Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42237
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ሲዳማ ሲወጣ የደቡብ ክልል ፈረሰ፣ ትግሬ ሲወጣ የክልሎች ፌዴሬሽን በሞላ ይፈርሳል፤ ለዚህ ነው ኤትኖክራሲ በኢትዮጵያ መፍረስ ያለበት

Post by Horus » 07 Sep 2020, 16:00

ልብ በሉ አሁን ስዉ ሁሉ አይኑ ያንድ ብሄር መገንጠል ላይ ስላቶከረ የሚሆኑት ነገሮችን ትርጉም በትክክል ማንበብ ወይ መገንዘብ ረስቷል ። ሲዳማ ከደቡብ ክልል ወጥቶ ራሱን ክልል ካደረገ በኋላ ደቡብ የሚባል ክልል (ደቡብ የሚባል የፖለቲካ ኤንቲቲ) የለም፣ በቃ! አሁን ሁሉም ወዴት እንደ ሚሄዱ ግራ ገብቷቸው ዝም ብለው ይታመሳሉ ። በድሮው ምትክ አዲስ የፖለቲካ እንቲቲ አልተፈጠረም ። የደቡብ መፍረስም በተዘዋዋሪ አገር አቀፍን የክልሎች ፌዴሬሽን አፍርሶታል።

ነገ ጳጉሜ 4 ትግሬ ከቀረው አገር አቀፍ የክልሎች ፌዴሬሽን ወጥቶ የራሱን ምርጫ አድርጎ መንግስት ይመርጣል ። ልክ ያ ሲሆን ለ29 አመት የነበረው አገር አቀፍ ፌዴሬሽን ከደቡብ ቀጥሎ ያፈርሰዋል ። ከዚያ በኋላ አዲስ እንቲቲ ካልተፈጠረ በቀር የድሮ እስትራክቸር ዲፌክቲቭ የሆነ በመሰረቱ የፈረሰ ተቋም ነው የሚሆነው ።

የዚህ ሁሉ ትርጉም መሆን ያለበት ይህ ነው። ብልጽኛም ሆነ ሌሎቹ ናኡስ ክልሎች፣ ኢዜማም ሆነ ሌሎች ፓርቲዎች ይህ መላ ቅጡ የጠፋው የክልል ጽንሰ ነገር ወዲያ በመርወር አዲስ ፌዴርሽ የሚያቆም ጉባኤ መጥራትና ለዘር ፖለቲካ ላንዴም ለሁሌም መፍቴ ማቅረብ ያለው ታላቅ ግዲታ ነው።

በኢትዮጵያ አንድም ክልል ተገንጥሎ አገር አይሆንም ። ያንን ተረት በመርሳት እውነተኛን በሽታ ማከሚያ ግዜው አሁን ነው ።