Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Wedi
Member+
Posts: 8647
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

"የወልቃይት እና የራያ ህዝብ የተጨቆነው በህውሃት ብቻ አይደለም፤ እኛም ተጨምረን ነው ፍዳቸውን ያበዛነው፣ ለዚህም በተደጋጋሚ ይቅርታ እንጠይቃለን።" - (አቶ ገዱ አንዳርጋቸው)

Post by Wedi » 04 Dec 2020, 03:07

"የወልቃይት እና የራያ ህዝብ የተጨቆነው በህውሃት ብቻ አይደለም፤ እኛም ተጨምረን ነው ፍዳቸውን ያበዛነው፣ ለዚህም በተደጋጋሚ ይቅርታ እንጠይቃለን።" - (አቶ ገዱ አንዳርጋቸው)

የአማራ ህዝብ የታገለው ርስት ለማስመለስ አይደለም። ይህንን Frame የቀረፀልን ህወሃት ነው። ጥያቄያችን ከመሬትና ከርስት በእጅጉ የላቀ ነው። ትግላችን ከሞት የተረፉት ወንድሞቻችን በነብስ እንዲቆዩ የማድረግ ነበር። በህይወት የመኖር አንገብጋቢ ትግል ነው የአካባቢው አማራዎች ያሳለፉት።

የአማራ ህዝብ የተዋደቀውም ከመሬትና ከርስት በላይ የሆኑት የወልቃይት፣ የጠለምት፣ የጠገዴ እና የራያ አማራዎች ነፃ እንዲወጡ ነው። በእነዚህ አካባቢ የሚኖሩ የአማራ ህዝቦች በህውሃት ጭቆና ከሰውነት በታች እንዲሆኑ ተደርገዋል። ጭቆና የሚለው በራሱ አይገልፀውም። ስለዚህ ትግላችን ወገኖቻችንን ነፃ ማውጣት ነው። ሌላው ከወንድሞቻችን ነፃነት በሗላ የሚመጣ ነው።

አሁን እነዚህ አካባቢዎች ነፃ ወጥተዋል። ነዋሪዎቹ አንገታቸውን ቀና አድርገዋል። ከዚያም አልፎ የሚበጃቸውን በአደባባይ እየገለፁ ነው። ነገም ወደሚፈልጉት ይሆናሉ። እኛም ከጎናቸው ሆነን እንደግፋቸዋለን።
ያም ሆኖ የወልቃይትን እና የራያን ህዝብ የጨቆነው ህውሃት ብቻ አይደለም፤ እኛም ተጨምረን ነው ፍዳቸውን ያበዛነው። ለዚህም በተደጋጋሚ ይቅርታ እንጠይቃለን።

(አቶ ገዱ አንዳርጋቸው - በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል በተካሄደው የባለሀብቶች መድረክ የተናገሩት)
ከአለማየሁ አየነው ገፅ ::

Please wait, video is loading...

Wedi
Member+
Posts: 8647
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: "የወልቃይት እና የራያ ህዝብ የተጨቆነው በህውሃት ብቻ አይደለም፤ እኛም ተጨምረን ነው ፍዳቸውን ያበዛነው፣ ለዚህም በተደጋጋሚ ይቅርታ እንጠይቃለን።" - (አቶ ገዱ አንዳርጋቸው)

Post by Wedi » 04 Dec 2020, 04:39

ሕገ መንግሥቱ የፀደቀው በ1987 ነው። ወልቃይትና ራያ ወደ ትግራይ በኃይልና በፖለቲካ ውሳኔ ወደ ትግራይ የተካለሉት ግን በ1982-83 ዓ.ም ነው። ታዲያ ዛሬ ወልቃይትንና ራያን ወደ እናት ምድራቸው ወደ አማራ ለመመለስ "በሕገ መንግሥቱን አሰራር ተከትሎ" ይታያል የሚል ማደናገሪያ አይሰራም።

ሲጀምር መች በሕግ ሄደና ነው በሕገ መንግስቱ አሰራር የሚመለሰው ሕገ መንግስት ሳይፀድቅ እኮ ነው በሀይል የተወሰደው የነበር።

አቶ ላቀ አያሌው አንተነህ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ሚኒስተር
Please wait, video is loading...

Post Reply