Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

Guest1
Member
Posts: 1926
Joined: 28 Dec 2006, 01:02

Re: ኦሮሞኛ ሚናገሩት የሌማን ጉራጌዎች ሲደሰቱ!!

Post by Guest1 » 22 Oct 2020, 08:47

H
በቅድሚያ ሶዶ ጉራጌ ኦሮሞና ጉራጌ ነው ሲባል ስምቻለሁ። ኦሮምኛ ተናጋሪ ሆኖ በጉራግኛ የሚጨፍር ሳይ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ጭፈራው የትግሬይ እጅ ውርወራም የአማራ እስክስታም አለበት ክክክክክክክክክክክክክክ ባለማውቄ መሳቅ ይፈቀድልኝ
መጠየቅ የፈለግኩት
ሌማን ምን ማለት ነው? ትርጉሙን ብትነግረን።

Horus
Senior Member+
Posts: 40426
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ኦሮሞኛ ሚናገሩት የሌማን ጉራጌዎች ሲደሰቱ!!

Post by Horus » 22 Oct 2020, 17:25

Gust 1
እንደ ምታውቀው ጉራጌ በምዕራብ ፣ በሰሜን እና ምስራቅ የተከበበው በኦሮሞ ነው ። ክ16ኛ ዘመን ጀምሮ ብዙ የጉራጌ መሬቶችና ጎሳዎች በኦሮሞ ተውጠዋል ። ሌላው ቀርቶ ባዲስ አበባ ዙሪያ ያሉት ገላኖች የጥንት ጉራጌዎች ናችው ። እዚህ ዘፈን ላይ ልጁ የሚዘፍንለት ከአዋሽ በፊት ያለው ሌማን የሚባለው ወንዝ ነው፣ ከበቾ ወደ አዳዲ ያለው ። ሌማን ላይ መልካ ቁንጡሬ የሚባል እጅግ የጥንት አርኪዮሎጂካል ሳይት አለ ። እነዚህ ኦሮምኛ ተናጋሪ (ብዙዎቹ ጉራጌኛም ይናግራሉ) እንደ ምታይው በጥንት ውላጆቻችው ባህል ይኮሩበታል ። ድሮ የጉራጌ ድንበር አዋሽ ወንዝና ዝዋይ ሃይቅ ነበር ። የዚያ አካባቢ ሕዝብ ሁሉ ይህ ነው ግንዱ ።

http://www.melkakunture.it/melka/index.html


Post Reply