Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 40229
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የጉራጌ ክልል እና የጉራጌ ተቋም ፤ The Gurage Institute

Post by Horus » 22 Jun 2020, 04:32



በእኔ አስተያየት ጉራጌ በአስቸኳይ የሚፈልገው የመደራጀት አይነት የዜና ሚዲያ ብቻ ሳይሆን የእውቀት፣ የጥናት፣ የምርምር፣ የታሪክ፣ የባህል፣ የቋንቋ፣ የኤቲክስ እና የአርት ምርምር ተቋም ነው።

ጉራጌ ቢያንስ በአራት ግዙፍ መስኮች እውቀት መር ሳይንስ ገፍ የሆኑ ስራዎች ተጋርጠውበታል ።

ጉራጌ አንድነቱ የሰመረ ፣ ጠንካራ፣ የተረጋጋ፣ የሰከነ ሕዝብ መሆን ግድ ይለዋል ። ይህን አለ መሆን ወድቀት ነው። ያንድ ህዝብ ተቀደዳሚ አላማ ይህ ነው።

ጉራጌ ዴሞክራሳዊ፣ ነጻ፣ ፍትሃዊ፣ በግለሰብ ልዕልና፣ በሰው ልጅ ክቡርነት፣ በጉራጌ ዴንጋ፣ በጉራጌ አርዴ ሁሉ ወንድማማችነት፣ ዘማችነት የረጋ ማህበረሰብ እድዲሆን ድግ ነው ። ይህን አለመሆን ውድቀት ነው። የጉራጌ ነፍሰ ህዋስ፣ የህልውናው ሁሉ ትርጉም የእያንዳንዱ ጉራጌ ሰብ ልዑልነት ስለሆነ ።

ጉራጌ የበለጸገ፣ ባለጸጋ፣ ሃብታም፣ የተማረ፣ ባለ ሳይንስ፣ ባለ ቴክኖሎጂ፣ ባለ እውቀት እና ጤነኛ፣ አካላዊ፣ አይምሮአዊ፣ ሳይኮሎጂአዊ፣ አስተሳሰባዊ ህይወቱ ጤና የሆነ ሕዝብ ሊሆን ግድ ነው። ድሃ ሕዝብ፣ ያልተማረ ሕዝብ፣ ቴክኖሎጂ የሌለው ሕዝብ፣ ጤነኛ ህይወት የሌለው ሕዝብ የወደቀ፣ የከሸፈ፣ ስኬት አልባ ደካማ ሕዝብ ስለሆነ ።

ጉራጌ ሲጀመርም ፈጣሪ ሕዝብ ነው። የጉራጌ ካልቸር የፈጠራ፣ የስራ፣ የፍልሰፋ፣ የኪነት፣ የስነት፣ ካልቸር ነው ። ጉራጌ ሲጀመርም ከተፈጥሮ ጋር በሰላም፣ በኬርነት የሚኖር ካልቸር ነው። ጉራጌ ጥልቅ መንፈሳዊ፣ ቸር ፣ ርዕታዊ፣ ትሁት፣ የሰከነ ካልቸር ያበለጸገ ሕዝብ ነው። ይህን ወድ መንፈሳዊ፣ ክሬቲቭ ካልቸር መጠበቁ ግድ ይላል።

ይህ ሁሉ እንዲሆን ጉራጌ ታሪኩን፣ ቋንቋውን፣ እምነቱን፣ እሴቱን፣ ባህሉን፣ የኢኮኖሚ ፣ የፖለቲካ፣ የሶሺያ፣ የካልቸር፣ የሳይንስ፣ የቴክኖሎጂ ምርምር፣ ግስጋሴና አቅጣቻ የሚቀድ አንድ ግዙፍ የመላ ጉራጌ ኢንስቲቲዩት ባስሸኳይ ማቆም ግድ ይለናል።

ትልቁ ቁም ነገር ዞን፣ ክልል፣ አገር ምናምን አይደለም ። ዛሬ እነዚህን እጅግ ታሪካዊ ግቦች ላይ ስኬታማ መሆን ነው። ኬር ዬሁን !!





Post Reply