ኮቪድ 19 VS ኮቪድ 19...
የሳዋ አነሮች እንደልባቸው እየተቃቀፉ ሲደንሱ፤ ተያይዘው ሲቦርቁ፤ አንገት ላንገት ተናንቀው ሲሳሳሙ ማየት አጀብ ያሰኛል'በሳዋ ምድር ' ኮቪድ 19 ከራሱ ጋር ይታገል እንደሆነ እንጂ መግብያ የለውም።
ድሮስ ቢሆን ቀውጢ ጦርነት መሃል የራሳቸውን ከአለም ላይ በርዝመቱ የሚታወቀውን ኦሮታ ሆስፒታል የገነቡ ዶክተሮች እኮ ናቸው፡፡ አቤት ሌላው ቢሆን እንዴት አድርጎ በጻፈው? እንዴት ከሽኖ ባወራው ? እኛ ደመ መራራ ሆን እንጂ ስንት ሽልማት ባስገባን ? ያቺ መሬት አቀማመጧ ጦስ ሆኖብን ስንጠብቃት ስንት ወርቃማ ጊዜያቶች አለፉ? ቁጭ ብለን ሳናወጋ ስንት ሌሊቶች አመለጡን ? ድል በድል እየተደራረበ ማየት እስኪሳነን የተሸፈነብን ታሪክና አሻራው ጊዜ ይገልጠው ይሆን ?
እንዲያም ሆኖ መወቀስ ካለብን እራሳችንን እንውቀስ፡፡ ሌሎች የሚዘባበቱበት ታሪካችንን አጉልተን ማውጣት አቃተን፡፡
አፋቸውን ለጉመው የሚለፉት፡ ጊዜ ለራሱ ሲል ስለሚያወጣው እውነታቸው፡ እኒያ ጀግኖቻችንን ለዘላለም ይክበሩልን፡፡ አዎ ጊዜ ከኛ ተሽሎ መሰተዋት ሆኖ አሳይቶናልና !
ኮቪድ 19 ሙሉ አለምን አናግቷል፡፡ የጅምላ መቃብር፤ የምግብ እጥረት፤ ከአንድ ቤተሰብ ጀምሮ እስከ ታላላቅ ሃገራት የኤኮኖሚ ድቀት፤ በጠቅላላ ርህራሄ የሌለው የአለማችን ከባድ ክስተት ሆኖ አሁንም ጠብ ያለሽ በዳቦ እያለ ሰው መቅዘፉን ቀጥሏል፡፡
ታዲያ በዚህ የዘመናችን አስፈሪ ቅጽበት፡ ሳዋ ላይ በኮቪድ ጊዜ በአለም ላይ የመጀመሪያው በአካል ተገኝቶ ምረቃ ተካሂዷል፡፡ ምን በአካል መገኘት ብቻ የሳዋ አነሮች እንደልባቸው እየተቃቀፉ ሲደንሱ፤ ተያይዘው ሲቦርቁ፤ አንገት ላንገት ተናንቀው ሲሳሳሙ ማየት አጀብ ያሰኛል፡፡
አቤት! መጨረሻ ላይ የዘፈነው ያ ተንከሲስ ልጅ ጉሮሮዉን እዛው ሳዋ ላይ ገጠመውለት ነው እንዴ? What an attitude??? ማንን አስታወሰኝ መሰላችሁ ? እነዛ ኤርትራ ኮቪድን መቋቋም ትችላች ወይ ብለው ሲያንጓጥጡ የከረሙት መልሳቸውን አግኝተው ይሆን ? በተለይ ያ ፕሮፌሰር ዓወት ወ/ ሚካኤል የሚባለው " የኤርትራ የኮቪድ 19 ታስክ ፎርስ እነማን ናቸው?'' ብሎ ሲወጣጠርና ትእዛዝ ሲሰጥ የከረመው!
it’s unclear who’s running [#Eritrea](https://www.facebook.com/hashtag/eritre ... tn__=-UK-R) during this Covid-19 pandemic. z country needs robust inter-ministerial taskforce on Covid-19 led by capable professionals
ይኸውልህ! ታስክ ፎርሱማ እንዳንተ ቆሌ በየደቂቃው ወረቀት ላይ የሚለቀልቅ ቃልቻ አደለም፡፡ ስውር መንፈስ ነው፡፡ በስውር ከኮቪድ በታች ረግጦህ ጭንቅላትህ ላይ በዋርሳይ ሙዚቃ ጨፈረብህ፡፡አታያቸውም፡ አትዳስሳቸውም የግዳስ ገና ያሳብዱሃል፡፡ Any more question ?
ለሁሉም በሳዋ ምድር ኮቪድ 19 ከራሱ ጋር ይታገል እንደሆነ እንጂ መግቢያ ቀዳዳ እንደተነፈገው በግልጽ ይታያል፡፡
ሳዋ የገቡት መሪዎቹ ብቻ ማስክ አደረጉ ብላችሁ ያለቃቀሳችሁ ድኩማኖች እንዲህ እንላችኋለን፡ ሳዋ ከኮቪድ 19 ነጻ ከተማ ናት፡፡ ከሌላ ቦታ የመጡ ሰዎች በታስክ ፎርሱ ህግ መሰረት ሙቀት ብቻ ተለክተው አደለም ተመርምረውና ማስክ አድርገው ነው የሚገቡት፡፡ በሳዋ ምረቃ ታሪክ ውስጥ ተመራቂዎችን ለመጀመሪያ ጊዜ በሩቁ ሰላም ያለው ፕሬዝደንት ኢሳያስ ለጥንቃቄ ነው፡፡ ተመራቂዎችም እንደድሮ ለሰላምታ አልከበቡትም፡፡ ይኸው ነው፡፡ከዚህ በተረፈ፡ አፋቸውን ዘግተው ምን ይሰሩ ነበር የሚለውን ማየቱ ደሞ አስፈላጊ ነው፡፡በህክምና ከድህረ ታሪካቸው ብንነሳ፡
By Thomas Keneally
Sept. 27, 1987 በኒው ዮርክ ታይምስ ካሰፈረው ረጂም ሃተታ፡ ጥቂት መስመር መነሻ አድርገን እንወያይ፡፡
Orotta is an extraordinary hospital, a vast series of bunkers and caves that extend almost five miles down a harsh valley. The hospital is arranged according to the standard Western administrative pattern, with bunkers for neurology, orthopedics, cardiovascular, maternity and other departments.
አሰራሩንና አርክቴክቱን ለጊዜው እንተወውና ቶማስ እንዳለው ሆስፒታሉ የተዋቀረው በምእራባውያን የአስተዳደር ደረጃ ነው፡፤ የዛሬ 33 አመት ቅልጥ ያለጦርነት መሃል ብረሃ ላይ ያለ ተራራ ቦርቡረው ከቦንብ ጥቃት ነጻ አድርገው የሰሩት ህንጻ ውስጥ ተአምራት ይሰሩበት ነበር፡፡ግን በዚህ አላቆሙም፡፡ የራሳቸውን የመድሃኒት ፋብሪካም ማቆም ነበረባቸው፡፡
In a bunker farther up the valley, Eritreans manned old pill presses from Manchester, England, producing antimalarial pills, antibiotics, iron tablets. Another machine - from Bologna, donated by an Italian aid organization - manufactures 40,000 capsules a night. (The hospital's equipment, like much of the materiel used by the Eritreans, is generally either bought by the Eritrean Relief Association or donated by friendly aid agencies in Western Europe, Canada, the United States and Australia.) You can see the canisters of E.P.L.F. drugs on the shelves of every mud-brick or stone clinic you visit.
ቶማስ የታወቀ ደራሲና ጋዜጠኛ ነው፡፡ አሳምሮ የጻፈው የሻዕብያ የሆስፒታል አመሰራረት በወቅቱ ታጋይ ኢሳያስን አግኝቶት ነበር፡፡ እንዲህም አለ፡፡"ቁመቱ መካከለኛ ነው" ደግነቱ የቀነሰው የኢሳያስን ቁመት ብቻ እንጂ የናቅፋን ሙሉ ገጽታ በአይነ ህሊናችን እስክናየው ግሩም አድርጎ አስፍሮታል፡፡
ሕዝቡን ለማገልገል በ1970 የተጀመረችው በአንዲት ለእናቷ ተንቀሳቃሽ የጤና ጣብያ ተመችቷቸው አገልግሎት መስጠት ባይችሉ እንኳን ከጊዜ ጋር ወደ 1፣600 ተንቀሳቃሽ ዶክተሮችና 41 አዋላጆች አሰልጥነው በተኗቸው፡፡ 1985 ላይ በ418 መንደሮች ቋሚ የጤና ባለሞያዎች፤ 150 አዋላጆች ከፍ እያለ ደሞ በ6 የአስተዳድር ወረዳዎች የጤና ጣቢያ ገንብተዋል፡፡ይህ ሁሉ የሚከናወነው ለጥቂት ጊዜ ከተማው ከወታደር ነጻ ሲሆንላቸው ነው፡፡
ይህን ሁሉ ድካምና ልፋት ጠይቆ የተዘጋጀው ባለሞያና ጣቢያ ታካሚውን ማሳመን ደሞ ሰማይን የመቧጠጥ ያህል በጣም ከባድ ነበር፡፡ በተለይ ከወለዱ በኋላ የማህጸን በራቸውን የሚሰፉ ጎሳዎች፡ እንደምንም ብለው ያዋልዷቸውና በባህላቸው መሰረት እንደነበረው መልሳችሁ ስፉን ይሏቸዋል፡፡ እነሱ ደሞ "እምቢ አንሰፋም"ይላሉ፡፡ ከዛ ጤና ጣቢያ ለመውለድ ያድሙባቸዋል፡፡ "ንጽህናችንን የሚያረክስ ጉዳይ መጣብን! አንሰፋም አሉን፡፡" ይሉና ጤና ጣብያ ከመውለድ በወሊድ ሞት ይጠቃሉ፡፡(የደራሲውንና የመጽሃፉን ስም የረሳሁት ኤሪትራዊ ዶክተር ነው፡፡ከታሰረበት የደርግ እስር ቤት በሌሊት ሻዕቢያ ሰርቀው አምጥተውት እራሱን ሳህል አግኝቶ ያገለገለው ዶክተር የጻፈው ነው፡፡ወይም አልሰፋም ብሎ ያመጸው ዶክተር! አሊያም ሻዕቢያ የሰረቀው ዶክተር)
እንዲህ ሲቸግር ማስተማሩ ይቀላል ተብሎ ቋንቋቸውን የሚናገር ሰው ጠፍቶ፡ጥግ አፋር የዘመተች ታጋይ ሃፊዛ ተፈልጋ ተገኘች፡፡ ዘላኖች በመሆናቸው እስኪመጡ ተጠብቆ ሃፊዛ ልታገኛቸው ሄደች፡፡ ሆኖም ቁምጣ የለበሰው አፍሮው ሃፊዛ ስለወንድ ተቆጥሮ እደጅ ነው ያገኙት፡፡ ድምጹ የሴት ሆኖባቸው በሳቅ ሊሞቱ ነበር እንጂ! እንዲህ ተገላልጦ የሚሄድ ወንድ ቢሆን ነው፡፡ ሴትማ ብትሆን ኖሮ ተሸፋፍና አብራቸው ኢግላ የሚባለው ቤታቸው ውስጥ ያስገቧት ነበር፡፡ ሃፊዛ በ10 አመቷ ወላጆቿ ተገለውባት ድርጅቱ ያሳደጋት ባለሞያ ናት፡፡ ዛሬ በዚህ ጎሳና በድርጅቱ መሃል የተፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታት ነው የተገኘች፡፡ ለሁሉም ወንድም ሴትም ያልሆነ ፍጥረት ጋር ሊወያዩ ፈቃደኛ አልሆኑምና ያለምንም ውጤት ተለያዩ፡፡ሃፊዛ እንደነሱ እየለበሰች አግባብታ ጥቂት ሴቶች አስልጥና ቦታዋ ተመለሰች፡፡እነሱም ቀሪውን እያስተማሩ፡ ዛሬ አይደለም መሰፋት የሴት ልጅ ግርዛት ሙሉ ለሙሉ ቀርቶ የጤና ጣብያ በስተቀር የትም አይወልዱም፡፡(ከኤሪ ቲቪ የተገኘ)
ሃፊዛ በአሁን ሰአት አንድ ተቋም ታስተዳድራለች፡፡ አልተነገረላትም እንጂ በሙስሊም እህቶቻችን ላይ የጀመረችው አብዮት የራሱ መጽሃፍ ይወጣዋል፡፡ ቀለም መቁጠር የማይችሉ ሴቶችን በምልክት እያስተማረች ነው ዘመናዊ አዋላጅ አደረገቻቸው፡፡
ከነጻነት በኋላ የተሰራው የራሱን አሻራ አሳርፏል፡፡ በመለንየም ጎል ከተሰጣቸው ጊዜ አስቀድመው ግባቸውን አሳክተው በአለም አቀፍ መድረክ ተሸልመዋል፡፡ ወባን አጥፍተዋል፡፡ የክትባት ሽፋን አሁንም በምእራባውያን ደረጃ ይሰጣል፡፡ ተላላፊ በሽታ ጠፍቷል፡፡ ኤድስ ከ2% በታች ነበር አሁን ከዛም በታች ወርዷል፡፡ የአንደኛ ደረጃ አስተማሪዎች፡ ተማሪዎቻቸውን ጥርስ አይንና ጆሮ ለመመርመር የሚያበቃ መሰረታዊ ስልጠና ይሰጣቸዋል፡፡ ችግር ሲያገኙ ተንቀሳቃሽ ሃኪሞች ይመጡና አስፈላጊው ህክምና በነጻ ይሰጣል፡፡ መነጽር ለሚያስፈልገው እንዲሁ፡፡የአቅማቸውን ሁሉ ያደርጋሉ፡፡ በቅርቡ የካንሰርና የልብ መታከሚያ ተቋም ከፍተዋል፡፡
የሳዋ አነሮች ፎቶ(ኤሪ ቲቪ) ከቀይህ ባሕሪ ፕሮፋይል፡
ክፍል ሁለት ይቀጥላል