Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Wedi
Member+
Posts: 8601
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ""ህወሃትን "የቀን ጅብ" ብሎ ሲሳደብ የነበረው የአብይ አስተዳደር "የተራበ ጅብ" ሲሆን ማዬት ያሳፍራል"

Post by Wedi » 19 Sep 2020, 05:26

"ህወሃትን "የቀን ጅብ" ብሎ ሲሳደብ የነበረው የአብይ አስተዳደር "የተራበ ጅብ" ሲሆን ማዬት ያሳፍራል" :lol: :lol: :lol: :lol:

(ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም)
==========================
የአብይ አስተዳደር አይነተኛ መገለጫው ፍጥጥ ያለ አይነ ደረቅነት እየሆነ ነው! ይህ ህሊና ቢስነት ነው!

በእርግጥ ስህተቶቹም ሆነ የባለስልጣናቱ አይነ ደረቅነት ከግብረ ገብ ችግር የመነጩ አይደሉም፤ በሁሉም ልብ ውስጥ የተቀበረ #ኦሮሙማ የሚባል ለአንድ ብሄር የመቆም ዝንባሌ ስላለ እንጂ።
ህሊና ቢስ መሆናቸው የሚገለጥባቸው የሄዱበትን ዘረኛ አካሄድ ከተሰጣቸው ሃላፊነት ጋር ለማስማማት የሞከሩ ጊዜ ነው። ኦሮሙማ ሁሌም ወንጀል ሲሰሩ በህሊናቸው ምትክ መንፈሳቸውን የሚያስታምሙበት ሚዛናቸው ነው!

ለአንድ ቡድን ተጠቃሚነት ሲሉ የሰሩትን ወንጀል በዚህ መልኩ ትክክለኛና የሚያኮራ ስራ አድርገው ማውራት ይጀምራሉ። ነገር ግን ይህ ህገ ወጥነት ነው፤ አደራን መብላት ነው፤ እምነትን ማጉደል ነው፤ ህዝብን መስደብና መናቅ ነው።

~~
እየሆነ ያለው ነገር አስቂኝም አስደናቂም ነው። ህወሃትን "የቀን ጅብ" ብሎ ሲሳደብ የነበረው የአብይ አስተዳደር "የተራበ ጅብ" ሲሆን ማዬት ያሳፍራል። በአይናችን እያዬን የሚፈፀመውን በደል እንኳን እንደሚኮራበት የሚናገር አይነ ደረቅ ሆኖ አረፈው።

የአብይ አስተዳደር አይነተኛ መገለጫው ፍጥጥ ያለ አይነ ደረቅነት እየሆነ ነው። ለምሳሌ፦ አማራንና አማርኛን የሚያጥላላ ንግግር ይናገርና "አማራና ኦሮሞ ደም ቅዳ ደም መልስ ነው" ይላል። "አማርኛ እንዲዳከም እየሰራን ነው" ባለበት አፉ "አማራና ኦሮሞን ለመነጣጠል የሚደረገው ሙከራ አይሳካም" ሲል እንሰማዋለን። "ነፍጠኛን ሰብረነዋል" ካለ በኋላ "የአማራ ህዝብ ወንድም ህዝብ ነው" ይላል።

ሌላው ቀርቶ በቅርቡ የተጋለጠውን የቤትና የመሬት ህገወጥ ወረራ የቀድሞው ከንቲባ እንደሚኮራበት በግልፅ የተናገረውን አንረሳውም። የሰራው የሚያስጠይቅ ወንጀል መሆኑን እያወቀ እንኳን "ወረራው ትክክል ነው፣ ህገ ወጥ ስራ በመስራቴ እኮራለሁ፤ እንዳውም ብዙ ወንጀል ባለመስራቴ ይቆጨኛል" ሲል ተናገረ። ተቋማቱ በሙሉ ስለ ፍትህ አይጠይቁም፤ በፊት የነበሩ ተቋማት ሳይቀሩ በልምሻ የተመቱ ይመስል እንዳለ ሽባ ሆኑ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሳይቀር በህግ እንዲጠየቅ ወይም ሌላ አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድበት ማድረግ ሲገባው ጭራሽ የሌላ ዘርፍ ሚኒስትር አድርጎ ሾመው። አስተዳደሩ "ብዙ ያጠፋ ብዙ ይሾማል" በሚል ብልሹ የማፊያ መርህ የተቃኘ ሆኗል።

የአብይ አስተዳደር ወጣ ወረዱ በዚህ ህሊና ቢስነት የተጠመቀ በመሆኑ እንጂ በኦሮምያ ክልል የዘር ፍጅት ጥሪን "ሀ" ብሎ የጀመረውና። በቅርቡ ግልፅ የጥላቻ ንግግር የተናገረው ሽመልስ አብዲሳ እና አዲስ አበባ ላይ ያን ያህል በደል የፈፀመው ታከለ ኡማ ለህግ መቅረብ ነበረባቸው። ዳሩ ግን አስተዳደሩ ከህግ በላይ፣ አመራሮቹም ህገ ወጥ ናቸውና ጥፋታቸውን እንደያሳፍራል የሚናገሩ ህሊና ቢሶች ሆኑ።
ያሳፍራል!

ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም

DefendTheTruth
Senior Member
Posts: 12909
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

Re: ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ""ህወሃትን "የቀን ጅብ" ብሎ ሲሳደብ የነበረው የአብይ አስተዳደር "የተራበ ጅብ" ሲሆን ማዬት ያሳፍራል"

Post by DefendTheTruth » 19 Sep 2020, 16:37

Maxi,

this post is suspicious and in case it is indeed an attempt to insinuate the Prof. then there is no one more a suspect than the demons of so called 360 something entity.

In case this post is a fabrication in the name of the Prof., then it also shows how much those guys have already entered their final chapter on the road to their demise.

It simply doesn't correspond to the spirit of what the Prof. said just recently in a video interview with a media outlet called Abay Media or so, the post is somewhere in the forum already.

And I don't think the Prof. is such a personality who would keep changing his opinion in so short time, for he is a man of self-esteem and who cares for his own integrity and credibility.

I am not trying to suggest that he is not entitled to his personal opinion at any time, I am trying simply to highlight that the spirit of the two messages don't match up.

So, try something else.

Wedi
Member+
Posts: 8601
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ""ህወሃትን "የቀን ጅብ" ብሎ ሲሳደብ የነበረው የአብይ አስተዳደር "የተራበ ጅብ" ሲሆን ማዬት ያሳፍራል"

Post by Wedi » 19 Sep 2020, 17:17

ይህን አዳምጠኸዋል? :P :P
Wedi wrote:
09 Sep 2020, 18:38
ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማሪያም ኢትዮጵያ ውስጥ "መንግስት የሚባል ነገር የለም" አሉ!!! :roll: :roll: :roll:

DefendTheTruth wrote:
19 Sep 2020, 16:37

Post Reply