Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 40411
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ሺመልስ አብዲሳ፤ ሰክሮ የነገረህን፣ ቸግሮት የጠየቀህን አትርሳ እንዲሉ !!

Post by Horus » 02 Oct 2020, 15:49


እኔ ደጋግሜ እንዳልኩት ይህ ሺመልስ ሚባል ሰው ለኦሮሞ መሪነት አይመጥንም ብያለሁ ። አንድ ቀን መነሳቱ አይቀሬ ነው ። ለምን በሉ?

አንደኛ ኦሮሞ ካቢይ የተሻለ መሪ ሊያገኝ አይችልም ።

እንደ ሺመልስ ከሆነ ኦሮሞ ስሜት እንጂ እስትራተጂ የለውም። ሺመልስ ያንን ያንደኛ ደረጃ ፍልስፍና ተብዬ ሲማር ያላወቀው ግዙፍ ፋክት፤ ኦሮሞ የሚኖረው በኢትዮጵያ ውስጥ መሆኑን ነው።

ይህን እጅግ እጅግ መሰረታዊ እውነታ ማይገነዘብ እንዴት ሆኖ የኦሮሞ መሪ ይሆናል? ትልቁ አሳዛኝና አሳፋሪ ነገር ያ ነው ።

ከምኞት ያለፈ አንድ እርምጃ የማይወስድ እስትራተጂ የሌለው ኢትዮጵያን ስለመርዳት አፍሪካን ስለማረጋጋት ሲቀባጥር ከመስማት የላቀ ድራማ የለም ።

የቀድሞ አቤ ጉበኛ በሰይፈ ነበልባል ንግግሩ 'እንዴት አንድ የከብት እረኛ የሕዝብ መሪ ይሆናል' ብሎ ነበር ።