ኮ/ል አብይ ታማኝ ተቃወሚዎችን ጠርቶ ሲያወያይ በመካከሉ ወደ ትግራይ ሀሜት ገባ፡፡ TPLF ምርጫ ማካህዱ ሳይሆን ምርጫ አካሂዶ አረና ፓርቲ አሸንፏል ቢል ግን ከፌደራል መንግስት ጋር ጦርነት ውስጥ ይገባል ሲል ቀልደ እኮ፡፡ የእስኮርቷ ጉዳይ ምነው ተደጋገመች?
አጭቤው ሲያብራራም፤ TPLF በሥልጣን እንዲቀጥል እኮ ፈደሬሽን ም/ቤት ወስኖለታልና በዚያም በዚህም ይቀጥላል፡፡ ስለዚህ TPLF ምርጫ አካሄደ ብለን ያንን አንቃወምም፡፡ ነገር ግን አረና ፓርቲ ያልተፈቀደለት ፓርቲ ስለሆነ ተመረጠ ቢባል ህገ-ወጥ ስለሆነ ከፈዴራል መንግስት ጋር ጠብ ውስጥ ይገባል በማለት ታማኝ ተቃዋሚዎቻቸውን ለማታለል ሞክረዋል፡፡
እኛ ግን እንጠይቅና የኮ/ል አብይን ቅጥፈት እናጋልጠው፡፡
1. ከህወሀት ሌላ ወደ ምርጫ ገብተው ስልጣን ሊቀራመቱ ያሉት ሌሎች ፓርቲዎችስ ልክ እንደ አረና በኮ/ል አብዮት ለምን የጠብ ማንሻ ምክንያት ሆነው
አልተጠቀሱም?
2. TPLF እኮ አሁን ሌላ ምርጫ ካካሄደ ከዘጠኝ ወር በኃላ ይቅርና ከአምስት ዓመት በፊት ሌላ ምርጫ ላያካሂድ ነው፡፡ ስለዚህ በአንድ ሀገር ሁለት
የምርጫ ዙር ሊኖር ነው ወይስ ፈዴራል መንገስት ራሱን አጄስት (አስታካክሎ) እንደሁኔታው ምርጫ ሊያደርግ ነው፡፡ ይኸ ነው የኮ/ል አብይ
ውርደት፡፡
3. አረና መቼ ሊወዳደር ነው? ከአምስት ዓመት በኃላ TPLFን ይቅርታ ጠይቆ?