የትግራይ ነፃ አውጪ ተብዬ የአንድ ቁዋንቁዋ ተናጋሪዎች ሥልጣን:ገንዘብ: ወታደራዊ ሃይል: ስለላ በአጠቃላይ የአንድ ህብረ ብሄራዊ አገርን ጠቅላላ ማንነት እና የአገር ባለቤትነት በመንጠቅ 27 አመታት ቅኝ ግዛት በሚመስል ስርዓት ውስጥ ካኖራቸው በሁላ በህዝቦች ትግል ተገፈቶ ከወደቀ እነሆ ሁለት ዓመታት አለፉ::
ዛሬ ኢትዮጵያኖች በታሪካቸው አይተው በማያውቁት ትሁት እና አዋቂ መሪ ጋር ኑሮአቸውን ለማሻሻል ጥረት የሚያደርጉበት አንገታቸውን ቀና አድርገው ትልቅ ተስፋ ሰንቀው የሚንቀሳቀሱበት ወቅት ላይ ናቸው:: የተሸናፊው ዘረኛ እና ዘራፊ ቡድን የሳይበር ተዋጊዎች የራሳቸውን እና የአለቆቻቸውን የበላይነት እና ጥቅም ለማስመለስ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም: አገሪቱን የሚፈርስም ቢሆን! ነገር ግን አይሳካላቸውም:: የኢትዮጵያ ህዝቦች በብሄር ብሄረሰቦች ስም ለሰላሳ አመታት ያህል የአንድ ጎጥ ወሮበላዎች የፈፀሙባቸውን ማጭበርበር: ዘረፋ: እና መከፋፈል: ግድያ እሰራት እንዲሁም መሳደድ ከቶ አይረሱትም እንዳይደገምም ነቅተው በመጠበቅ ላይ ናቸው: በህዝቦች ላብ እና ደም ባለስልጣኖች የሚፋፉበትን ዘመን እንዳይመለስ ሁሉም ተግቶ እየሰራ ነው:
የአዞ እንባ አፍሳሾች ለራሳችሁ አልቅሱ! በእውነትም ናላችሁን እስክትስቱ ድረስ ለራሳችሁ እያለቃቀሳችሁ መሆኑን እንረዳለን::