Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42313
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የትህነግ እስትራተጂክ አላማ ምንድን ነው? ዛሬም እንደ ድሮ የለውም !

Post by Horus » 06 Nov 2020, 15:50

አንድ፣
አዲስ ነጻ ተገንጣይ የትግሬ አገር ለማቆም ከሆነ ያን ማድረግ የሚችለው ድሮ ነበር ። ይህ የማይቻል አላማ ነው ።

ሁለት፣
የኢትዮጵያ ማዕክላዊ መንግስት መልሶ ለመያዝ ከሆነ ላለፉት 3 አመታት ሞከረ፤ ማድረግ በሚችልብት ግዜ። አልቻለም፣ የማይቻል አላማ ነው።

ሶስት፣
የራሱን ክልል የጦር ሃይል ለመገንባት ከሆነ ለምን አላማ? የጦር ሃይል ምን ሊያርግበት? በጎሬላ ጦርነት እንደ ገና አዲስ አበባን ለምያዝ ከሆን ያም የማይቻል አላማ ነው ።

አራት፣ ራሱን የትግሬ ገዢ መደብ (መንግስት) ሆኖ ለመቀጠል ከሆነ ማናልባት፤ ግን ያ ሚሆነው በኢትዮጵያ ሕግ ስር ነው። ወንጀለኞችን በማስረክብ ነው ።

አምስት፣
አገር አቀፍ ሲቪል ጦርነት ለማስነሳት ከሆነ በቁጥር 2 ሞክሮ ያቃተው ነገር ነው ።

ስለዚህ ዎያኔ ልክ እንድ 1975 ዛሬም ከስኬት የሚደርስ አላማ የለውም። ያለው ያው የድሮ የሰካራም ራዕይ ነው ።

Horus
Senior Member+
Posts: 42313
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የትህነግ እስትራተጂክ አላማ ምንድን ነው? ዛሬም እንደ ድሮ የለውም !

Post by Horus » 06 Nov 2020, 16:30

ስድስት፣

የዎያኔ ደጋፊዎች ሺ ግዜ እንዳሉት የትህነግ አላማ ትግሬን ደፋክቶ እስቴት አድርጎ ለመኖር ከሆነ አሁን ምላሽ እያገኘ ነው ። ትግሬን ሙሉ በሙሉ ከብቦ በመነጠል፣ ከውጭ ወደ ውስጥ ምንም እንዳይገባ፣ ከውስጥ ወደ ውጭ ምንም እንዳይወጣ በመዝጋት፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የያዘው ንብረት ወርሶ፣ መረቡን በጣጥሶ በኦክሲጂን እጦት መግደል ነው ። ያለ ምንም ጦርነት ማለት ነው ። ያንን ነው የስካራም ራዕይ ያልኩት ።

Post Reply