ጄኖሳይድ ተፈጸመብን፣ በዘርና በኃይማኖት ተለይተን ተበደልን፣ ሰፋሪዎች ተብለን ነው ይኅ ሑሉ የሚደርስብን እያሉ የሚጮኹትን ድምጽ የሰማ በሚመስል መልኩ በኦሮሚያ የሰፈረው የነፍጠኛው መንግስት ያወጣውን መግለጫ አነበብኩ፡፡ የተጎዱትን መልሰን እናቋቁማለን የሚልም አለበት፡፡ መልካም ነው፡፡ ግን የት ላይ ነው ሊያቋቁሙዋቸው የተፈለገው?
በኦሮሞ ላይ የሀበሻ የፓለቲካ በላይነት እስካለ ድረስ ማንም ከሀበሻ መንግስት ጋር የሚወግን ሠፈሪ ሰላም ማግኘት ይችላል ብሎ ማሰቡ ራሱ የጠና አይመስልም፡፡ እናም እስከ አሁን የተከሰተው ዓይነት መገዳደል መልሶ አይቀሰቀስም ብሎ ለመገመት ያስቸግራል፡፡ ስለዚህ የፓለቲካ ትግሉ በኦሮሞና በአማራ መንግስት መካከል መቀጠሉ የሚጠበቅ ሆኖ ጄኖሳይድ ደረሰብን የሚሉትን ሰፋሪዎች ወደመጡበት ትውልድ ሀገራቸው ሄደው በዘለቂነት እንዲቋቋሙ ማድረግ አይሻልም ወይ?
ለምንድን ነው በስለላና በመሳሰሉት የፓለቲካ ሥራዎች ሊጠቀምባቸው መንግስት የሀበሾች ሰፈራ በኦሮሚያ ውስጥ እንዲቀጥል ችክ የሚለው? ነፍጠኞቹ ከትውልዳቸውም ውስጥ ዉጪ ሀገር ያለ ዘመድ አፈላልገው ርዳታ ጠይቀው በዘላቂነት ከሚመቻቸው አካባቢ ለመኖር ሲያመቻቹም ብዙ አይታይም፡፡ ለምን?
በርግጥ ኦሮሚያ ነጻ ከወጣች በኃላ እኮ እንኳን በጠይም ቀለማቸው የሚመስሉን ሀበሾች ይቅርና ቢጫው ወገንም ኦሮሚያ ውስጥ መኖር መብት ሊሆን ነው እኮ፡፡ ስለዚህ ሰፋሪዎችን በዘላቂነት ማቋቋም የመንግስትና የዘመዶቻቸው ጥረት ቢሆን ለሰላም አስተዋፅኦ አለው እላለሁ፡፡ የመንግስት መግለጫም ያሳሰበኝ ይህን ጥረት ስላላመላከተ ነው፡፡