Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Ejersa
Member
Posts: 3978
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

12.12.12 የተባለው የዶሮ ብልት ተቃውሞ ከሸፈ!

Post by Ejersa » 18 Aug 2020, 17:37

12 12 12 በሚል መጠሪያ በዛሬው እለት በመላው ኦሮሚያ የተጠራው የኢኮኖሚ ማዕቀብ አልፎ አልፎ መጠነኛ ጫና ቢያሳድርም በመላው ክልሉ እንቅስቃሴ መኖሩ ተገለጸ፡፡ በአዲስ አበባ ሁሉም በሮች እንቅስቃሴ መኖሩና ወደ የትኛውም ስፍራ ተሸከርካሪዎች ተሳፋሪዎችን እየጫኑ መዋላቸውን ከስፍራው ዘጋቢያችን ያደረሰን መረጃ ያሳያል፡፡ በተለይም በአዲስ አበባ መርካቶ አካባቢ በሚገኘው ዋና አውቶብስ ተራ እና በቃሊቲ አውቶቢስ ተራዎች አልፎ አልፎ ወደ ተወሰኑ ከተሞች የሚጓዙ ተሸካርካሪዎች በቂ አቅርቦት ባለመኖሩ የተወሰኑ ሰልፎች ቢስተዋሉም መደበኛ እነቅስቃሴ ግን ስለመኖሩ የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ስዩም ጌቱ ያደረሰን መረጃ ያሳያል። በኢሉባቦር መቱ ከተማ፣ በአምቦ እነዲሁም በወሊሶ በኩል ወደ ተለያዩ አቅጣጫዎች የሚያስተላልፉ መንገዶች ሙሉ ክፍት ሆነው ተሸካርካሪዎችን ሲያሳልፉ መዋላቸውን ማረጋገጥ ተችሎአል።

ከሻሸመኔ አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቨሌ የሰጡት የከተማዋ ነዋሪዎችም በማህበራዊ ሚዲያ በኩል የቀረበውን የትራንስፖርት እቀባ ጥሪን ተከትሎ በከተማዋ እንቅስቃሴ ባይገታም ከወትሮ ባነሰ ሁኔታ ቀዝቀዝ ብሎ መዋሉ ተገልጾዋል፡፡ የዛሬውን የክልሉ እንቅስቃሴ አጠቃላይ ሁኔታን በማስመልከት መግለጫ የሰጠው የኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካላት የቀረበው የትራንስፖርትና የኢኮኖሚ ማዕቀብ ጥሪ ከሽፏል ሲል ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡ የክልሉ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ሰሞኑን ከህብረተሰቡ ጋር ውይይቶች ሲደረጉ እንደነበር ገልጸው ህብረተሰቡ የመልካም አስተዳደር እና የህግ የበላይነት ክፍተቶች እንዲመለስለት እንጂ ልማቱን የሚደናቅፍ ጥሪ አለመቀበሉን ለአምስተኛ ጊዜ የተጠራውን ማዕቀብ በማክሸፍ አረጋግጠዋል ብለዋል፡፡ ኃላፊው ከእንግዲህ በክልሉ የህግ የበላይነትን በማስጠበቅ ላይ ደርድር እንደሌሌ በመጠቆም መሰል ጥሪን የሚያስተላልፉትን ባንዳ በሚል እንደጠርዋቸዉ ስዩም ጌቱ ከአዲስ አበባ ያደረሰን ዜና ያሳያል።