Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 40355
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

2 የጉራጌ ወጣቶች ባህል ላሳያችሁ

Post by Horus » 25 Aug 2020, 03:30


ነጆ አራጆ፣ ዝላይ ወይም ኩስ የምንለው የጎረምሶች ዝላይ (አትሌቲክ ችሎታ) የሚጠይቅ ጨዋታ በመስክረም እና ጥቅምት ብሎም የገና (አንቃት) ጨዋታ እስከ ሚጀምር የሚድረግ የወጣቶች ባህል ነው ። የችሎታው መለኪያ የቆመው ሰው ራስ ሳይነኩ ዘሎ ማለፍ ነው ። በፈረንጅ ሃይ ጃምፕ ወይም መሰናክል (ሀርድልስ) እንደ ሚባለው ማለት ነው።





የገና ጨዋታ በሁሉም እድሜ ልጆችና ጎረምሶች በያንስ ለ2 ወር እስከ ገና ቀን ድረስ እረኛ ሁሉ የሚጫወተው ከልደት ጋር የተያያዘ ባህል ነው። ስሙ በሰሜን ጉራጌ አንቃት ይባላል ። ያንቃት መዝጊያ የገና ቀን ቤተስኪያን መልስ አገሬው ሜዳ ወርዶ ቀበሌና ቀበሌ እየተጋጠመ አሸናፊው ቲም አንቃቱን (ጥንጉን) ወደ መንደሩ ካስገባ ያ ቡድን ያሸንፋል ። ለምሳሌ አማዉቴ ውስጥ ከባሎልድ ክብር መልስ ሰው ሁሉ ሶሶቱ ይወርድና ግጥሚያ በእንጀሪና ወተደር መሃል ሆኑ ሲመሽ አካባቢ አንዱ ያሸንፋል ። ዛሬ ወጣት ሁሉ ባላገር ስለሌለ ባህሉም ሊረሳ ደርሷል