Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Wedi
Member+
Posts: 8647
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

አሳፍሪው የትግሬ ጅንታ አፍኖ ወስዳቸው የነበሩት ብርጋዴር ጄኔራል አዳምነህ መንግስቴ የሰሜን ዕዝ ምክትል ኦፕሬሽን አዛዥ ነፃ ከወጡ በኋላ የተናገሩት

Post by Wedi » 12 Dec 2020, 11:43



አሳፍሪው የትግሬ ጅንታ አፍኖ ወስዳቸው የነበሩት ብርጋዴር ጄኔራል አዳምነህ መንግስቴ የሰሜን ዕዝ ምክትል ኦፕሬሽን አዛዥ ነፃ ከወጡ በኋላ የተናገሩት

Ethiopian Press Agency /የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት/


“እናትና አባትህ ይክዱኛል ብለህ የማትጠብቅበት አይነት ሁኔታ ውስጥ በሰራዊቱ ላይ ክህደት ተፈጽሟል። ቤታችን ነው ሰላም ነው ባልንበት ቦታ በተደራጀ ሃይል አፈና ተካሂዶብናል”

👉 የጁንታው አመራሮች በቅርበት ይከታተሉን ስለነበር የአየር ሀይላችን እነርሱን ነጥሎ ጠባብ መንገድ ላይ በአየር ድብደባ ተሸከርካሪዎቻቸውን አቃጥሏል፤

👉 የጁንታው አመራሮች ወደኋላ ሲመለሱ ደግሞ ተሸከርካሪዎቻቸውን በመምታት መንገዱ እንዲዘጋባቸው አድርጓል፤

👉 የጁንታው አመራሮች መሄጃ በማጣታቸው የነበራቸውን ተሽከረካሪዎች እና ንብረት እየጣሉና እያንጠባጠቡ ሲበታተኑ መከላከያ ሰራዊታችን ደርሶ አብረውኝ የነበሩትን ሁሉ ነጻ አውጥቷል፤

👉 ሰራዊቱ የታፈኑትን ነጻ ሲያወጣ ጠላትና ወገንን የለየ ምርጥ ኦፕሬሽን አከናውኗል፤

ብርጋዴር ጄኔራል አዳምነህ መንግስቴ
የሰሜን ዕዝ ምክትል ኦፕሬሽን አዛዥ
******************************

(ኢ ፕ ድ)
ሽሬ:- መከላከያ ሰራዊት በጁንታው ታጣቂዎች አማካኝነት የታፈኑትን የሰራዊቱ አመራርና አባላትን ነጻ ሲያወጣ ጠላትና ወገንን የለየ ምርጥ ኦፕሬሽን አከናውኗል ሲሉ ከታጋቾቹ መካከል አንዱ የነበሩት የሰሜን ዕዝ ምክትል ኦፕሬሽን አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል አዳምነህ መንግስቴ ተናገሩ።

የሰሜን ዕዝ ምክትል ኦፕሬሽን አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል አዳምነህ መንግስቴ እንደገለጹት፤ መከላከያ ሰራዊቱ ታጋቾችን እና የጁንታውን ታጣቂ ለመለየት የተጠቀመው እርምጃ የሚደነቅ ነው። የሰራዊቱ አመራርና አባላትን በማይጎዳ መልኩ ጥንቃቄ የተሞላበት ኦፕሬሽን በተሳካ ሁኔታ ፈጽሟል።

"መከላከያ ሰራዊታችን እኛ የታፈንነውን አመራርና አባላት ላይ አደጋ እንዳይደርስ ጥንቃቄ በተሞላው መንገድ እርምጃ ወስዷል። በተለይ የጁንታው አመራሮች በቅርበት ይከታተሉን ስለነበር እነርሱን በሚነጥል ሁኔታ በአየር ከፊት ጠባብ መንገድ ላይ ተሸከርካሪዎቻቸውን አቃጥሏል።

መከላከያ ሰራዊቱ የጁንታው አመራሮች ወደኋላ ሊመለሱ ሲሄዱ ከኋላ ተሸከርካሪዎቻቸውም በመምታት መንገዱ እንዲዘጋባቸው አድርጓል። በዚህ ወቅት የጁንታው አመራሮች መሄጃ በማጣታቸው የነበራቸውን ተሽከረካሪዎች እና ንብረት እየጣሉና እያንጠባጠቡ ሲበታተኑ መከላከያ ሰራዊታችን ደርሶ አብረውኝ የነበሩትን ሁሉ ታጋቾችን ነጻ አውጥቷል" በማለት የሰራዊቱን እርምጃ አወድሰዋል።

ሰራዊቱ የታፈኑትን ነጻ ሲያወጣ ጠላትና ወገንን የለየ ምርጥ ኦፕሬሽን አከናውኗል ያሉት ብርጋዴር ጄኔራል አዳምነህ፤ መላው የኢትዮጵያ ህዝብም ደስተኛ የሆነበት እና ጥሩ ስራ የተከናወነበት ነው በማለት ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። <<መከላከያ ሰራዊታችንን በግሌም ሆነ አብረውኝ በነበሩ አመራሮች ስም ላመሰግን እወዳለሁ። በመከላከያ ሰራዊታችን ኮርተንበታል>> ብለዋል።

በአፈናው ወቅት ስለነበረው ሁናቴ ሲያስረዱም “ስሜቱን መግለጽ ያጥረኛል። እናትና አባትህ ይክዱኛል ብለህ በማትጠብቅበት ሰዓት በሰራዊቱ ላይ ክህደት ተፈጽሟል። ቤታችን ነው ሰላም ነው ባልንበት ቦታ በተደራጀ ሃይል አፈና ተካሂዶብናል” ነው ያሉት።

የአፈናው ጊዜ በሙሉ በርካታ ውጣ ውረዶች ያሉት ነው፤ ረጅም የእግር ጉዞዎች በቀንም በሌሊትም ያለዕረፍት ነበረው። ዞሮ ዞሮ ህይወታችንን ካተረፉን የመከላከያ ሰራዊት ወንድሞቻችን ጋር ሆነን ታሪኩን በጽሁፍ በሰፊው የምናቀርበው ይሆናል በማለት ሁኔታውን በአጭሩ አስረድተዋል።

ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ላይ በጁንታው ቡድን ታጣቂዎች ጥቃት ተፈጽሞባቸው የታፈኑት የሰሜን እዝ መከላከያ ሰራዊት አመራሮች ሽሬ ከተማ ሲደርሱ በሰራዊቱ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። በርካታ የሰራዊቱ አባላት ታፍነው የሰነበቱ አመራሮቹን እና ጓደኞቻቸውን ሲያገኙም ወደሰማይ በተተኮሰ የጥይት ድምጽ እና በጭፈራ ደስታቸውን ገልጸዋል።

ህዳር 30 ቀን ከሰዓት በኋላ የጁንታው ቡድን አጋቾች አዴት በተባለ አካባቢ በእግር ሲያጓጉዟቸው የነበሩትን ከ1ሺህ በላይ የሰራዊቱን መኮንኖች በመልቀቅ በየአቅጣጫው መበታተኑ ታውቋል። ታፍነው የሰነበቱ የሰራዊቱ አመራሮች መንግስት ላደረገው የህይወት አድን ጥረት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በጌትነት ተስፋማርያም


Please wait, video is loading...

Wedi
Member+
Posts: 8647
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: አሳፍሪው የትግሬ ጅንታ አፍኖ ወስዳቸው የነበሩት ብርጋዴር ጄኔራል አዳምነህ መንግስቴ የሰሜን ዕዝ ምክትል ኦፕሬሽን አዛዥ ነፃ ከወጡ በኋላ የተናገሩት

Post by Wedi » 12 Dec 2020, 11:55

Ethiopian Press Agency /የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት/

የህወሓት ጁንታ አፍኖ ወስዶ ሲያንገላታቸው የነበሩ ከአንድ ሺ በላይ የመከላከያ ሰራዊት ጄኔራሎች እና መኮንኖች በሰራዊቱ ጥንቃቄ የተሞላበት እርምጃ ነጻ ከወጡ በኋላ ሽሬ ከተማ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

በአቀባበሉ ስነስርዓት ላይ ይሙቱ ይኑሩ እርግጠኛ ያልነበሩ አመራሮቻቸውን እና ጓደኞቻቸውን ያገኙ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት አገርን፣ ህዝብን እና ሠራዊቱን የሚያወድሱ ዜማዎችን በማሰማት ደስታቸውን በአደባባይ ገልጸዋል። በስፍራው የሚገኘው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘጋቢም ይህንን ሁነት የሚያሳዩ ምስሎችን አድርሶናል።

Please wait, video is loading...

Post Reply