የ1960ዎቹ አነብናቢ ፊዴል በቃኝ የእነ ዋለልኝ መኮንን መሬት ለአራሹ ጥያቄ ኢትዮጵያን የገበሬዎች አገር ብቻ ማድረግ ነበር - ማዘመን አልነበረም።
የ1960ዎቹ አነብናቢ ፊዴል በቃኝ የእነ ዋለልኝ መኮንን መሬት ለአራሹ ጥያቄ ኢትዮጵያን የገበሬዎች አገር ብቻ ማድረግ ነበር - ማዘመን አልነበረም።ብዙዎች ኢህአፓ ፣ወያኔ ፣ ወዘተ ነን የሚሉ የዚያ ትውልድ ወገኖች የምጣኔ ሃብታዊ ፋይዳ እና እውነታ ሳይሆን መሬት ነፍስ ወከፍ በቤተሰብ አባል ማካፈል ዕድገት ያመጣል ብለው ያሳቡ ነበር። በመርህ ደረጃ መልካም የሞራል እሳቤ ቢኖረውም አርሶ አደሩን መሬት ላይ ተለጥፎ ከመኖር እንዴት ወደ ዘመናዊ ሰፋፊ እና ሜካናይዝድ ግብርና እንዱም በኢንዱስትሪና አገልግሎት ዘርፍ ሊሰማራ እንደሚችል ጭራሽ በህሌና አንቴናቸው ዘወር አላለም። ይበልጡንም የነበረውን ነባር የመሬት ይዞታ ባህል ብጥስጥሱን በማጥፋት አገሪቱ እስከ ዘለዓለም ወደ ዘመናዊ ኢኮኖሚ እንዳትሸጋገር በሩን ጥርቅም አድርጎ ዘግቷል። ምናልባት የወፈፌዎቹ የነዋለልኝ ዘመን - ሁሉ አረሰ ማን ይሸምት ይሆን የሚለው ብሂል ይሆን መሬት ለአራሹ እያሉ ገበሬውን መሬት ዐልባ ብቻ ሳይሆን ተቀፍድዶ unskilled labor እንድሆን የተፈረደበት።የ1960ዎቹ የመሬት ለአራሹ ትሩፋት የሆነው አርሶ አደሩ በመኸር ወቅት ሳይቀር የነቀዘ ስንዴ እና በቆሎ በቋሚነት ተረጅ መሆን ነው። ያከንቱ 60ዎቹ ትውልድ በዚህም ልክ የጎሣ መርዝ ዘርተው አሁን የ genocide ምርት እንደሚታፈሰው በእዚህም ይኮራሉ:: I will count their death and wasteful sacrifice as sunk-cost in history.