Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Meleket
Member
Posts: 4808
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

ምክር ቢጤ ለኢትዮጵያዉያን አርቲስቶችና የጥበብ ሰዎች በሙሉ

Post by Meleket » 03 Jul 2020, 04:53

አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ኢትዮጵያዊው ወንድማችሁ፡ በጥበቡና በወኔው ግፈኞችን ፊት ለፊት ተጋፍጦ እርቃናቸውን ያወጣ ድንቅ የኦሮሞና የኦሮምያ ተወላጅ፡ ወጣት የልጆች አባትና ከልቡ በፈለቀ ፍቅር በዓላማ ጽናት በመታገል፡ ለዘመናት በህዝብ ጫንቃ ላይ ሲንፈላሰስ የነበረን አረመኒያዊ ስርዓት በመገርሰስ ጉልህ ሚና ያበረከተ ብርቅና ድንቅ የአንቦ ልጅ ነው።

ይህ ለጋ ወጣት መድረክ ላይ እንደ አንበሳ እየተጎማለለ የጥበብን ኃያልነትና የዜጎችን እኩልነት በድፍረት ገልጾ የጨለማ ኃይሎችን ዳግም እንዳያንሰራሩ አድርጎ ቀልባቸውን ስለገፈፈው፡ ነብሰበላዎቹ ህይወቱን ቀጥፈውታል። የኦሮምያ ክልላዊ መንግስትም የዚህን የጥበብ ሰው አኩሪ ታሪኩንና ገድሉን ይበልጥ ለመግለጥና ለዘመናት ተሻጋሪ በሆነ መልኩ ለትውልድ ለማስተላለፍ በአዲስ አበባ ሀውልት እንደሚያቆምለት ሰምተናል። የጨለማ ኃይሎችን ተንኮልና ሴራ እየገለጸ ለዘመናትና ለትውልድ እያስተላለፈ የሚኖር በጎ ግሩምና ክቡር ተግባርም ነው።

ኢትዮጵያዉያን የጥበብ ሰዎች ባጠቃላይ በተለይም ተመሳሳይ ድፍረትና የትግል ወኔ የዓላማ ጽናትና ቁርጠኝነት ያላችሁ እነ ቴዲ አፍሮና እነ ወዘተ እንዲሁም የአርትስ ቲቪዎቹ ጦቢያን በጃዝና ወዘተዎች ማለትም ተመሳሳይ ዝግጅቶች ጭምር፣ የጥበብን ኃያልነትና ባፈለቀው ልዩ የጥበብ ተሰጥኦው ምክንያት መስዋእት የሆነውን ኢትዮጵያዊ ወንድማችሁን ሀጫሉ ሁንዴሳንና ጥበብን ለማክበር፡ እንዲሁም ተስፋ የቆረጡ የጨለማ ኃይሎችን እኩይ ተግባር ይበልጥ ለማጋለጥ፡ አምላክ በጥበቡ በሰጣችሁ ተሰጥኦ ተጠቅማቹ፡ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ ግሩም ኢትዮጵያዊ ሙዚቃ (እንጉርጉሮ) ለአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳና ተመሳሳይ ታሪክ ላላቸው ኢትዮጵያዉያን በሙሉ ታሪካዊ ግጥምና ዜማ ስሩለት እስቲ።

ኢትዮጵያዉያን የጥበብ ሰዎች ኢትዮጵያዊውን የጥበብ ሰው ሀጫሉ ሁንዴሳን ዘክሩት፤ ኣዎ ያኔ የኢትዮጵያዉያን አርቲስቶች ኢትዮጵያዊ ህብረዜማና ቅላጼ ቅኔና እንጉርጉሮ ከዳርእስከዳር ሲያስተጋባባቸው ግዜ የቃኤል መንፈስ የተጠናወታቸው የጨለማው የጥፋት ኃይሎች ይበልጥ ጨርቃቸውን ጥለው እርቃናቸውን ወጥትው እርማቸውን ያወጣሉና! በጨለማውና የጥፋት ኃይሎች መቃብር ላይም ኢትዮጵያ በሰላማዊው የእድገት ጎዳና ይበልጥ ትረማመዳለችና!

ክብርና ሞገስ ለድንቁ ኢትዮጵያዊ አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ!

Meleket
Member
Posts: 4808
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ምክር ቢጤ ለኢትዮጵያዉያን አርቲስቶችና የጥበብ ሰዎች በሙሉ

Post by Meleket » 04 Jul 2020, 05:24

ይህቺ ምክራችን ቴዲ አፍሮን ብቻ ሳይሆን አለማየሁ እሸቴን ንዋይ ደበበን ጠሃየ ዮሃንስን ታማኝ በየነን እነ ጎሳየን እነ ማህሙድ አህመድን እነ አስቴር አወቀን እነ ሃመልማል አባተን ጃኖ ባንዶችን ጦብያ በጃዞችን ሀገር ፍቅሮችን ብሄራዊ ቲያትሮችን የተለያዩ የቴሊቭዝን መርሃግብረኞችን ወዘተዎችንም ጭምር ይመለከታል!

እርግጥ ነው የአምቦው ፈርጥ ሎሬት ፀጋየ ገብረመድኅን በህይወት ቢኖሩ ኖሮ፡ የዚህን ብርቅና ድንቅ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ታሪክ የአጤ ቴዎድሮስን ታሪክ በምናባቸው ከደረሱልን በበለጠ ይጥፉልን ነበር።

ለጥበብ ሲል የተሰዋን የጥበብ ሰው መዘከር ቅዱስ አላማ ነው!

ክብርና ሞገስ ለድንቁ ኢትዮጵያዊ አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ!

Post Reply