የሎሬት ሰላም ሽልማት ተሸላሚው ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ መሀመድ በሲቪል ድርጅት ስብሰባ ላይ የዋሸው የበሬ ወለደ ውሸት፤ ምርጫን በማጭበርበር በተመለከተ ወይም ደግሞ ስላስመዘገቡት የኢኮኖሚ እድገት ቢሆን ምንም አልነበረም ፤ ሙልጭ አርገው የሚዋሹት ስማቸው ዘራቸው ሀይማኖታችው ተለይቶ ስለሞቱ ኢትዮጵያዊያን ነው ፤ አብይ የደረሰውን ጥቃት አምኖ ነገር ግን ይህንን ጥቃት ያደረሱት ጥቂት የተደራጁ አክራዎች ናቸው የትልቁን የኦሮሞን ህዝብ አይወክሉም ፤ ከሞቱትም ውስጥ ኦሮሞዎችም አሉ ብሎ መደምደም ሲችል ይህንን ነው አብይ ያለው ፡፡
“ ይህ ግድያ እናንተም እንደምታውቁት ብሄር ተኮር አልነበረም በአብዛኛው የተገደለው ኦሮሞ ነው ያውም ሁለት ሶስት እጥፍ “
ኦዎ እንደመሪ ነገሮችን ማረጋጋት ፤ ህዝቡን ማረጋጋት ይጠበቅበታል ነገር ግን የዚህ የዘር ጭፍፍጨፋ ሰለባ የሆኑትን ነፍጠኛ ተብለው የተጨፈጨፉትን አማሮች ፤ ጉራጌዎች ፤ትግሬዎች ሞት በመሸፈን ፍጹም መሆን ነበረበት? እውነት ኦሮሞዎች የዚህ ዘር ማጥፋት ሰለባ ከሆኑ ለምንድነው በየቤተክርስቲያኑ ተጠልለው የሚገኝት ማህከል ያላገኝናቸው? ለምንድነው የኦሮሞ ቢዝነሶች እየተዘለሉ የአማራው የጉራጌው ቢዝነሶች የተቃጠሉት ፤ አብይ የኢትዮጵያ ህዝብን እስካሁን እዲከተለው ያደረገው እነ ለማ መገርሳ ሲንሸራተቱ ሲያይ ፤ ብዙ አብረውት ከጉኑ አብረውት ሲሰሩ የነበሩት ጓደኞቹ ብዙ ዝባዝንኬ ሲናገሩ ሁሉም ነገር ጥሩ ይሆናል ብለው ያሰቡት በአብይ ባላቸው እምነት ነበር ፤ ከዚህ በፊትም ጀዋር በጠራው አመጽ እንዲሁ በዘርና በሀይማኖት ተለይተው እንደተጨፈጨፉ እየታወቀ ኦሮሞ ነው አብዛኛው የተገደለው በሚል የዘር ሀይማኖትን ተገን ያደረገውን ጭፍጨፋ አለባብሶ አለፈው ፤ በዚያም ወቅት ቢሆን አሁንም ለተጎዱት ሀዘኑን አልገለጽም ፤ ወይም ከአሁን በኋላ አይደገምም ብሎ ቃል አልገባላቸውም ፤ አሁንም የተሰራውን የዘርና የሀይማኖት ተኮር ጭፍጨፋውን ሽፋን እየሰጠ ነው ፡፡ እስካሁን ያለውን የህዝብ እምነት ምን ያህል እንደናደው ምንም አልገባውም ፡፡ ከዚያ ደግሞ ይባስ ብሎ እስክንድር ነጋን በህዝብ ጭፍጨፋ ተሳትፏል ፤ በሚሊየን ገንዘብ አውድሟል ብሎ ከሶ፤ ምስክሩም ፤ ችሎቱም ዝግ እንዲሆን ተወስኗል ፤ የነጀዋርና ፤ የበቀለ ገርባስ ለህዝብ ክፍት ሊሆን ነው ወይስ ዝግ ነው የሚሆነው? አብይ እግሩ ላይ እየተኮስ ነው፡፡
Hear and judge this Oromo Gentleman’s sister testimony: this is a testimony from the eyes of the storm, Shasemene.
https://www.facebook.com/10001239117062 ... 305253266/