ቄሮ ለሁለት ተከፈለ
ሁሉም እየተነሳ የቄሮ አደራጅ ነኝ የሚባልለት የቄሮ ስብስብ ለሀለት ተከፍሏል:: ቄሮዎቹ ለሁለት የተካፈሉት የሸዋ እና የወለጋ ቄሮዎች በአንድ ላይ የአርሲ የባሌ እና የሃረርጌ ቄሮዎች ደግሞ በሌላ ጎራ ተከፍለዋል።
የሸዋ እና የወለጋ ቄሮዎች QBO(Qeerroo bilisuummaa Oromo) በመባል ነው የሚታወቁት።
ክፍፍሉም በመጪው ሰኞ በ #OMN ታውጆ የነበረውን አድማ አርሲዎች ናቸው ውጪ ተቀምጠው ያወጁት በማለት QBO ቹ አድማውን በመቃወማቸው ነዉ። በሀጫሉ ሁንዴሳ ሞት ምክንያት ከኦሮሚያ ክልል በአርሲ ውስጥ ነው ውድመትና ግድያ የተፈፀመው:: QBO ዎች የትኛውንም አድማ መጥራት የሚችለው QBO ብቻ ነውም ብለዋል። በዚህም የተነሳ በትናንትናው እለት ከፍተኛ ውዝግብ አስነስቶ ነበር አሁንባለው መረጃ መሰረት OMN ለመጪው ሰኞ የጠራው አድማ መሰረዙን OMN ከሰአታት በፊት በሚዲያው አስታውቋል።