ባለፉት ሀለት ዓመታት የአዲስ አበባ ም/ከንቲባ ያሻውን ሲያደርግና ጎበዝ ብለው ሲያጨበጭቡ ከርመው። ከዛም አልፎ እንደ እነ እስክንድር አይነቶቹ ሲቃወሙ፣ ውሻ በበላበት እንዲሉ፣ ብርሃኑና ኢሳቶች ከከንቲባው ጋር በመወገን ሲያጥላላቸው፣ ስብስባዎቻቸውንና የፕሬስ ኮንፍሬሶቻቸውን ሲያስርዙና ሲያስበትኑ ከርመው፣ ባላንጣ ናቸው ብለው ሁሉንም እስር ቤት ካጋዙ በህዋላ፣ አሁን ሜዳው የእኛ ነው ብለው ሌላ ትርክት ብርሃኑ ከሽሽበት ከአሜሪካ ይዞ ብቅ ብልዋል። የአዞ እንባውንም በሙሾ አውራጆቹ ኢሳቶች ያነብንበዋል።
የአዲስ አበባም ህዝብ ሞኝ አይደለም እንክዋን የብርሃኑና ጀሌዎቹ ሽፍጥ ይቅርና ጠማማ ዝንብ አይተው ያውቃሉ። እድሜ ለአብይ ሙሉ የመንግስት ድጋፍ ወጪ ጭምር ሽፍኖ የእሱ አሻንጉሊት አድርጎ ይዝዋቸዋል። ዞሮ ዞሮ ግን ብርሃኑ አጉል ብልጥ ነኝ ብሎ ስለሚያስብ በአብይ ተንጠልዬ ለስልጣን እበቃለሁ ብሎ ስለሚያስብ ለእራት ያስበው አብይ ለቁርስ እንደሚያደርገው በቅርብ እናያለን። እሱም ብርሃኑና የኢሳት ጋዜጠኞች ከሽሽት ወደ ሀገራቸው ከተመለሱ ነው። ቸር ያቆየን ገና ብዙ ጉድ አለ። የአጭበርባሪዎች አጭር ዘመን ናት። ያልፋል።
Re: ጅብ ከሄደ ውሻ ጮሃ ነው የብርሃኑ ነጋና ኢዜማ የውሽት ለቅሶ
ቄስ ሞገሴ /ብርሃኑ ነጋ!! አያ አሻጋሬ!! "አብይ፣ ለማ፣ ታከለ... ያሻግሩናል.."

Please wait, video is loading...