Re: A POEM DEDICATED TO ATO ASHAGRE: POOR ETHIOPIA: አባይን ከደፈረው መሪ ወደ ግጥምን የደፈረ ወፈፌ መሪ ተሸጋገረች.
እኔ ብነካ መንግስታችን ተነካ ብለው ከሰበታ፣ ከሱሉሉታ ነቅለው ሊመጡልኝ ነበር ብሎ ሲናገር ያልተረዳው ነገር ቢኖር ምን ያህል የናንተ የጎሳ ዋሻ አስተሳሰብ እንደበከለው ባለመረዳት ነው፡ ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኢትዮጵያ ነን ብሎ ለተናገረ ሰው ፤ ሰበታና ሱሉልታ ይደርሱልኛል ብሎ ሲናገር እንደምሰማት የሚያስቅ ነገር የለም ፡ ኢትዮጵያ እያለ ሱሉልታ ይደርሱልኛል ፡ አየህ ጭንግፍ ሀሳብ እናንተ ተሸክማቸሁ የምትኳትኑት አብይም እንደ ጉንፋን ሲይዘው የናንተን ቫይረስ ነው ሲያነጥስ የሚያወጣው፡ ጉንፋኑን እንተገሳዋልን ከናንተ ካንሰር አንጻር ፡፡ ምንግዜም የኢትዮጵያን ታላቅነት ሲናገር ሲያያችሁ በተለይም ደግሞ አብይ ሲናገረው ዛራችሁ ይነሳይ ፤ጨሌህን አጥልቀህ ዛርህ እስኪወጣልህ ድረስ ማጓራት ትችላለህ፡፡ ስለዚህ ይህንን ሆድጂፖጂ ዝባዝንክ ግጥም ነው ብለህ ሰው ፊት ባታቀርበው ይሻልህ ነበር ፡