Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abaymado
Member
Posts: 4594
Joined: 27 Sep 2017, 21:56

ውይ ውርደት!

Post by Abaymado » 10 Sep 2020, 12:26

ከአሲማባ ፖርቲ የተሠጠ መግለጫ
ዓዴፓ "የትግራይን 6ኛ ምርጫ" የተባለውን የከሸፈ ምርጫ ውጤት ሙሉ በሙሉ እንደማይቀበል ከወዲሁ ያስታውቃል::
ዛሬ ጥዋት ማለትም ጳጉሜ 5/2012 ዓም ባሳወቅነው መሰረት በክልሉ በርካታ ኣካባቢዎች ላይ መቐለ ከተማን ጨምሮ
1. ከፍተኛ የምርጫ ኮሮጆ ግልበጣ ተካሂዷል፣
2. የምርጫ ኣስፈፃሚዎችንና የምርጫ ታዛቢዎቻችን ታስረዋል፣
3. በምርጫ ተወዳዳሪዎቻችንና ደጋፊዎቻችን ላይም ከፍተኛ የሆነ እንግልት እየተፈፀመ ይገኛል፤ በዓዲግራትና ኣክሱም ከተሞች ደግሞ ድብደባና እስራትም ነበር::
በመሆኑንም እነዚህንና መሰል የምርጫ ውጤት የሚያስቀይሩ ተግባራት በተፈፀሙበትና እየተፈፀሙ ባሉበት ሁኔታ የምርጫውን ውጤት ለመቀበል ኣስቸጋሪ ስለሆነብን፣ ውጤቱን ከወዲሁ እንደማንቀበል ማህበራዊ መሰረታችን የሆነው ህዝባችን በተለይም ደጋፊዎቻችን እንዲያቁልን ጥሪ እናቀርባለን:: በተጨማሪም በድህረ-ምርጫ ግምገማ ላይም መገኘት እንደማንችል እንገልፃለን:: ይሁን ብለን በሒደቱ ብንቀጥል እንኳን ለህዝብ ድምፅ (በተለይም ለኢሮብ ህዝብ ድምፅ) ዋጋ ኣለመስጠት ይሆንብናል::
ጳጉሜ 5/2012 ዓም
ዓሲምባ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
ዓዲግራት ኢሮብ