Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Ejersa
Member
Posts: 3978
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

የማይካድራው ጭፍጨፋና አቶ ተክለወይኒ!

Post by Ejersa » 24 Nov 2020, 16:26

ገዳዮቹ ወይም ጨፍጫፊዎቹ ...

የልብ ልብ ተሰምቷቸው እንዲደፋፈሩና እንዲጨክኑ አስፈላጊ ስለነበረ አማራዎቹን ከመግደላቸው በፊት መጠጥ ጠጥተው መስከር ነበረባቸው ።

በመሆኑም እነዚህ የጨፍጫፊው ቡድን አባላት ሃወልቲ ከተባለው ሰፈር ጀምሮ ግጀትና ግምብ ሰፈር በሚባሉ ሰፈሮች በሚገኙት ቡና ቤቶች እየዞሩ ሲጠጡ አመሹ።

የቡና ቤቱ ባለቤት አማራ ከሆነ የተጠጣው መጠጥ ሂሳብ አይከፈልም ነበር።ገዳዮቹ ፍሪጅ እየከፈቱ ያሻቸውን እንዳሻቸው አየጠጡ ከሰከሩ በኋላ ለመግደል ዝግጁ ሆኑ ። (ለነገሩ አማራው የቡና ቤት ባለቤት የዛኑ ዕለት ሌሊት ላይ መገደሉ ላይቀር ነገር ቤቱ ውስጥ ለተጠጣው መጠጥ ሂሳብ ተከፈለው አልተከፈለው ምንም አይፈይድለትም)

ታዲያ በጊዜው የገዳዮቹን ቡድን ሰብስበው የአልኮል መጠጦችን ሲጋብዙ ካመሹት ግለሰቦች መካከል ትናንትና የተገደለው ተክለወይኒ የተባለው የወያኔ ሰው ዋነኛው ነበር። ማይካድራ ውስጥ የራሱ ሆቴልም ነበረው ።