚባሉትን ሳስብ አእምሮየ ውስጥ የሚመጡብኝ ሁለቱ TPLF እና EPLF ወይም ሻእብያን የመሰሉ ድርጅቶችና ፕሮፌሰር ተስፋጽዮን መድሃኔ የተባሉ የኤርትራ ሙሁር ናቸው፡፡ በግምት ከሶስት አመት በፊት አካባቢ ይመስለኛል በጻፉት አርቲክል በኤርትራም በትግራይም ያሉት ሁለቱ የገዥ መደቡ አባላት ለተመሳሳይ አለማ እየሰሩ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡ ኢትዮጵያን የሚመሩት አካላት በኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን በኩል የኤርትራ ትውልድ እንዳለቸው የሚወራውን ያክል በኤርትራ በኩልም ያሉት መሪዎች የትግራይ ትውልድ ያላቸው የተጠራቀሙበት ተደርጎ እንደሚወሰድ ይገልጻሉ፡፡ ይህ ፕረዚደንቱንም ይጨምራል፡፡

እንደሳቸው አባባል የኤርትራ ማህበረሰብ ተራማጅ ፤ ለውጥ የሚቀበልና ስልጡን ማህበረሰብ ተደርጎ ይቆጠር እንደነበር በተቃራኒዉ የትግራይ ማህበረሰብ ደግሞ ወግ አጥባቂና ለወግና ልማድ ተገዥ እንዲሁም ለለውጥ የማይመች ተደርጎ ይቆጠር እንደነበር ያብራሩና ይህ አመለካከትና ተጨባጭ ነበር ብለው የሚያምኑት ነባራዊ የነበረው ሁኔታ እንዲሁም ይህ አመለካከት የወለደው በኤርትራና በትግራይ መካከል የነበረውን የተዛነፈ የስነ-ልቦና ልዩነት ፤ አመለካከትና አንዱ ለአንዱ የነበረውን የተዛባ አመለካከት ለመቀየር በየፊናቸው እየሰሩ መሆናቸውን ይገልጻሉ፡፡ የኤርትራ መንግስት የኤርትራን ማህበረሰብ በብዙ መልኩ ቀይዶ በመያዝና ማህበረ-ባህላዊ እድገቱን በመግታት ዝቅ አድርጎ ያየው የነበረውን የትግራይን ማህበረሰብ በሚያደርገው ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴና እድገት የተለየ አድናቆትና ክብር እንዲያሳድር ለማድረግ ተግቶ እየሰራ ነው ይላሉ፡፡ በኢትዮጵያ በኩል ደግሞ የሀገሪቱን ሃብት በብልጫ በመውሰድ ክልሉን በማልማት የትግራይን የሞራልና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን በማሳደግ ከኤርትራዊያኖቹ ጋር ተቀራራቢ ስነ-ልቦና እንዲፈጥር በማድረግ ሁለቱን ማህበረሰቦች የማቀራረብ ስራ መስራት ነው፡፡ አባባሉ አንደገባኝ አንዱ ዝቅ እንዲል አንዱ ደግሞ ከፍ እንዲል ተደርጎ በተመጣጠነ ስነልቦና ለአዲስ የትግራይ ትግሪኝት አገር ምስረታ ዝግጁ ይሆናሉ ማለት ነው፡፡
--------
ገበጣ በሚባለው የባህል ጨዋታ በራያ ጭንቋሌ የሚባል የጨዋታው ህግ አለ፡፡ ጨንቋሌ ማለት አንድ ሰው ጨዋታውን ለማስኬድ ጁሙን ወይም ጉድጓድ ውስጥ ያለውን ድንጋይ ሲያነሳ ከሚያነሳበት በፊት ካለው ጉድጓድ አንድ ጠጠር ካለ ጭኗቋሌ ይላል፡፡ ይህ ማለት ይች ከኋላ ጉድጓድ ያለችው ጠጠር ብታስፈልገኝ ወይም ብተጠቅመኝ ትከተለኝ ባትጠቅመኝ ትቅር ማለት ነው፡፡ እናም ጭንቋሌ ብወዳት ትከተለኝ ብጠላት ትቅርብኝ ብሎ ይነሳል፡፡ ይዞር ይዞርና ጠቃሚ ሆና ከተገኘት አንስቶ ይበላባታል/ያሸንፍባታል ካልጠቀመች ይተዋታል፡፡

የአግአዚያንም ፖለቲካ የጭንቋሌ ፖለቲካ ነው፡፡ መጀመርያ ከኤርትራዊያን በላይ አርትራዊያን ሆነው፤ የኤርትራ ጉዳይ ብለው ጽፈው ራሳቸውንና ሌላውን የሚያደነግር የቅኝ ግዛት ታሪክ ፈጥረው ፤ ኤርትራዊያን ራሳቸው በሆነ የአስተዳደር ስርአት ኢትዮጵያ ጋር ለመኖር ፍላጎት ሲያሳዩ በኤርትራ ህዝብ ፍላጎት እየተደራደራችሁ ነው ብለው ከሰው ፤ አገር በጋራ ሲቆጣጠሩ አመለካከታቸውን እንዲያለዝቡ አድርገው በጋራ መኖር እንዳይችሉ አለማቀፋዊ ወግና ስርአቱ ባልጠበቀ ሁኔታ አጣድፈው እንዲወጡ አድርገው አገሪቱን በቁጥጥር ስራቸው እንዳሻቸው ሲያደርጉ ከኖሮ በኋላ ሌላው የፍትሃዊነት ፤ የእኩልነት ፤ የነጻነት ጥያቄ አንስቶ በነበረው የበለጠ ተጠቃሚነት ደረጃ መጠቀም እንደማይቻል መገንዘብ ሲጀምሩ ጭንቋሌ ማለት ጀመሩ ማለት ነው፡፡ ለአግዚያን ኢትዮጵያ የጭንቋሌ ድንጋይ ነች ማለት ነው፡፡ ጥቅም ስትሰጥ የምትገለገልባት ከሌሎች በበለጠ መጠቀም እንደማትችልባት ስትረዳ አንገተህን አስግገህ ፤ ወንዝ ተሸግረህ ፤ ታሪክ መዘህ አግዚያዊነት የምታማትርባት የጭንቋሌ ድንጋይ፡፡

ፐሮፌሰሩ ባሰቀመጡት መንገድ እና በሁለቱ ማህበረሰቦች በነበረው ታሪካዊም ይሁን ማህበረ-ፖለቲካዊ መሰረት የሌለው መናናቅ ምክኒያት አዲስ አባባ እንደገቡ አብረው ለመቀጠል እንኳነ ቢስማሙ ተሰማምተው ሊዘልቁ የሚችሉባቸው ፖለተካዊም ፤ ኢከኖሚያዊም ይሁን ስነልቦናዊም ነባራዊ ሁኔታዎች አይኖሩም ነበር፡፡ ያም እዛ ሆኖ በቡና ምርት ላኪነት በአለም ደረጃ ደረጃው እንደተጠበቀለት መቀጠል ሲያምረው ፤ በዚህ በኩል ደግሞ ቡናን ጨምሮ ጥቅሙ በነሱ ከተያዘ ለእኛ ምን ተረፈ በሚል ግብግብ ጨዋታ ፈረሰ ደቦ ተቆረሰ ብለው ወንድሞቻችንን ላልረባ ነገር አስጨረሱብን፡፡

አሁን ምን አዲስ ነገር ተገኘ ????????? የሚለው ትልቁ ጥያቄ ነው::
እሳቸው ይህ ዝግጅት ኤርትራ ውስጥ የትግርኛ ተናጋሪውን ቁጥር በመጨመር የፖለቲካ ሚዛኑን ወደ ትግሬዎቹ ስለሚያጋድለውና ነባር ግንኙነቱን ስለሚያዛባው እንዲሁም አሁን ያለው በኤርትራዊ ዜግነት ላይ የተመሰረተ ማህበረሰባዊና ፖለቲካዊ አተያይ ስለሚበክለው አይደግፉትም፡፡ ተጨማሪና ሁለተኛው ተያያዥ ምክኒያታቸው TPLF ኢትዮጵያ ውስጥ ያሳደገውን የበለጠ ተጠቃሚነት ቀመሩንና አስተሰሰቡን ይዞብን ስለሚመጣ ኤርትራ ውስጥ በማህበረሰብ ደረጃ የሰፈነውን ፍትሃዊ አመለካከትና አሰራር (አንድ ጎሳ በሌላው ኪሳራ የሚከብርበት ፖለቲካዊ አስተሳሰብም አሰረርም ባለመኖሩ) ኤርትራ ውስጥ ባሉ የተለያዩ ማህበረሰቦች ማህበረሰባዊ ችግር ያስከትላል ብለው በማመናቸው እንዲሁም በአካባቢው ሌሎች ማህበረሰቦች ፍላጎት ካላቸው ውጫዊ አካላት ጋርም መልካም ባህላዊም ይሁን ፖለቲካዊ ግንኝነት ስለማይፈጥር ኤርትራ የተረጋጋች አገር አትሆንም ከሚል ስሌት የመጣ ይመስላል፡፡

የፕሮፌሰር ተስፋጽዮን መድሃኔ ትንታኔ እሳቸው በገለጡት መንገድ ትክክል ይሆን??? የሚል ጥያቄ ሊጭር ይችል ይሆናል (በተለይም በኤርትራ በኩል ይሰራል የተባለው ) ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ባለው ፖለቲካዊ ሁኔታ ውስጥ ተሁኖ ከኤርትራ ጋር ሊፈጠር የሚፈለገው ወንድማማችነት ግን የሚያመላክተው በቁም ነገር ተይዞ እንደ አንድ የፖለተቲካ አማራጭ ዝግጅት እየተደረገበት ያለ አብይ ጉዳይ ሆኖ ይሰማኛል፡

ይህ ደግሞ ለእኛ ለራዮች ፤ ለዋጎችና ለወልቃይቴዎች በተለየ መንገድ ለሌሎች ኢትዮጵያዊያን ባጠቃላይ ምን ማለት እንደሆነ ማሰብና ማሰላሰል ያስፈልጋል፡፡ እንደ “ብሄረ አግአዚያኑ” ነን ባዮች ድንበር ሳንሻገር የዋግ ፤ የራያና ወልቃይት ኢትዮጵያዊ ወንድማማችነት አያስፈልግም ተትላላችሁ?????? ለትብብራችን መነሻ የሚሆን የውሸት ታሪክ ሺ አመታት ወደ ኋላ ተጉዘን መፈብረክም አያስፈልግም፡፡ህያው ነዋ!!!!

የራያ ሰው ሁሩበ በሚባለው ማታ ማታ በሚደረግ የጎረምሳ ወንዶች የባህል ስፖርት ጨዋታ ለሁለቱም ቡድኖች እንደ ጆከር የሚያከለግለውን ግለሰብ በራይኛ “ወርሕ ኮለል” ይለዋል ፡፡ እናም ዋጎች ከመልከአ ምድራዊ አቀማመጣቸው ይችን ድርሻ መጫወት ያለባቸው ይመስለኛል፡፡

አግዘው ህዳሩ

Hameddibewoyane
Member
Posts: 3890
Joined: 25 Sep 2019, 02:42

Re: የትግራይ ቅዠት !!!!

Post by Hameddibewoyane » 15 Dec 2020, 13:01

ትግራዮች በተለምዶ ትግሬዎች እየተባሉ ይጠራሉ። ይሄ ትግሬ የሚለው ስም ሌላ ኤርትራ እና ሱዳን ውስጥ ካለ ትግረ (ሐይሻ) በሚል ከሚጠራ ብሔር ጋር እንዳይመሳሰል ላስገነዝብ ወዳለሁ። ኢትዮጵያውያን ትግሬ እያልን የምንጠራቸው ባብዛኛው አሁን ትግራይ እየተባለ በሚጠራው ክልል ውስጥ በአደዋ፣ ሽሬ(ሽረ)፣ መቀሌ(መቐለ) የሚኖሩትን ትግርኛ ተናጋሪዎች ሲሆን አሁን ያሉት እነዚህ ከላይ በተጠቀሱት ቦታዎች የሚኖሩ ትግርኛ ተናጋሪዎች ራሳቸውን በክልላቸው ስም ትግራይ እንዲሁም ተጋሩ እያሉ መጥራትን ይመርጣሉ ።

እኔም በዚህ ፁሑፍ ላይ መጠራት በፈለጉበት ስያሜ ትግራዮች እያልኩ እጠራቸዋለሁ። ወደ ዋናው ነገራችን ስንመጣ ብዙ ወገኖች ትግራዮች እና የ ኤርትራ ብሄረ ትግርኛ አንድ አይነት ብሔር ይመስሉዋቸዋል። በመሰረቱ ግን ሁለቱ ፍፁም የተለያዩ ነገዶች ናቸው። ትግራዮች የ ኤርትራ ብሄረ ትግርኛን ትግራዮች ናቸው አንድ ብሔር ነን ብለው ያስባሉ። ብዙ ትግራዮችም ኤርትራዊ የመሆን ፍላጎት አላቸው። የባድመ ጦርነት ከመነሳቱ በፊት ብዙዎቹ ትግራዮች ራሳቸውን ኤርትራዊ እያሉ ይጠሩ ነበር። ከባድመ ጦርነት በሁዋላ እነዚህ ትግራዮች ከፍተኛ የሆነ የማንነት ቀውስ ውስጥ ገብተዋል። በተቃራኒው ብሄረ ትግርኛዎች ስለ ትግራዮች ያላቸው ስሜት ምን እንደሆነ ሲጠየቁ ትግራዮች ወይም አጋሜዎች እያሉ ይጠሩዋቸዋል። (Hassan Adem, M.T., Tekle B, 2010) እነዚህ ኤርትራውያን ብሄረ ትግርኛዎች ትግራዮችን የማይታመኑ እና ልባቸው የማይገኝ አድርገው በአሉታዊ መንገድ ይስሉዋቸዋል። ”Eritreans sometimes contemptuously refer to them- cannot be trusted and never could.” (Smith,et al. 2003, Africa, volume 73, p.377) ። በኤርትራውያን ብሄረ ትግርኛዎች ላይ በተደረገው በዚህ አንትሮፖሎጅካል ማህበራዊ ጥናት ላይ አንድ የ eplf ታጋይ የነበረ ለፕሮፌሰር ሪድ ”አባቶቻችን እና ቅድመ አያቶቻችን እነዚህ ትግራዮች አደገኛ ናቸው በደንብ እናውቃቸዋለን ብለው አስጠንቅቀውናል” ብሎ ኤርትራውያን ነፃነታቸውን ባወጁበት ዓመተምህረት በ አውሮፓ አቆጣጠር በ1991 ወይም በ1983 ኢ.አ ምስክርነት ሰጦ ነበር። “Be careful, these people are dangerous, we know them well!” (Smith,et al. 2003, Africa, volume 73, p.377 )

ብሄረ ትግርኛዎች ከ ትግሬዎች የተለየ ማንነት እንዳላቸው እያሳወቁ ትግሬዎች ብሔረ ትግርኛዎችን እንደራሳቸው ብሄር አድርገው ለምን ይቆጥሩዋቸዋል? ብሄረ ትግርኛዎች ኤርትራዊ የሚባል ሃገራዊ ማንነት ሲገነቡ ትግራዮች ከብሄረ ትግርኛዎች የተለየ ብሔራዊ ማንነት መገንባት ለምን ተሳናቸው? በትግራዮች ዘንድ የሚታየው የማንነት ቀውስ ምንጩ ምንድን ነው? ለመሆኑ ይህ የብሔረ ትግርኛዎች ለ ትግራዮች ያላቸው አሉታዊ አመለካከት እንዴት ሊመጣ ቻለ?

የነገድ ማንነት ትርጉም በተለያዩ የማህበራዊ ሳይንስ ተመራማሪዎች እና ፀሐፊዎች የተለያየ ፍች ይሰጠዋል። ነገድ ጎሳ እና ብሄር የሚሉት ቃላት ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ባለው ተቀራራቢ ፍች ነው ያላቸው። ብሔር ከሀገር ጋር ጎሳ ከቁዋንቁዋ ጋር ስለሚዛመዱ ethnicity ለሚለው የእንግሊዘኛ ቃል በጣም ተቀራራቢ የሆነው ቃል ነገድ የሚለው ስለሆነ ነገድ እያልኩ እጠቀማለሁ።

ማክስ ዌበር የነገድ ማንነትን ተመሳሳይ የሆነ ውጫዊ አቁዋም ወይም ልምድ ስላለን አንድ የጋራ የነገድ ምንጭ አለኝ ብሎ የማመን ግላዊ እሳቤ ነው ይለዋል። የአንድ ነገድ አባልነት እውነተኛ የደም ትስስር ቢኖረም ባይኖረም ዋና አላማው ፖለቲካዊ ቡድን ወይም ማህበረሰብ መፍጠር ነው ይላል።

“Those human groups that entertain a subjective belief in their common descent because of similarities of physical type or of customs or both, or because of memories of colonization and migration; this belief must be important for group formation; furthermore it does not matter whether an objective blood relationship exists…ethnic membership does not constitute a group; it only facilitates group formation of any kind, particularly in the political sphere. On the other hand, it is primarily the political community, no matter how artificially organized, that inspires the belief in common ethnicity.” (1978, Max Weber, p. 389)

ፕሮፌሰር ጆሹዋ ደግሞ የነገድ ማንነት የሚወሰነው በዋናነት በስነልቦና ነው ይላል። አንድ ሰው የአንድ ነገድ አባል ነኝ ብሎ ራሱን ማሳመን እና መግለፅ ይኖርበታል ይላል።

The psychological dimension of ethnicity is perhaps the most important because, regardless of variations in the biological, cultural, and social domains, if a person self-identifies as a member of a particular ethnic group, then he or she is willing to be perceived and treated as a member of that group. Thus, self-ascribed and other-ascribed ethnic labels are the overt manifestations of individuals’ identification with a particular ethnicity. (2001, Joshua A. Fishman, p.115)

የነገድ ማንነት ከ ሃይማኖት ከቋንቋ እና ባህል ጋርም ይያያዛል። ግን በሀማኖት እና ቋንቋ መቀራረብ አንድ የጋራ ነገድን አይፈጥርም። ለምሳሌ ጀርመኖች እና ኦስትርያዎች ተመሳሳይ ቋንቋ አና እምነት እንዲሁም ተቀራራቢ ባህል እና ወግ ቢኖራቸውም ራሳቸውን እንደ ሁለት የተለያዩ ነገዶች ነው የሚያዩት። ሁቱ፣ ቱትሲ እና ትዋ ሶስቱም ነገዶች ሩዋንዳ ሩንዲ የተባለ ተመሳሳይ የአፍ መፍቻ ቋንቋ ነው ያላቸው። ሃይማኖታቸውም ባመዛኙ ተመሳሳይ ካቶሊክ ነው። ባህላቸውም ተቀራራቢ የባንቱዎች ባህል ነው። ነገር ግን ራሳቸውን እንደተለያዩ ነገዶች ነው የሚቆጥሩት። በደቡብ ሱዳን ያሉ ዲንቃዎች ቋንቋ ብዙ አይነት አነጋገር ቢኖረውም አንድ ዲንቃ ነገድ ነን ነው የሚሉት። የ ኑዌሮች እና የ ሺልቆች (Shilluk) ቋንቋ በጣም ተመሳሳይ ቢሆንም ሁለቱ ራሳቸውን እንደተለያዩ ነገዶች ነው የሚያዩት።
ለብሄረ ትግርኛ ነገድ ትግርኛ የቋንቋቸው መጠሪያ እና የነገዳቸው መጠሪያ ስያሜ ምንጭ ነው።

”In official papers distributed by the Eritrean Government, the ‘language’ (Tigrinya) is used as an ethnic term of the group” (1998, Kjetil Tronvoll, P. 30).ኤርትራ ውስጥ ያሉ ሌሎች ነገዶችም የቋንቋቸው ስም የነገዳቸው መጠሪያ ሁኑዋል። ”Nearly all the ethnic groups in Eritrea are also named after their language, including the Tigre, Kunama, Afar, Nara, Saho, Hedareb, and Bilen” (Hassan Adem, M.T., Tekle B, 2010)

ብዙ በዓለም ላይ ያሉ ነገዶች ስም እና ቋንቋ የተመሳሰለበት ግዜ አለ። አማራ እና አማርኛ ፣ ኦሮሞ እና ኦሮምኛ፣ እንግሊዝ እና እንግሊዘኛ፣ ፍሬንች እና ፈረንሳይኛ ወዘተረፈ። በ 1990ዎቹ በተደረገ ጥናት አብዛኛዎቹ ብሄረ ትግርኛዎች ራሳቸውን የሚገልፁት ሐማሴን፣ አካለ ጉዛይ እና ሰራዬ በሚል ነበር።

“However, people from the highlands do not speak of themselves as “Tigrinyans.” When asked they would usually reply as did Tewolde, a 60-year old villager from Mai Weini: “Tigrinya is just the language, it is not the tribe (aliet). The tribe is Kebessa (highland). Or, when in the highlands, the tribe is Akele-Guzai, Seraye or Hamasien”( Kjetil Tronvoll, P. 30,1998 )”

የመጀመሪያው በትግርኛ የተፃፈ ፅሁፍ የተገኘው የአሁኗ ኤርትራ ውስጥ ሲሆን ትግርኛ ቋንቋ ሁለት አይነት የአነጋገር ዘየዎች አሉት። የ አስመራ እና የ ትግራይ። የትግርኛ ቋንቋ መደባዊ ቋንቋ የ አስመራ ዘዬ ነው ። ሃማሴኖች በ ንጉስ ላሊበላ እና በ አፄ ሰርፀ ድንግል ከ ወሎ እና ጎንደር በውትድርና የሄዱ እንደሆኑ ብዙ የታሪክ ድርሳናት ያትታሉ።

ከእንግዲህ በ ብሄረ ትግርኛ በትግራይ እና በ ትግረ መካከል ያለው ዝምድና ”ትግ” የምትለው ቃል ናት። ይህም እነዚህ ሶስት ህዝቦች ከዘመናት በፊት ከአንድ ተቀራራቢ የዘር ሐረግ መጠው ሊሆን ይችላሉ። ዳሩ ግን ከዘመናት በፊት ሁሉም የሰው ልጅ ከአንድ የዘር ግንድ እንደተነሳ ይታመናል። በዘመናት ሂደት ይህ አንድ የሰው ዘር በቦታ እና በአካባቢ ልዩነት የራሱን ቋንቋ እና ባህል እንዲሁም ነገድ ማህበራዊ ቡድን እየፈጠረ እንደመጣ ይታመናል።

ከ እንግዲህ እነዚህ ብሄረ ትግርኛዎች ራሳቸውን ከ ትግራዮች ጋር እንደ አንድ ነገድ የማያዩት ለምድን ነው? ምክንያቱም ተመሳሳይ የሆነ ስነልቦና እና አብሮ የመኖር ትስስር ስለሌላቸው ነው። ብሄረ ትግርኛዎች እና ትግራዮች ለዘመናት የተለያዩ ግዛቶች እንደነበሩ በታሪክ ተጠቅሱዋል።አብዛኛዎቹ ብሄረ ትግርኛዎች ጎንደሬዎች ቤጃዎች እና በለዎች እንደሆኑ በስፋት ተጠቅሱዋል።

“The 9th-century Arab geographer Al-Ya’qubi wrote of six Beja kingdoms located in what is today Eritrea. Beja place names are found throughout the central and northern highlands of Eritrea, suggesting widespread Beja interaction with other communities (Schmidt, Curtis, Teka , p. 284, 2008)”

ብሄረ ትግርኛ እና ትግራዮች ተቀራራቢ ቋንቋ ቢጠቀሙም የተለያዩ ሁለት ነገዶች መሆናቸውን በአካባቢው ጥናት ያደረጉ ተመራማሪዎች ፅፈዋል። ሮይ ፓተማን ብሄረ ትግርኛ እና ትግራዮች ሁለቱ የተለያዩ ነገዶች መሆናቸውን እንዲህ አስቀምጦታል። አስትርያዎች ጀርመኖች እና የተወሰኑ ስዊዞች ጀርመንኛ ቢናገሩም ሁሉም የተለያዩ ህዝቦች እነሆኑት ሁሉ በ ኤርትራ ከፍታማ ቦታዎች የሚኖሩት እና ትግራዮች ከጥንት ጀምሮ የተለያዩ ነገዶች ናቸው ስል ፅፉዋል።

“Even in those distant times, however, it is clear that the land and people of highland Eritrea were distinct from people of Tigray, even though they spoke the same language-just as the Austrians, Swiss Germans and the Germans of today are very different people (Roy Pateman, P.33, 1998).”

ከላይ እንደገለፅኩት ሁቱ እና ቱትሲ ተመሳሳይ የአፍ መፍቻ ቋንቋ እና ተመሳሳይ ሃይማኖት ቢኖራቸውም ራሳቸውን እንደ ሁለት የተለያዩ ነገዶች ነው የሚቆጥሩት። ፖርቹጋላዊው ፍራንሲስኮ አልቫሬዝ በ 16ኛው ክፍለ ዘመን ወደ ምስራቅ አፍሪካ በመጣ ግዜ ያየውን እንዲህ ገልፁዋል።

”ይህ መረብ የተባለው ወንዝ ባህረ ነጋሽ እና ትግራይን የሚለያይ ድንበር ነው” ”Here; this river, the Mareb, separates the country of the Bahar Nagash from that of Tigray” ( Francisco Alvarez al et , P. 91, 1540)።

ባለባበሳቸው እና በባህላቸውም የተለያዩ መሆናቸውን ገልፁዋል

”The men (of Medri-Bahri) wear different costumes; so also the women who are married or living with men. Here (Tigray), they wear wrapped round them dark coloured woolen stuffs, with large fringes of the same stuff, and they do not wear diadems on their heads like those of the Barnagasi (Midri-Bahri people)”. ( Francisco Alvarez, P. 91-2 ,1970)

ስኮትላንዳዊው ጀምስ ብሩስም ባህረ ነጋሽ የ አሁኑ ኤርትራ ከ ትግራዮች የተለየ መሆኑን እና ድንበራቸው መረብ ወንዝ መሆኑን አስቀምጡዋል። በምዕራብም በኩል የትግራይ ድንበር ተከዜ ወንዝ እንደሆነ ቁልጭ አድርጎ አስቀምጡዋል። ትግራዮች ከ ብሄረ ትግራይ ጋር በታሪክ አብረው የኖሩበት ግዜ አልተመዘገበም። የአሁኖቹ አንዳንድ የትግራይ ምሁራን ከየት አምጥተው ነው ብሄረ ትግርኛን እና ትግራይን የለያየው ምንሊክ ነው የሚሉት? ከዚሁ ጋር በተያያዘ ወልቃይት ጠገዴ ጠለምት እና ታች አርማጭሆን አፄ ምንሊክ ነው ወደ ጎንደር ያስገቡት የሚሉት ሁሉ ውሸት መሆኑን የጀምስ ብሩስ ማስረጃ ያሳያል።

“The greatest length of Tigre (Tigray) is two hundred miles, and the greatest breadth one hundred and twenty. It lies between the territory of the BaharNagash (which reaches to the river Mareb) on the east, and the river Tacazze on the west.” ( James Bruce, p.83,1860)

በ 1838 ወደ አካባቢው ያቀናው አሳሽ ጆን ሚልስም የ ትግራይ እና የባህረ ነጋሽ ድንበር መረብ ወንዝ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ አስቀምጡዋል። ”መረብ የ ትግራይ እና የባህረ ነጋሽ ግዛትድንበር ነው”። እውነታው ይህ ሁኖ ሳለ የማንነት ቀውስ ያለባቸው አንዳንድ የትግራይ ልሂቃን በፈጠራ እኛ እና ብሄረ ትግርኛ አንድ ነበርን ምንሊክ ነው የለያየን የሚል የሐሰት ክስ ያቀርባሉ። እውነቱ ግን ምንሊክ ሳይወለድ በፊት ትግራይ እና ብሄረ ትግርኛ በአንድ ግዛት ኑረው አያውቁም። አንድ ነገድ ሁነውም አያውቁም።

“the Mareb, which forms the boundary between Tigre (sic, Tigray) and the Kingdom of Baharnagash.” ( John R. Miles, P. 131,1846)
በ19ኛው ክፍለ ዘመን ወደ አካባቢው ያቀናው እንግሊዛዊው ፕሎውደን ትግራዮች ብሄረ ትግርኛን እንደ ራሳቸው ነገድ አያዩትም ነበር ሲል ቁልጭ አድርጎ አስፍሩዋል። ” ከ ራስ ሚካኤል ግዜ ጀምሮ የሐማሴን እና ሰራዬ ሕዝብ ከ ትግራዮች ጋር ተመሳሳይ ቁዋንቁዋ ቢናገሩም ትግራዮች በ ብሄረ ትግራይ ላይ ተደጋጋሚ ጦርነት ያደረጉባቸው ሲሆን አንድ ነን ብለውም አያስቡም”

“The people of Hamazain and Serowee, since the time of Ras Michael, though speaking the same language, are still scarcely (hardly) considered by the people of Tigray as a portion of that country whose governors, since that period, have made war on them….” (Walter Chichele Plowden, P. 39, 1868)

ከ እንግሊዝ ጋር ተዋውለው የእንግሊዝን ጦር አቅጣጫ እየጠቆሙ በትግራይ በኩል በማስገባት የባንዳነት ሥራ የሰሩት እና በመቅደላው ጦርነት አፄ ቴዎድሮስ እጅ አልሰጥም ብለው ራሳቸውን ከሰዉ በሁዋላ በእንግሊዞች መሳሪያ እርዳታ ስልጣን የያዙት ብዝብዝ ካሳ ወይም አፄ ዮሐንስ ወደ ባህረ ነጋሽ ጦራቸውን ልከው ከፍተኛ ጭፍጨፋ መፈፀማቸው ይታወቃል። በወሎ እና ጎጃም ሕዝብ ላይ የጅምላ ፍጅት የፈፀሙት በዝብዝ ካሳ ወደ ኤርትራም ራስ አሉላን ልከው ሁለት ሶስተኛ የሚሆነውን የባህረ ነጋሽ ሕዝብ ጨፍጭፈዋል። (, Lyda Favali and Roy Pateman, p. 36, 2003 ) (, Hagai, and Erlikh, p.35, 1996) (Hassan Adem, M.T., Tekle B, 2010)

አፄ ዮሐንስ አደዋ ላይ ከ እንግሊዙ አድሚራል ሂወት ጋር በተዋዋሉት በሕወቴ ውል (Hewett Treaty) መሰረት ለእንግሊዞች አግዘው በመሰለፋቸው ድርቡሾች መተማ ላይ በተደረገ ጦርነት ገለው አንገታቸውን ወስደውታል። አፄ ዮሐንስ ከሞቱ በሁዋላ ራስ አሉላ በምንሊክ ከመገዛት ነፃ የትግራይ መንግስት ለማቁዋቁዋም ለጣልያኖች ከመረብ ማዶ ያለውን ባህረ ነጋሽ እንዲወስዱ ስምምነት ማድረጋቸውን የታሪክ ፕሮፌሰር ጌታቸው መታፈሪያ እና የፖለቲካ ሳይንስ ፕሮፌሰር ጳውሎስ ሚክያስ The Battle of Adwa: Reflections on Ethiopia’s Historic Victory Against European Colonialism በተባለው መፃህፋቸው አስፍረዋል። (Milkias, Metaferia, p.69, 2005)

ትግራዮች ብሄረ ትግርኛን እንደራሳቸው አንድ ነገድ አድርገው እንደማያዩ ራስ አሉላ ከዚህ በታች ለጣልያኖች ያቀረቡት የድርድር ሃሳብ ፍንትው አድርጎ ያሳያል።

”ቤታችሁን ለመስራት እርሻ ለማረስ ቤተክስርስቲያናችሁን ለመገንባት እስከ መረብ ድረስ ሀገር ከፈለጋችሁ ምኒልክ ሳይሆን እኛ ለናንተ እንሰጣችሁዋለን። የጣሊያን ወታደሮች ወደ አድዋ ይምጡ እንደ ወዳጅ አስተናግዳቸዋለሁ” “You want the country to the Mareb (Eritrean highlands/Medri Bahri) to cultivate your gardens, to build your houses, to construct your churches….? We can give it to you. [And not Menilek.] Let the Italian soldiers come to Adwa, I shall come to meet them like a friend.” (1996, Ḥagai Erlikh, P. 164)

ራስ አሉላ እና ሌሎች የ 19ኛው ክፍለ ዘመን የ ትግራይ መሳፍንት ሙሉ በሙሉ ባህረ ነጋሽን ጣሊያኖች እንዲጠቀሙ ነበር የተስማሙት። ብሄረ ትግርኛዎችን እንደ ራሳቸው ነገድ ቆጥረዋቸው አያውቁም።

” እናንት ጣሊያናውያን ለምን እሩቅ ወዳጅ ትፈልጋላችሁ? እኛ ጎረቤታሞች ነን እርስ በርስ መጠቃቀም እንችላለን። መንገድ እንዲከፈትላችሁ ትፈልጋላችሁ እኔም እፈልጋለሁ። እናንተ እስከ መረብ ድረስ ያለውን ጠብቁ እኔም አስቀ ጎንደር እና ከጎንደርም አልፎ ያለውን እጠብቃለሁ። በ እግዚአብሔር እርዳታ ሀገራችንን ትግራይ ለማልማት ወደ ባህሩ ዳርቻ ድረስ በመሄድ መነገድ አለብን። ምኒልክ ሩቅ ነው ለናንተ የሚጠቅማችሁ ነገር የለም። በመካከላችን ወዳጅነት እንመስርት”

“And you (Italians), why do you need to look for distant friends? We are neighbors (meaning Medri Bahri and Tigray) and can serve each other. You want the road to be open and I want the road to be open. You should guard to the Mereb River and I will guard it to Gondar and even beyond Gondar. We must be able to go to the coast to trade in order that our country (meaning Tigray) would flourish, with the help of God, Menelik is too far to be of any use to you. Let us make friendship between us. (1996, Ḥagai Erlikh, 164)”
ቬሮኒካ መላኩ

Post Reply