Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum


Hameddibewoyane
Member
Posts: 3890
Joined: 25 Sep 2019, 02:42

Re: ሰበር ዜና፣ ሌ/ጄ ጄኔራል ጻድቃን ገብረትንሳኤን ጨምሮ ከ 40 በላይ የኢትዮጵያ አየር ሃይል፣ ያገር መከላከያና የፖሊስ አመራሮች ላይ የእስር ትእዛዝ ወጣ!!!!

Post by Hameddibewoyane » 11 Dec 2020, 12:07

ሌ/ጀነራል ጻድቃን ገብረትንሳዔን ጨምሮ 40 የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር ሃይል፣ የሀገር መከላከያና የፖሊስ አመራሮች ላይ የመያዣ ትእዛዝ ወጣ። ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው እነዚህ አመራሮች በሀገር ክህደትና የሀገር መከላከያና የፌደራል ፖሊስ አባላት እንዲታገቱ በማድረግ ወንጀል ተጠርጥረዋል። ከህወሀት የተሰጣቸውን ተልዕኮ በመምራት በማስተባበርና በመፈጸም በሀገር ላይ ከፍተኛ አደጋ ያደረሱ በመሆናቸው ለህግ እንዲቀርቡ የእስር ትዕዛዝ የወጣባችው መሆኑ ተመልክቷል። የቀድሞ ኤታማዦር ሹም ሌ/ጀ ጻድቃን ጦርነቱ ከመጀመሩ አንድ ሳምንት በፊት ከሀገር መውጣታቸው ይታወሳል። ፌደራል ፖሊስ እነዚህን ተጠርጣሪዎች አድኖ ለመያዝ በሚደረገው የህግ ማስከበር ዘመቻ ህብረተሰቡ ትብብር እንዲያደርግ ጠይቋል።


Post Reply